Site icon ETHIO12.COM

በጁባ የተበጣጠሰው የጁንታው የሽብር መረብ

ኢትዮጵያ ባለብዙ ጀግኖች ሃገር ናት ኢትዮጵያ ሃገራችን ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተግባር ከ1951 በኮርያ የጀመረው የሰላም አምባሳደርነት  በሩዋንዳ በኮንጎ በቡርንዲ በላይቤርያ በዳርፉር በአብዬ በሱማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሰላም ላጡ ህዝብ ሰላምን አስፍኖ ለተራበው አጉርሶ ለተጠማው አጠጥቶ ዛሬም በአለም አደባባይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ለሰላም ተመራጭ የሆነ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነው።

ታድያ ዛሬም በቡዙ ሺዎች የሚቆጠር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአለም ሰላም ማስከበር ላይ ተሰማርቶ በጀግንነትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

ይህንን በከፍታ ማማ ላይ ያለ ሠራዊትን ሊነቀንቁት አስበው በደቡብ ሱዳን ጁባ የሚገኝውን የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ላይ ደም ለማፋሰስ የሽብር ተግባር ለመፈፀምና የኢትዮጵያ ሃገራችንን ገፅታ ለማበላሸት ልባቸው በተንኮል ያበጠ ቀልባቸው በራቃቸው  በብሄር ፓለቲካ አይናቸው የታወረ ጥቂት የጁንታው ተላላኪዎች ያሰቡት ሳይሳካ በጥበብ በተመራ የአመራር ብስለት ዳግም ህልማቸው ቅዠት ሆኖባቸው ወደ ደቡብ ሱዳን መጠለያ ካምፕ ፔስታላቸውን አንጠልጥለው ተሸኝተዋል።

ይህንን የሽብር ቡድን በህዕቡ ሲመሩና ሲያስተባብሩ የነበሩ

1- ኮ/ል ገብረ መድህን

2- ኮ/ል ፀጋዬ አብርሃ

3- ኮ/ል ካህሳይ መረሳ

4- ሌ /ኮ ይርጋ

5- ሌ/ኮ ፍተሃነገስት አብርሃ

6- ሌ/ኮ ገብረሚካኤል ለማ

7- ሌ/ኮ ተስፋዬ አሰፋ

8- ሌ/ኮ ደስታ ሃይሉ

9- ሻለቃ ተስፋዬ ዘነበ

10- ሻምበል አደራ ከብዙ በጥቂቱ እነዚህ የትግራይ ተወላጆች የጁንታው ተላላኪዎች ያሰቡት የሽብር ተግባር አልተሳካም ።

ካሰቧቸው የሽብር ተግባራት የሻለቃው ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል መለስ ይግዛው ላይ ጥቃት መሰንዘር የኢትዮጵያን የሆኑትን ድንቅ እና የሰላም አምባሳደር ልጆችዋን እርስ በርስ እንዲጠራጠርና አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ ማድረግ የሰራዊቱን ምግብ በመበከል ሰራዊቱ እንዲያልቅ ማድረግ ሰራዊቱ በሚያደርጋችው የግዳጅ ስምሪቶች እንከን እንዲገጥመውና ብቃት እንደሌለው አሳንሶ ለማሳየት መሞከር  ይህንን ሁሉ የተንኮል ድራቸውን ታድያ አስቀድሞ ያወቀው የሻለቃው አመራርና አባላት የሃገራችን ክብርና ዝና በእናት ጡት ነካሾች ጥቂት የጁንታው የሽብር ማስፈፀምያ የትግራይ ተወላጆች እንዳይፈፅሙት ቀንና ለሊት በመከታተል ምንም ያሰቡት ሳይሳካላቸው ትጥቅና ወታደራዊ ማቴሪያል ቁጭ አድርገው እኛው ስንጠብቀው ወደነበረው የስደተኛ ካምፕ ካርቶን ፔስታል ማዳበርያ አንጠልጥለው ገብተዋል።

እኛ በትግራይ ምድር እንወለድ እንጅ ውስጣችን ያለው ኢትዮጵያዊነት ነው ያሉ 20 የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የትግራይ ተወላጆች ወደሚወድዋት ሃገራቸው ለመጎዝ በናፍቆት እየተጠባበቁ ነው። (ፋሲል የኔዓለም)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Exit mobile version