ETHIO12.COM

ከአፋር በርሃሌ አሳዛኝ ዘገባዎች እየወጡ ነው

ነብሰ ጡሮች፣ መጫቶች፣ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞች፣ ህጻናት ከለሊት ጀምሮ አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው። ይህ እስከታተመ ደረስ ሃምሳ ሺህ የሚሆኑ ነጹሃን ዜጎች ከደሃ ጎጇቸው በማያውቁት ምክንያት ጥይት ወረዶባቸው ተፈናቅለዋል። ይህ እስከተዘገበ ድረስ ደሳሳ መጠለያቸውን ጥለው እየሸሹ ነው። አሸባሪው ሃይል በበርሃሌ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለምን ጥቃት እንደፈጸመ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

ደብረታቦርን ለመቆጣጠር በርካታ ሃይልና ከባድ መሳሪያ አሰልፎ የነበረው ትህነግ ያሰበው ባለመሳካቱና ሃይሉ በደመሰሱ፣ የተረፈውም ምርኮኛ ግማሹም መውጪያ አጥቶ ሲበተን በንዴት ከተማዋን በከባድ መሳሪያ መደብደቡን፣ በዚህም ከአንድ ቤተሰብ አምስት ሰዎችን መግደሉና አባትና አንዲት የጎረቤት ልጅ መቁሰላቸውን ያስታወቁት የዞኑ ሃላፊ ” አሸባሪው ያለው እድል መደምሰስ ወይም እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ብለው ነበር።

የሰሜን ምዕራብ እዝ የአንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በአሸባሪው ትህነግ ላይ በተወሰደው እርምጃ ተመትቶ የተበታተነውን ጠላት ሕዝቡ ሊለቅመው እንደሚገባ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

ቀደም ሲል ወደ ሰሜንና ምዕራብ ጎንደር ከመስፋፋቱ በፊት በአፋር ግንባር ወረራ ሲፈጽም በቀናት ውስጥ የጅቡቲን መስመር ለመቆጣጠር እንደሚችል አስታውቆ የነበረው ትህነግ በዛው ግንባር ከፉኛ የሰው ሃይሉ ስለተጎዳ፣ በተመሳሳይ ንዴት በጋሊኮማ አንድ መቶ ህጻናትን ጨምሮ 240 በላይ ሰዎችን መጨፍጨፉ፣ ለ30 ሺህ ሰዎች የተዘጋጀ እህል መጋዘን ውስጥ ማንደዱ በአካባቢው አስተዳደር፣ በቆሰሉ ምስክሮችና በዓለም አቀፍ አንዳንድ ሚዲያዎ መገለጹ የሚታወስ ነው።

“ለወንድም የአፋር ሕዝብ ስንል ኦፕሬሽኑንን አቁመነዋል” በሚል ፊታቸውን ወደ ሰማኤና ደቡብ ጎንደር ያዞሩት የትህነግ አመራሮች፣ ከሳምንታት በሁዋላ በመልሶ ማጥቃት ክፉኛ ስለተጎዱ ሳይታሰብ በትናትናው እለት ለሊት በርሃሌን ወሮ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ታውቋል።

በሰሜን አፋር ያደረገውን ትርጉም አልባ የትህነግ ወረራ እንደሚቃወሙ የአፋር አክቲቪስቶች እየገለጹ ነው።

ዶ/ር ኮንቴ ” እውነቱን እናውቀዋለን፣ ትህነግ ጨፍጭፎናል” በአፋር የሶስት ቀን ሃዘን ታወጀ፤ ትህነግ ተጨማሪ 8 የቤተሰብ አባላት ገደለ

“ቅጥፈታችሁ እየወየበና እየደበዘዘ፣ እውነት ወደ አደባባይ እየመጣች ነው። እውነቱን እናውቀዋለን። ተጠያቂዎቹ እናንተ ናቹህ”

ከስፍራው እንደሚሰማው በለሊት በከባድ መሳሪያ ተደግፎ በርሃሌን የወረረው የትህነግ ጭፍራ ጭፍርጨፋ አካሂዷል። በአማራ ክልል ከተማ በማውደም፣ ሰላማዊ ዜጎችን በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ከባድ መሳሪያ እየጨረሰና ያገኘውን እየዘረፈ እንደሆነ የሚነገርለት ትህነግ በርሃሌን ከቦ በከባድ መሳሪያ ሲደበድብ ያደረበት፣ ከዛም የወረረበት ምክንያት ለበርካቶች አስገራሚና አሳዛኝ ሆኗል።

