“ውጊያው አልቋል” ያለው ትህነግ የሰላም ድርድር ጥያቄ አቀረበ፤

ከሶስት ሳምን በፊት ” ጦርነቱ አልቋል፣ ለድርድር መሽቷል። ዛሬ 1991 አይደልም…” ሲሉ ከነበሩት፣ ትህነግን ሆነው የሚሟገቱትና አስቀድሞ መረጃ በማሰራጨት የሚታወቁት የኖርዌይ ተወላጅ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮድቮል ትህነግ ለሰላም ንግግር ሲል ወሮ ከያዝቸው አካባቢዎች መልቀቁን አመለከቱ።

ሮይተርስም የትግራይ ታታቂ ሃይሎች ሲራመዱ የሚያሳይ ምስል ለጥፎ ” የትግራይ ሃይሎች ከአጎራባች የኢትዮጵያ ክልሎች ወጣ” ሲል አፈቀላጤ አቶ ጌታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል።

የትግራይ ወራሪ ሃይል መሪ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ጽፋት ያሉትን ደብዳቤ በማስታወስ ሺትል እንዳሉት ” ኳሷ አሁን በኢትዮጵያ መንግስት እጅ ላይ ናት” ሲቀጥልም የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መሆኑንን አመላክተዋል።

ቀደም ሲል ልክ እንደማርቲን ፕላውት ለምን ማፈግፈግ እንደተፈለገ ብዙም እንዳልገባቸው ሲያስታውቁ የነበሩት እኚሁ ሰው ዛሬ የሰላም ድርድር ጉዳይ በኢትዮጵያ እጅ መሆኑን ሲያስታውቁ በትህነግ በኩል ለሰላም ንግግር ምንም አይነት ጥርጥር እንደሌላቸው በማሳየት ነው። ሼትል የትግራይ መከላከያ ሃይል የሚለውን ስም ያወጡ መሆናቸው ይታወሳል።

ትህነግ በወረራ የያዛቸውን ስፍራዎች ባስቸኳይ ለቆ እንዲወጣና የደረጃእውን ሃይል ትጥቅ እንዲያስፈታ፣ በህግ የሚፈለጉትን እንዲያስረክብ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦለት የሰላም ንግግር ሊደረግ እንደሚችል መንግስት አመልክቶ እንደነበር ይታወሳል።

እኚህ ሰው ከወር በፊት ዛሬ 1991 አይደለም። ለድርድር መሽቷል።ሲሉ የሽግግር መንግስት ምስረታው እንዲታሰብበት፣ ከጠ/ሚ አብይ መውደቅ በሁዋላ ስለሚኖረው ሽግግር ስማቸውን የዘረዘሯቸው አካላት እንዲያስቡ … ዛሬ ደግሞ “እርቅ” እያሉ ነው

ከዛ ቀደም ሲል ትህነግ ቀደም ሁኔታ አስቀምጦ የሰላም ንግግር ሊደረግ እንደሚችል በተደጋጋሚ ማስታወቁ፣ ንግግሩ ዓላማው የሽግግር መመስረት መንግስት እንደሆነ፣ ይህ ካልሆነ ጦርነቱ እየገፋና በመሄዱ አዲስ አበባን እንደሚቆጣጠር ሲያስታውቅ መሰነበቱ አይዘነግም። በመካከሉ ግን ምን ተፈጥሮ እንደሆነ ባይታወቅም አቶ ጊታቸው ረዳ አስፈላጊው ማህበራዊ አገልግሎት ከተከፈተ ለመደራደር ፈቃደና መሆናቸውም አመልክተው ነበር። ሁሉም አልፎ የጥምር ሃይሎች በወረራ የተያዙትን ቦታዎች እያስለቀቁ ወደ መቀለ ለመንደርደር የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በሚያመቻቹበት በዚህ ወቅት የሰላም ንግግር እንዲደረግ ትግነግ በጻፈው ደብዳቤ ቅድመ ሁኔታ እንዳላስቀመጠ ታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።

የአፋር ፓርቲ ሊቀመንበር ” ከትህነግ ጋር ድርድር ብሎ ነገር የለም” ሲሉ አሁንም ለሰላም እየዘመረ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት መሰንዘሩን አመልክተዋል። ሙሉውን ለስር ያንብቡ

” ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነትም፣ ንግግርም፣ ድርድርም አንፈልግም “- አቶ ሙሳ አደም

