ETHIO12.COM

ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ አሁንተገኝ፣ ኮን፣ ሐሙሲትና አርቢት ነጻ ወጡ – ጥቃቱ ቀጥሏል

አሸባሪው የትህነግ ሃይል በወረራ ከያዝቸው ቦታዎች በየቀኑ እየተመታ እየለቀቀ መሆኑንን ከተለያዩ ግንባሮች በአካል ተገኝተው የሚዘግቡ የሚዲያ ባለሙያዎች እያስታወቁ ነው። የአማራ ልዩ ኀይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን ጠቅሶ ሚዲያዎቹ እንዳሉት ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ አሁንተገኝ፣ ኮን፣ ሐሙሲት እና አርቢት ወደ መሰረታዊ ባለቤታቸው ተመልሰዋል። ታላቅ ደል ነው።

ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን 

በተጠቀሱት ቦታዎችና ትህነግ መንጋውን አስርጎ ባስገባበት አካባቢዎች ሁሉ ሽንፈት ተከናንቦ መደምሰሱን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን አረጋግጠዋል፡፡

የሀገር መከላከያ የደቡብ ዕዝና ሌሎች የፀጥታ አካላት ባደረጉት ፈጣን ኦፕሬሽን ድል መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡ የሽብር ቡድኑ ከአራት የሰሜን ወሎ ወረዳዎች ተጠራርጎ መውጣቱን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።

በጥቅሉ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ አሁንተገኝ፣ ኮን፣ ሐሙሲት እና አርቢት የተባሉ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸው ነው የተገለፀው። አካባቢዎቹን በኃይል ወሮ በነበረው የህወሓት የሽብር ቡድን ላይ በተሰወሰደ ወታደራዊ እርምጃ በስም የተጠቀሱትን ቦታዎች መልሶ መቆጣጠር እንደተቻለ ታውቋል።

ማስለቀቅ ብቻ ሳይሆን እየተቆራረጠ መግቢያ ያጣውን የወንበዴ ሃይል ህዝቡ፣ ሚሊሻው፣ ልዩ ሃይል፣ መከላከያ በመሆን ተናበው እያጸዱትና እየደመሰሱት መሆኑ ተመልክቷል። ከጋሽና የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት በርካታ እጅ ሰጥተዋል። ለጊዜው መቁጠር በማይቻል ደረጃ ተደምሠዋል። ለማምለጥ እየሞከረ ያለው ሃይል ተከቦ ጥቃት እየደረሰበት ነው። ተጨማሪ የተረጋገጡ የድል ዜናዎች እንደሚኖሩ የአካብቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Exit mobile version