በአማራ ክልልም ሆነ በአፋር በመቶ ሽህ የሚቆተሩ ሲፈናቀሉና በመቶዎች ሲጨፈጨፉ፣ ከተማ ሙሉ በሙሉ ሲወድም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መበት ኮሚሽነር ያለው ነገር የለም። በማይካድራ ጭፍጨፋ ላይ ዳተኛነትን የመረጠውና መንግስት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት የሚመድብለት ተቋም ሚናው አነጋጋሪ ሲሆን፣ ከንግሊዝ የተመለሱት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል አቋማቸው ጥያቄ ውስጥ መግባቱን በማህበራዊ ገጾች እየተዘገበ ነው። አማራ ክልልም ” የት ገቡ” ሲል ጠይቋል።

ሳይታሰብ የትህነግ ጭፍራ ከለሌት ጀመሮ ባካሄደው ጥቃት እስካሁን 50 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ተፈናቅሏል። ነብሰ ጥሮችን ጨምሮ ህጻናትና መቸታቶ፣ እንዲሁም አረጋዊያን ለስቃይ ተዳርገዋል። ከአካባቢው እምኞች እንደሚናገሩት ከሆነ የተፈጸመው ጥቃት ዘግናኝ ነው። የአፋር ልዩ ሃይልና መከላከያ ወራሪውን ሃይል ልክ በጭፍራ እንዳደረጉት ለመመከት እየሰሩ መሆን ተሰምቷል።

የትግራይን ህዝብ ዙሪያውን ጠላት እያፈሩለት እንደሆነ የሚነገርላቸው የትህነግ አመራሮች አፋርን ወረው ሕዝብ የሚጨፈጭፉበት ምክንያት ለሚደግፏቸውም ግልጽ አይደለም። እጅግ ደጋፊያቸው እንደሆነ የሚነገርለት በስዊዲን የሚኖር የትግራይ ተወላጅ ” ይህ ሊገባኝ አልቻለም። ዝርፊያና ሰላማዊ ሰዎችን መግደል ተቀባይነት የለውም። አጣርቼ አቋሜን አሳውቃለሁ” ሲል ለዝግጅት ክፍላችን አመልክቷል።

አንዳንዶች እንደሚሉት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንዲሆንም በወልደያ ግንባር ጫናው ስለበዛና ከበባው ስለጠነከረ ሃይል ለመበተን የተደረገ ወረራ ነው። ይህ እስከተጠናቀረ ድርሰ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች፣ አገራትና ሚዲያዎች ያሉት ነገር የለም።

በሌላ በኩል ያለው ግምት ግን ረሃቡን ተንተርሶ አሁን የተጀመረው አዲስ ጫና በሲዳን በኩል ድንበር ለማስከፈት በመሆኑ የአፋርን ዙሪያ የጦርነት ቀጠና ማድረጉ ሌላው ስትራቴጂ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። ከ12 ግዜ በላይ የሁመራን ዝግ በር ለማስከፈት ሞክሮ እንዳልተሳካለት የተነገረለት ትህነግ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ከሱዳን አስርጎ ቢያስገባም 109 ሲማረኩ የተቀሩት መደምሰሳቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ሳማንታ ፓዎር በፋር አዲሱ ወረራ ከመካሄዱ በፊት ምግብ ማለቁን ጠቅሰው ሁሉም ኮሪደሮች፣ የአየር ትራንስፖርት ያለገደብ ሊከፈት እንደሚገባ ገልጸው መግለጫ አሰራጭተው ነበር። አፋር ለትግራይ ጅቡቲ ለትግራይ 300 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የሚገኝ ቅርብ አማራጭ መሆኑንን በመግለጽ መንግስት በሱዳን በኩል ኮሪዶር እንደማይከፍት፣ የአየር ትራንስፖርትም ከሆነ ፍተሻ እየተካሄደበት መንቀሳቀስ እንደሚችል ማስታወቁ ይታወሳል። ሳምንታ በመግለጫቸው የጠየቁት ፍተሻ እንዲቀር ስለመሆኑ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። እንደሚሰማው ከሆነ ግን ትህነግ ጥይት እያለቀበት ነው። የሴትየዋም ጥያቄ ” ጥይትና መሳሪያ አልቋል” የማለት ያህል ነው።

በበርሃሌ የዓለም የስደተኞች ተቋም ጣቢያና ሰራተኞች ያሉበት፣ ዩኒሴፍም የሚንቀሳቀስበት መሆኑ ይታወቃል።

Exit mobile version