Site icon ETHIO12.COM

ሳማንታ ፓዎር “እህል / ጥይት አልቋል” አሉ

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ትግራይን መልሶ ከተቆጣጠረ በሁዋላ የዕርዳታ ስርጭቱን ሲያደንቁ የነበሩት የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በትግራይ ለተረጂዎች የሚቀርብ እህል ሊያልቅ መሆኑንን ጠቅሰው የኢትዮጵያን መንግስት መውቀሳቸውን ተከትሎ ” ጥይትና መሳሪያ አልቋል” በሚል ቢያስተካከሉት ይሻላል” ሲሉ ዜናውን ባሰራጨው የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ ገጽ አስተያየት ላይ በርካቶች ተቃወሙ።

የኢትዮጵያ ፓርላማ ” አሸባሪ” ሲል የፈረጀው ትህነግ ወደ አማራና አፋር ክልል ወረራ ሲያካሂድ የሰጠው ምክንያት ” መንግስት ዳግም ትግራይን ስለማጥቃት እንዳያስብ አድርጎ ለመምታት ነው” ቢልም በዋናናት ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ የመደራደሪያ አቅሙን ለማጎልበት እንደሆነ ሲጠቀስ ነበር። የትህነግ የሚዲያ አስተባባሪ ሆኖ እንደሚሰራ የሚነገርለት ማርቲን ፕላውት “ደብረጽዮን ነገሩኝ” ሲል እንደዘገበው በቅርቡ የጀቡቲ መነገድ ተቆርጦ እርዳታ በቀጥታ ወደ ትግራይ እንዲደርስ እንደሚደረግ መዘገቡም ይታወሳል።

በዚሁ ሃሳብና እቅድ መሰረት ወደ አፋር የዘለቀው የትህነግ ሰራዊት ወደፊት መጓዝ አልቻለም። በውቅቱ የቀረቡ ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት ትህነግ በፋር ግንባር ክፉኛ ሊባል የሚችል ክስረት አጋጥሞታል። በርካታ ሰራዊቱ ሙት፣ ቁስለኛ፣ እንዲሁም ምርኮኛ ሆነውበታል። በዚሁ ሳቢያ “ለአፋር ወንድሞቻችን ስንል ኦፕሬሽኑን ተተነዋል” ሲል ፊቱን አማራ ክልል ወደያዛቸው ስፋራዎች በማዞር ጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።

በርካታ የአማራ ክልል ሲወረር፣ ሲዘረፍ፣ ህዝብ ሲጨፈጨፍ፣ ንብረትና መሰረተ ልማት ሲወድም የኢትዮጵያውን ጨምሮ የዓለም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች፣ አሜሪካም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት ያሉት ነገር የለም። አፋር ላይ ትሀንግ በር ዘግቶ የርዳታ መኪኖች እንዳይገቡ ሲከለክል የተቃወመ አልነበረም። የመንግስት ሃላፊዎችና በስፍራው የተገኙ ሚዲያዎች እንደሚሉት ዛሬ ሳማንታ ፓዎር ላለፉት ዘጠኝ ወራት ከሆነው በላይ የርዳታ እህል እያለቀ መሆኑንን ያስታወቁት የትህነግ “ወራሪ” ሃይል እየተመታና ይዞት የነበረውን አካባቢ እየለቀቀ፣ እንዲሁም የሰረገው ሃይሉ ተከቦ መውጣት እንዳይችል ሆኖ እየተደመሰሰ በመሆኑ ነው።

“ትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በነበሩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመጀመያ ጊዜ የእርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው ነው” ሲሉ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ያሰሙት ሃላፊዋ “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ አደጋ በተጋለጡበት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ የዩኤስኤይድና ሌሎች ድርጅቶች የእርዳታ ምግብ ማከማቻ መጋዘኖች ባዶ ናቸው በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ” ሲሉ ካስታወቁ በሁዋላ አክለው እጥረቱ የተከሰተው ምግብ ጠፍቶ ሳይሆን “የአየርና የየብስ ማጓጓዣ መስመሮችን፣ የእርዳታ አቅርቦትና የእርዳታ ሠራተኞችን ተግባር የኢትዮጵያ መንግሥት በማደናቀፉ ነው” የሚል ምክስ አቅርበዋል።

“ሴትየዋ ክስ ሲያቀርቡ በትግራይ ክልል ውጊያ የለም። ውጊያ ያለው በተወረረው የአማራ ክልል የሚደረግ የህልውና ትግል ነው” ሲሉ የሚቃወሙ እንደሚሉት የትህነግ ፍጻሜ እየተቃረበ ስለሆነ ትጥቅ፣ ስንቅ፣ ወታደራዊ ድጋፍ ማግኘት እንዲችሉናበሱዳን በኩል ያሰፈሰፈ የሰለጠነ ሃይል ይገባ ዘንድ መንገድ እንዲከፈት ጫና ለመፍጠር ነው። ሌላ ዓላማ የለውም።

“ሲገባ የነበረውና ቀድሞ የተከማቸው ዕህል ለተረጂዎች በአግባቡ ይደርስ ከነበረ ስለምን ስለ ችጋር ይወራል” ሲሉ የሚጠይቁ እንደሚሉት ” ሕዝብ አግቶ በረሃን የሚቆምረውን የወንበዴ ቡድን ለመታደግ ሲባል የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ህልውና ላይ ጫና ለማሳደር መሞከር ችግሩን ያሰፋው ካልሆነ በቀር አያለዝበውም” ሲቀጥልም አሁን የተነሳው ህዝብ እንደሆነ አለመረዳት ልዩ ትርጉም እንዳለውም አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ አርብ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሆን ብሎ እርዳታ እንዳይደርስ እያገደ ነው የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስተሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በሰጡት ምላሽ በክልሉ ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለያዩ ስፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውንና ማንኛውም ወደ ትግራይ ክልል ለመግባት የሚፈልግ አካል በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠውን አሰራር መከተል እንደሚኖበት ተናግረዋል።

መንግስት አስቀድሞ እንዳለው የአየርም ይሁን የየብስ ትራንስፖርት ክፍት ነው። ነገር ግን በረራ ከአዲስ አበባ መቀለ ከፍተሻ በሁዋላ፣ መንገድ እጅግ ቅርብ በሆነው በአፋር ሰመራ በኩል ሲሆን ኬላዎች ላይ ያለውን ብርበራ ማለፍ ግድ ነው።

በትግራይ ህጻናት፣ እናቶች፣ አረጋዊያን መቸገር እነደሌለባቸው፣ እርዳታ ሊደርስላቸው እንደሚገባ በርካቶች ያምናሉ። ይሁንና ትህነግን በገሰጽ ለአሜሪካ ለምን እንደከበዳት ግን ግልጽ አይደለም። ትህነግ በአማራና በአፋር ክልል ወረራ እያሰፋ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመራ፣ ኢህአዴግ ቁጥር ሁለትን እንደሚመሰርት፣ ባህር ዳርና ጎንደርን፣ ደሴና ኮምቦልቻን ተቆጣጥሮ ወደ ደብረብርሃን ለማምራት እንዳይችል የሚከለክለው አንዳች ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ሲገልጽ፣ ተኩስ አቁሙን እንዲያከብርና እርሻ እንዲጀመር፣ የርዳታ እህል እንዲገባ ጫና መፍጠር ብቀርቶ የተነፈሰ አካል አልነበረም። አሁን ሃይሉ እየተመታና ከበባው እየጠነከረ ሲሄድ የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ጩኸት ማሰማታቸው ዜጎችን አሳዝኗል።

Exit mobile version