Site icon ETHIO12.COM

ትግራይ – ልጆቻችን የታሉ?

በትግራይ የቀሩ ህጻናትን፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን ለሽብር ተግባሩ ለማሰለፍ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ያለው አሸባሪው ህወሓት ከህዘቡ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል። ልጆቻችሁን ወደ ት/ቤት ላኩ ብሎ ህጻናቱን ወደ ዘመቻ ከላከ በኋላ ት/ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ማሰልጠኛነት ቀይሯቸዋል።

በትግራይ የቀሩ ህጻናትን፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን ለሽብር ተግባሩ ለማሰለፍ እንዲያግዘው ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ያለው አሸባሪው ህወሓት እውነቱን እየተረዳ ከመጣው ህዝብ ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ታማኝ ምንጮች ባደረሱን መረጃ፤ የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈጸመባቸው የአፋር እና የአማራ ክልል አካባቢዎችን ደጋግሞ በማሳየት አዲስ አበባ ልንደርስ ነው፤ ሰመራ ከተማን ይዘናል፤ ባቲና ኮመቦልቻን ተቆጣጠረናል፤ በሀገሪቱ የገቢ ወጪ ንግድ ቆሟል፤ ጎንደርን ተቆጣጥረን ባህርዳርን ልንቆጣጠር ትንሽ ቀርቶናል በሚሉና መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች ህዝቡን እያታለለ ሲሆን፤ በዚህም ያገኘነውን ድል ለመቋጨት ሁሉም መዝመት አለበት በሚል በከተሞች የቀሩ ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶችን ለጦርንት ለማሰልፍ እያስገደደ ይገኛል።

መከለከያ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ፣ ትምህርት እንጀምራለን በሚል ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ ካግባባ በኋላ ተማሪዎችን ወደ ውጊያ ማጋዙን የጠቀሱት ምንጮቻችን፣ እንደ መቀሌ፣ ሽሬ፣ አድዋና መሰል ከተሞች ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችንም ማሰልጠኛ አድርጓቸዋል ብለዋል።

እንደ ባንክ ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ክፍት በለመሆናቸው የክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቁ ሳያንስ አሸባሪው ቡድን በሚነዛው የሀሰት “የድል ዜና” መሰላቸት ውስጥ በመግባቱ አሸንፈናል አዲስ አበባ ልንገባ ነው ካላችሁን ወር አለፈው ልጆቻችንስ የታሉ የላክናቸው የት እንዳሉ ሳናውቅ የቀሩትን አምጡ ትሉናላችሁ በሚል ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል።

ይህንን ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎችም በምሽት እየታደኑ ወደ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ በዚህ ምክንያትም ቡድኑ በአፈና መዋቅሩ ተጠቅሞ የሚያደርገው ስለላ የተለየ ሃሣብ የሚሰነዝርና ቅሰቀሳውን የሚቃወም ሰው እስር እንግልትና ግድያ እየተፈጸመበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ህዝብ እየተነገረው ያለው ሰመራ፣ ባቲ ኮምቦልቻና ጎንደር መያዛቸው ሲሆን ቀጥሎም ባህርዳርን በቅርብ እንቆጣጠራለን፣ ቀጣይ ጉዟችን ወደ አዲስ አበባ ነው በሚል ህዘቡን ለማሰባሰብ እየተጠቀሙበት ነው። ህዘቡ እውነታውን እንዳይረዳ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎቹ የሆኑትን ሚዲዯዎች ብቻ እንዲያዳምጥ ይገደዳል።

ለትምህርት ወጥተው እና በየመንገዱ ታፍሰው የተወሰዱ ልጆቻችን የደረሱበትን ያላወቀው ህዝብ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛል። እንደ ምንጮቻችን ገለጻ በመላው ትግራይ ባለው የነዳጅ እጥረት ትራንስፓርት አለመኖሩ እና በክልሉ ሌሎቸ አገልግሎቶች አለመኖራቸው ህዘቡ ክፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ነግረውናል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በመቀሌ እና ሌሎች ከተሞች እናቶች ልጆቻችንን አምጡ በሚል ሰልፍ ማድረጋቸው በኩዊሃ አራት የአሸባሪው ቡድን አመራሮች በህዝብ አመጽ መገደሉ ይታወቃል። በቅርቡም ህጻናትን ለውትድርና የመለምል የነበረ አንድ ከፍተኛ የአሸባሪው አመራር በመቀሌ ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወሳል።

ይህንን የህዝብ ንቅናቄ ለማስታገስ እና የተዳከመ ሃይሉን ለማጠናከር አዲስ አበባ ልንገባ ነው የወጭና ገቢ ምርቶች ወደ ሃገሪቱ እንዳይገባ አድርገናል። ሀገሪቱ እየፈረሰች ነው፣ በቅርቡም አዲስ አበባ እንገባለን በሚል ከፍተኛ ቅስቀሳ እና አፈሳ እያደረገ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version