Site icon ETHIO12.COM

ከመቶ በላይ የተዘረፈ ዕቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መንገድ ተከበው ቆመዋል፣” አማራ ክልል የገባ ጠላት እንዲወጣ አይደረግም”

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከአማራ ሕዝብ ዘርፎ ሊወጣ የጫነበት በመቶዎች የሚቆጠር ተሽከርካሪ በጋይንት መስመር ይዞ ለመቆም መገደዱ ተሰማ። “የአማራን ሕዝብ አዋርዶ የሚወጣና የሚቀር ጠላት የለም፤ ሁሉም በየደረሰበት ጠላትን መደምሰስ አለበት” ሲሉ የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን ጥሪ አስተላለፉ።

ኮሚሽነሩ ይህ ያሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የተቀናጀ ሕዝባዊ ሠራዊት ጋሸና እና አካባቢውን ተቆጣጣረ። ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ ኮን፣ አርቢት፣ አሁንተገኝና ሐሙሲት ከጠላት ፀድተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለሚዲያ ባስታወቁበት ወቅት ነው።

ህዝብ በደጀንነትና ከጠላት ጋር በመዋደቅ፣ መረጃ በምስጠት የጅግንነት ተግባር እየፈጸመ መሆኑን ያወሱት ኮሚሽነሩ፣ ጠላትን የሚመራ ጥቂት ባንዳ መኖሩን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ “ሕዝቡም መሬቱም የእኛ ነው” ጠላት መፈረካከሱንና መውጪያ ማጣቱን አመልክተዋል። ምክትል አዛዡ “ማንኛውም ሰው ጠላትን ማጥቃት አለበት” ሲሉ የገባ ወራሪ ሳይወጣ መደምሰስ እንዳለበት አመልክተዋል።

ሕዝቡ በመዋጋት፣ መረጃ በመስጠት፣ ስንቅ በማቀበልና በሌሎች መስኮች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው። “በአጭር ጊዜ የአማራን ክልል ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ እንደምናደርገው እርግጠኛ ነኝ” በማለት የተመዘገበውን ድል ዘርዝረዋል። ለዚሁም ድጋፍ የሆኑ ከሠራዊቱ ጋር እየተዋደቁ ያሉ የአካባቢ መሪዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የተቀናጀ ሕዝባዊ ሠራዊት ጋሸና እና አካባቢውን ተቆጣጣረ። ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ ኮን፣ አርቢት፣ አሁንተገኝና ሐሙሲት ከጠላት ፀድተው እንደተያዙ ያስታወቁት የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን፣ ” ❝አሁን የገባው ኃይል መውጣት የለበትም። ወደ ሀገሩ ሊመለስ አይገባም። መሬታችን የረገጠ ኃይል በዚያው መቅረት አለበት፤ በቂም በቀል ዘርና ሀብት ለማጥፋት የመጣ ቡድን መውጣት የለበትም። ከተቻለ መያዝ ካልተቻለ ደግሞ መውደም አለበት❞ ሲሉ ሁለት አማራጭ ብቻ መኖሩን አስታውቀዋል።

የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን እንዳሉት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ሕዝባዊ ሠራዊት የጋሸናን መስመር ቆርጦ አካባቢውን እንደተቆጣጠር በወሎ ግንባር ለጋዜጠኞች መግላጫ ሲሰጡ እንዳሉት፣ ሠራዊቱ በሰሜን ወሎ አራት ወረዳዎችን ተቆጣጥሮ ተጋድሎ እያደረገ ነውም ብለዋል። ልዩ ኃይሉ ከመከላከያ ሠራዊትና ራሱን ችሎ በሰሜን ወሎና በደቡብ ጎንደር ደጋማ ቦታዎች ውጊያው እያካካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።

ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ኮን፣ አርቢት፣ አሁንተገኝና ሐሙሲት ከጠላት ፀድተው ተይዘዋል ብለዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ማኅበረሰቡ ባደረገው ትግል ነው ቦታዎችን የተቆጣጠረው። ኅብረተሰቡ ለሠራዊቱ ስንቅ በማቀበል፣ በመዋጋትና መረጃ በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል። የደፈጣ ውጊያ በመውጣት፣ የጠላትን መረጃ በመስጠት እያደረገው ያለው ተጋድሎ ከፍተኛ መሆኑን ነው የገለፁት። ለጦርነቱ አስተዋጽኦ የሌላቸው ሰዎች ጠላት በዚህ ገባ በዚህ ወጣ እያሉ በውሸት ሕዝብን ከማደናገር እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

ሁሉም የአማራ ሕዝብ ጠላትን መውጋት እንደሚገባውም አሳስበዋል። ሠራዊቱ ከውጊያ በላይ ፈታኝ የሆኑ ተፈጥሯዊ ነገሮችን በመቋቋም የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ያለ ረፍት እየሠራ ነው ብለዋል። ወደ ደቡብ ጎንደር የገባው ኃይል መውጫ መግቢያው እንደተያዘም ገልጸዋል። አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከአማራ ሕዝብ ዘርፎ ሊወጣ የጫነበት በመቶዎች የሚቆጠር ተሽከርካሪ በጋይንት መስመር ይዞ መቆሙንም ጠቁመዋል። የአማራን ሕዝብ አዋርዶ የሚወጣና የሚቀር ጠላት የለም፤ ሁሉም በየደረሰበት ጠላትን መደምሰስ አለበት ነው ያሉት።

ዜናው ከአሚኮና ከሌሎች መረጃዎች የተውጣጣ ነው

Exit mobile version