የአፋር ተቃዋሚ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ክልሉን የሚመራው የአፋር መንግስት፣የአማራ ክልልና በአማራ ስም የተደጀው አብን በድርድር ጉዳይ እጅግ የጸና አቋማቸውን በአመራሮቻቸው አማካይነት በተደጋጋሚ ይፋ አድርገዋል። ከአሁን በሁዋላ ትህነግ ስጋት እንዳይሆን ማድረግና በዚህ ደረጃ ውድመትና ግፍ የፈጸሙትን ወደ ፍትህ የማምጣቱ፣ ትግራይ ከኢትዮጵያ ጋር የምትቀጥል ከሆነ ህግና ደንብ ተከብሮ ሊሆን እንደሚገባው በተደጋጋሚ እያስታወቁ በመሆናቸው የትህነግ የሰላም ንግግር እንዴት እንደሚስተናገድ እስካሁን ፍንጭ የለም።

ሰሞኑንን የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በሁለቱም ወገን የተፈጸመውን ወንጀል የሚያጣራ ኮሞሽን ማቋቋሙን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከትህነግ ወገን የተሰማው የሰላም ንግግር ጥያቄና ትሮንቮል ” ካሁን በሁዋላ ጉዳዩ የተመድ የጸጥታው ምክርቤት” ይሆናል ማለታቸው የነገሩን ኢትዮጵያ ውሳኔውን እንደማትቀበል ስትገልጽ ይፋ ካደረገችው ምክንያት ጋር የሚጣታም ሆኖ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ጥምር ሃይሎች ሁለተኛ የዘመቻ ዓቅዳቸው ምን እንደሆነ እስካሁን ይፋ አልተነገረም። አንደኛው ዘመቻ በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር አቡ ከማስታወቃቸው ወጪ ስለ ሁለተኛው ዘመቻ ያሉት ነገር የለም። ይሁን እንጂ ዘመቻው ተላት የተባለውን ሃይል የሚያደቅ እንደሆነ አመልክተው ነበር።

አዲስ አበባ መከበቧንና የመንግስት መቆየት ያለቀለት ጉዳይ እንደሆነ ሲዘግቡ የነበሩ ሚዲያዎችና ትህነግ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ መንግስትና ሕዝብን ሲያካልቡ የነበሩት እነ አሜሪካ፤ የትህነግ ዘመቻ በህዝብ ክተትና ትግል፣ በመከላከያና ድፍን የአገሪቱ የክልልና የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች፣ ፋኖና ሚሊሻዎች ጥምረት ሲቀለበስ ” አሜሪካ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ አሳስቤያለሁ። ሰዎቹ 1983 ላይ የተቸከሉ ናቸው። አይሰሙም” የሚል መግለጫ በፌልትስ ማን ማካይነት ማሰራጨታቸው የሚታወስ ነው።

አቶ ጊታቸው ረዳ በትግርኛ ” አሜሪካ ወደ አዲስ አበባ እንድንገባ አግዛናለች” ማለታቸው ያስቆጣቸው የአሜሪካ ባለስልጣናት ” ለአፍታም ቢሆን ትህነግን ረድተን አናውቅም” ሲሉ ለዚሁ ብተግባር ባዘጋጁት የአሜሪካ ሬዲዮ አማካይነት ማስተባበያ መስጠታቸውም አይዘነጋም። የኢትዮጵያን መሪ ዶክተር አብይን ከአገር እንዲኮበልሉ ሲያግባቡ የነበሩት አሜሪአክኖች የዲፕሎማሲ ስራው ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል ተሰው የጄኖሳይዱን ክስ እንደሚያነሱም ሲናገሩ ነበር። በአሜሪካ ባለስልታናትና ተላላኪዎች አማካይነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አገር እንዲከዱ ሲጫኑ የነበሩ ሁሉ ዛሬ መንገዳቸውን እንደቀየሩ ምልክቶችም እየታዩ ነው። የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ አብይ አህመድ እንዳሉት ወረራው ተቀልብሶ ነገሮች ወደ መቸረሻቸው እያመሩ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ይህ እስከታተመ ድረስ ስለ ሰላም ንግግሩ ኢትዮጵያ የሰተችው ምላሽ አልታወቀም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ከማን ጋር? ድርድር መከላከያን ካረደ ሃይል ጋር?” ማለታቸው አይዘነጋም። የወድሞ ሌተናል ጂነራልና የህዝብ ማዕበል ውጊያን በመንደፍ ” ምጡቅ” የተባሉት ጻድቃንም ” ጦርነቱ አልቋል፤ ከማን ጋር ነው ድርድሩ” ሲሉ ነበር። ዶክተር ደብረጽዮን በበኩላቸው ” አልቋል እጃችሁን ለትግራይ ሃይሎች ስጡ” የሚል ጥሪ ያስተላልፉ ነበር። ዛሬ የተገላቢጦሽ ሆኗል የሚሉት በዝተዋል። የቀረው መርዶ በየቤቱ የሚተከለው ድንኳን ነው። ሁሉም ቤት ሃዘን ግብቷል። ሰላም አማራጭ የለውም። በርካቶች እንደሚሉት ፍትህ ያለበት ሰላም ግድ ነው።


Leave a Reply