Site icon ETHIO12.COM

የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ነዋሪዎችን ምንነቱ ያልታወቀ መርፌ ሲወጋ ማየቱን የዓይን እማኝ ገለጸ

በሃብሩ ወረዳ ቀበሌ 020 የሚኖረው ወጣት መሐመድ አንሷር እንዳለው የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በአካባቢው ሰርጎ ከገባ በኋላ የተለያዩ የግልና የሕዝብ ንብረቶችን ዘርፏል።

በየደረሱባቸው አካባቢዎች ሁሉ ዘርፎ የሚፈልገውን ያክል ከጫነ በኋላ ሌላውን በማቃጠል ሲያወድም ተመለክተናል ብሏል።

ከዚህ ባለፈም “የኮሮናቫይረስ መከላከያ ነው” በሚል አሸባሪው ቡድን የተለያዩ ሰዎችን መርፌ ሲወጋ ተመልክቻለሁ ብሏል መሐመድ።

አሸባሪ ቡድኑ ሰዎችን የሚወጋው መርፌ እስካሁን ምን እንደሆነና ለምን ዓላማ እንደሆነ ባይታወቅም “መርፌ የተወጋ እርዳታ ያገኛል” በሚል በርካታ ሰዎችን ወግቷል ነው ያለው።

የአሸባሪው ሕወሓት ዘራፊዎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ቤት ሲያቃጥሉ ንጹሐንን ሲገድሉ ማየቱንም ተናግሯል።

የአሸባሪው ቡድን ዘራፊዎች ለሰው ልጅ ምንም አይነት ርህራሄ የሌላቸው ጨካኞች መሆናቸውን በሚፈፅሟቸው ግዲያዎች ተመልክተናል ብሏል መሐመድ።

በተለያዩ አካባቢዎች የአርሶ አደሮችን ቤት በማቃጠልም በጭካኔ ንብረቶችን ሲያወድሙ ተመልክቻለሁ ሲል እማኝነቱን ገልጿል።

የአርሶ አደሮችን የቤት እንስሳቶች እየዘረፉ በማሸሽና ከባድ በደል በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ መግለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version