Site icon ETHIO12.COM

ህዝቡ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በሰጠው ድጋፍ አሸባሪው በየአካባቢው ድባቅ እየተመታ ነው- አቶ አገኘሁ ተሻገር

ህዝቡ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በሰጠው ድጋፍ አሸባሪው ቡድን በጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች በየአካባቢው ድባቅ እየተመታ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ አሸባሪው ቡድን በወረራቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴቶችን በመድፈር፣ ወጣቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደልና መሰል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜጎችን ከማፈናቀል ባለፈ የግለሰብና መንግስት ሃብት እየዘረፈ መሆኑንም አስረድተዋል።

ወራሪው ቡድን የከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ በተደረገው የክተት ጥሪ ህዝቡ የሰጠው ምላሽ የሚያኮራ ነው ብለዋል።

በዚህም በጠላት ሃይል ላይ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ የልዩ ሃይል፣ የሚሊሻ፣ የፋኖ እና አርሶ አደሩ በየሄደባቸው አካባቢዎች ድባቅ እየመታው መሆኑን አስታወቀዋል።

ይህ ሃይል የአማራ ክልልን ህዝብ አንገት ለማስደፋት፣ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብሎም ለጠላት አጋልጦ ለመስጠት የመጣ አፍራሽ ቡድን በመሆኑ ወደ ክልሉ እንዳይወጣ ህብረተሰቡ በየደረሰበት ተከታትሎ በመደምሰስ የተጋድሎ ጀግንነት ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

Ena

Exit mobile version