Site icon ETHIO12.COM

« … የትህነግ ጀሌዎች በአማራ መሬት ላይ ሲቀበሩ ዋሉ”

እምቢ ማለት ነው ነፃነትን የሚያመጣው፣ እምቢ ማለት ነው ፀሐይ የሚያወጣው፣ እምቢ ማለት ነው ክብር የሚሰጠው፣ እምቢ ማለት ነው ጠላትን የሚቀጣው። እምቢ ለነፃነት፣ እምቢ ለአንድነት፣ እምቢ ለኢትዮጵያዊነት፣ እምቢ ለክብር፣ እምቢ ለፍቅር፣ እምቢ ለሀገር ያሉት ናቸው ኮርተው ያኮሩን። ተከብረው ያስከበሩን ።

እምቢ ብለው ነው ዓድዋን ያመጡ፣ የአፍሪካን ጀንበር እንዳትጠልቅ አድርገው ያወጡ፣ እምቢ ብለው ነው ለዳግም ወረራ የገባውን የጣልያን ወራሪ ከሀገር ያስወጡ፣ እምቢ ብለው ነው በየዘመናቱ የመጣውን ጠላት የቀጡ። በየዘመናቱ ኢትዮጵያን ለመውረር፣ ኢትዮጵያውያንን ለማስገበር የመጣው ጠላት ሁሉ አፈር ልሷል፣ የኢትዮጵያዊያንን ክንድ ቀምሷል።

ለውጭ ጠላት ያደረ የውስጥ ባንዳም በአንድነት ክንድ እየተመታ ኢትዮጵያ ኮርታ ኖራለች። ዛሬም ኮርታ እየኖረች ነው። ነገም ኮርታ ትኖራለች። ምክንያቱም እምዬ ጀግና ልጆችን መውለድ ታውቃለችና።

ከሀጥያት ላይ ትእቢት ሲጨመር ሞት ይፈጥናል። መዋረድም ይጨምራል። ሀጥያት መሥራት ብቻውን በቂ ነበር፣ ትእቢት ሲጨመርበት የበለጠ ከፍ ይላል። የአሁኑ የኢትዮጵያ የውስጥ ጠላት ሀጥያተኛም፣ ትእቢተኛም ነው። በኢትዮጵያውያን ላይ እልፍ በደሎችን ፈፅሟል፣ የኢትዮጵያን ሀብት ዘርፏል፣ የአንድነቷን ገመድ ለመበጠስ ተውተርትሯል፣ ዳሩ የአንድነቷ ገመድ በፅኑ የተገመደ፣ በቀላሉ የማይበጠስ ነው።

ኢትዮጵያዊነት በከፋ ዘመን መፅናት፣ የበዛውን ጠላት ማጥፋት፣ ነጥሮ መውጣት፣ ክፉውን ዘመን አሳልፎ መልካም ዘመን ማምጣት ነው። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ያለ ጠላት ያለፉበት ዘመን የላቸውም። ጠላት በተነሳ ቁጥር በጋራ እየተነሱ፣ በአንድነት ክንድ እየደቆሱ፣ ከወሰን መለስ እየመለሱ፣ ወሰን የተሻገረውንም ባለበት እየደመሰሱ ነው የኖሩት።

ዛሬም እንደቀደመው ዘመን የውስጥ ጠላት ተነስቶባቸዋል። የውጭ ጠላትም አሰፍስፎባቸዋል። ዳሩ የጋራ ጠላታቸውን በጋራ ለማጥፋት በጋራ ተነስተዋል። እያጠፉትም ነው። የተነሳባቸው ጠላት የተፈጠረባትን ሀገር እየጠላ የኖረ፣ እየጠላት ያስተዳደረ ከሀዲ ነው። የኖረበትን ማሕፀን የረገጠ፣ ያጠባውን ጡትና ያጎረሰውን እጅ የነከሰ ነው።

የኢትዮጵያውያን የጋራ ጠላት ትህነግ ኢትዮጵያውያንን ሊቀብርበት የቆፈረው ጉድጓድ ራሱ እየተቀበረበት ነው። “ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ” እንዳሉ ትህነግ ጭሮ ጭሮ መታረጃውን አውጥቷል። ቆፍሮ ባወጣው እየታረደ ነው፣ ጨርሶም ይታረዳል፣ ለዓመታት ለጦርነት ተዘጋጅቶ በሳምንታት ተመትቶ ዋሻ ውስጥ የቆዬው ትህነግ በተደበቀበት ዋሻ አጠገብ የሚኖሩ የትግራይ አርሶ አደሮች እንዲያርሱ፣ አርሰው እንዲያፍሱ፣ ነጋዴው እንዲነግድ ሌላውም በሰላም እንዲኖር እፎይታ ቢሰጠው ለሌላ ጦርነት ተነሳ። ዳግም በለኮሰው ጦርነትም ከምስረታው ጀምሮ የሚጠላውን የአማራ ሕዝብን ወርሯል። በአማራ ላይም በደል ፈፅሟል፣ እየፈፀመም ነው።

ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ የአፋርን ሕዝብ ወርሯል። በወረራውም ንፁሐንን ገድሏል። አፈናቅሏል፣ ሀብትና ንብረትን አውድሟል። ዳሩ በሁለቱም ክልሎች የገባው ወራሪውና አሸባሪው ኃይል መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶበታል። የተነሳበት አካባቢ እንደ ሰማይ ርቆታል፣ ሞት ቀርቦታል፣ ሰማይ ተደፍቶበታል።

በአማራ ክልል የገባውን ወራሪ ቡድን የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ከሌሎች ክልሎች የመጡ የልዩ ኃይል አባላት፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና ሕዝቡ በገባበት እያነቀ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ እየሸኘው ነው።
“በተወለዱበት ባደጉበት ቀዬ አፈር የለም አሉ፣
የትህነግ ጀሌዎች በአማራ መሬት ላይ ሲቀበሩ ዋሉ” ወደውም ሆነ ተገደው ከትግራይ ተነስተው ወደ አማራ መሬት የገቡት ሁሉ ጥይት እየበላቸው፣ ባሩድ እየቆላቸው መውጫ መግቢያ ጠፍቶባቸው ወደማይቀርላቸው ሞት እየተሸኙ ነው። ያደረሱት እና እያደረሱት ያለው በደል ሕዝቡን አስቆጥቶታልና። ቀፎው የተነካ ንብ አድርጎታል። እንደ አንበሳ አግስቶ፣ እንደ ነብር አስቆጥቶ ቀስቅሶታል።

በደል የመረረው ሕዝብ ሲነሳ መቆሜያው ከባድ ነው።
“ክተት በነጋሪት በጎራዴው ስለት አንገቱን ቀንጥሰው
የማንን እንጀራ ማነው የሚቆርሰው” እንዳለ ገጣሚው የአንተን እንጀራ ማንም እንዲበላው አትፍቀድ፣ የሰው እንጀራ አትንካ የራስህንም አታስነካ፣ በፍቅር ለመጣ ግን በኢትዮጵያዊነት ባሕልህ ያለህን አካፍለህ አብለው፣ አልብሰው አጉርሰው፣ በቂም በቀል መጥቶ፣ ሀብትህን ሊወርስ፣ ቀዬህን ሊያረክስ ሲከጅል ግን ክንድህን አሳዬው። ለማንነት እና ለክብር ሸብረክ እንደማትል አረጋግጥለት።

“ባሕርና አፈሩን ለባንዳ የሚሸጥ ለሰላቱ ሚሰጥ ወንድነቱን ሰልቦ ንገሯት ለእናቱ ይበላዋል በሏት ይበለዋል ጅቦ” ሀገር ለመሸጥ፣ ትውልድ ለማዋረድ፣ ንብረት ለመዝረፍ የሚመጣው ሁሉ ተበልቶ ይቀራል። ረጅም ታሪክ የተሰነደው፣ ሀገር ፀንቶ የቆመው፣ ትውልድ የኮራው፣ ወገን ያልተዋረደው በአንድነት ነው፡፡ ዛሬም አንድነትን በማጠናከር የቀደመውን ታሪክ ማስቀጠል ግድ ይላል። ታሪክ የተሠራለት ትውልድ ታሪክ ሠርቶ ማሳዬትና ለቀጣይ ትውልድ ታሪክ ማስቀመጥ አለበት።

“ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፣ የጥበብን ትምህርት ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል ብልሃትን ለአላዋቂዎች ይሰጥ ዘንድ ለጐበዛዝትም እውቀትንና ጥንቃቄን፣ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል። ምሳሌንና ትርጓሜን የጠቢባን ቃልና የተሸሸገውን ነገር ለማስተዋል። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና። ልጄ ሆይ ኃጢዓተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል። ደምን ለማፍሰስ ከእኛ ጋር ና እናድባ፣ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት ቢሉ በሕይወታቸው ሳሉ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፣ በሙሉም ወደ ጕድጓድ እንደሚወድቁ ይሁኑ፣ መልካሙን ሀብት ሁሉ እናገኛለን፣ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፤ ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፤ ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ፣ ልጄ ሆይ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፣ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፣ እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፣ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና። መርበብ በወፎች ዓይን ፊት በከንቱ ትተከላለችና። እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፣ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ። እንዲሁ ይህ መንገድ ትርፍን ለማግኘት የሚሳሳ ሁሉ የባለቤቱን ነፍስ ይነጥቃል” እንዳለ መፅሐፍ የአማራን ሕዝብ እናጥፈው፣ ንብረቱንም እንዝረፍ ሲሉህ የሰማህ የትህነግ አጋዥ ሁሉ የአንተንም የወዳጆችህንም ነብስ ታስነጥቃለህ። በአማራ ሀብት የሚሞላ ቤት፣ በአማራ ገንዘብ የሚገኝ በረከት አታገኝም። ሞትህም፣ ስቃይህም፣ ገድለህ እከብርበታለሁ ባልከው የአማራ ምድር ላይ ይሆናል።

አሁን አማራው ጠላቱን በጥርሱ አስገብቷል፣ እያደቀቀም ነው። ጠላትን ሙሉ በሙሉ ለመቅበር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ መታገል ማታገል፣ መረጃ ማቀበል፣ ተላላኪን መቆጣጠር ግዴታ ነው።

በታርቆ ክንዴ – ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ)

Exit mobile version