Site icon ETHIO12.COM

መሳሪያና ገንዘብ በቀይ መስቀል መኪና ጭነው ወደ ደቡብ ጎንደር ሰርገው የገቡ የህወሀት ተላላኪዎች ተደመሰሱ‼

በአካባቢው በፀጥታ ስራ ላይ የነበሩ የመረጃ ምንጫችን በደቡብ ጎንደር ዞን ልጫ በምትባል ከተማ 6 ስናይፐር፡ በርካታ ክላሽንኮፍ መሳሪያና ተተኳሽ ጥይት እንዲሁም እስከዚህ ሰዓት ያልተቆጠረ ሁለት ኩንታል ብር በቀይ መስቀል መኪና ጭነው ሰርገው የገቡ የህወሀት ተላላኪዎች አካባቢያቸውን ሲጠብቁ በነበሩ ታጣቂዎች ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ተደምሰዋል ብለዋል።


READ MORE

ሰርጎ ገቦቹ አቁሙ ሲባሉ መኪና ለማቆም ፈቃደኛ ባለመሆን ጥሰው ለማምለጥ ሲሞክሩ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመረጃ ምንጫችን ገልፀዋል። ገንዘቡና መሳሪያው ገቢ መደረጉንም ምንጫችን አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉና ተራራ አካባቢ የነበረው የህወሀት ታጣቂ ቡድን ዛሬ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። በዚህም በደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪው በተኩስ ደስታውን ሲገልፅ አምሽቷል።

ESAT

Exit mobile version