Site icon ETHIO12.COM

በጅግጅጋ- አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ፣ የመከላከያ ሠራዊትን የሚያገን ሰልፍ ተካሄደ

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በገዛባቸው 27 ዓመታት በሰራው ህዝቡን የመከፋፈል ስራ በለውጡ ማግስት “ኢትዮጵያውያንን በጋራ የሚያቆማቸው ነገር የለም፤ ሀገሪቱም በራሷ ጊዜ ትፈራርሳለች” ብሎ ቢጠብቅም ህዝቡ ግን ለለውጡ መንግስት ያሳየው ድጋፍና አንድነት ሀሳቡን ከንቱ አድርጎታል ነው ያሉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር።

ይህ ለአሸባሪው ህወሓት ሕልውና አደጋ ነው ብለው ያሰቡ የሽብር ቡድኑ አባላት፤ ኢትዮጵያን በሀይል ለመበተን ከውጭ ሀገራት ጋር በማሴር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአሸባሪው ህወሓት የአገዛዝ ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂ የነበረው የሶማሌ ማህበረሰብም ይህ ቡድን ስርዓተ ቀብሩ እስኪፈፀም ከመከላከያና ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማስወገድ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎችም ጁንታው ዳግም ኢትዮጵያን የመምራት አቅም እንደሌለው በመገንዘብ ሀገሪቱን እኔ ካልመራኋት ትበተን በማለት የከፈተውን ትንኮሳ ለመቀልበስ በሚችሉት ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የኢብኮ ዘገባ ያሳያል።

በጅግጅጋ ስታድየም በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ኢዜአ

Exit mobile version