Site icon ETHIO12.COM

አማራ ክልል ተበትኖ መውጪያ ባጣው የትህነግ ጭፍራ ላይ ሕዝብ በያለበት እርምጃ እንዲወስድበት ጥሪ ተላለፈ

በክምር ድንጋይ አካባቢ ሲዋጋ የነበረው ጠላት እየተደመሰሰና ከፊሉ እየሸሸ መሆኑን የሰሜን ምዕራብ እዝ የአንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ተናግረዋል። በአሸባሪው ትህነግ ላይ በተወሰደው እርምጃ ተመትቶ የተበታተነውን ጠላት ሕዝቡ ሊለቅመው እንደሚገባም አዛዡ አሳስበዋል።

ጀነራሉ አሁን ላይ ቡድኑ የመዋጋት ቁመና የሌለውና የተከበበ መሆኑን ገልጸዋል። “አሸባሪው ትህነግን ዛሬ ካልደመሰስነው ነገ ሀገር ማፍረሱ ጥርጥር የለውም፤ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ሳንደመስሰው አናርፍም” ነው ያሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ። የተበታተነው ቡድን ነገ ድጋሜ ሊሰባሰብ ስለሚችል ሕዝቡ አንድ ሆኖ ጠላትን በማነቅ መደምሰስ ያለበት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል። አሸባሪው ትህነግ በሚያሰተላልፈው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ መረበሽ እንደማይገባም ገልጸዋል።

“በርካታ የጠላት ኀይል ረግፏል” ያሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ ጠላት ይዞት የገባው ከባድ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎቹ ወድመዋል ብለዋል። ሕዝቡ በግንባር በመዝመት፣ ስንቅ በማቀበልና መረጃ በመስጠት ለሠራዊቱ እያደረገ ባለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

አሸባሪው ቡድን ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ የሕዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። “ሕዝቡ ድሉ የእሱ ድል መሆኑን አውቋል” ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ሌሊት ሳይቀር በስኬት ያታገለልን ሕዝቡ ነው ብለዋል።

በጋይንት ግንባር የሜካናይዝድ ክፍሎች አስተባባሪ እንዲሁም የአየር ኀይልና የምድር ኀይል እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸው የጠላት ዓላማ ኢትዮጵያን መበታተን መሆኑን ከምርኮኞች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ጠላት በአየር እና በምድር ኀይል ከፍተኛ ውድመት እንየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል። ሕዝቡ በውጊያው ከመሳተፍ በተጨማሪ እስከ ምሽግ ድረስ ስንቅ በማቅረብና ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር ደጀንነቱን አስመስክሯል ነው ያሉት። ሌሊት ላይ በጋሳይ የመጣው ጠላትም ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ኮሎኔል ዘለቀ አስረድተዋል። አሁንም የጠላትን እግር በመከተል የመደምሰስ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም ኮሎኔሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

Exit mobile version