Site icon ETHIO12.COM

“እብድ ውሻን ማባረር ከእብድ ውሻ ስጋት ነጻ አያደርገም” የአማራ ክልል

“ትህነግ የሚባለው አሸባሪ፤ እብድ ውሻ ” ይላላል የአማራ ክልል መልዕክት፣ በክፋት ተጸንሶ፣ በክፋት ተወልዶ፣ በክፋት እድጎ፣ ከነክፋቱ ለመሞት ግምሽ ሰውነቱ ወደ መቃብር እየወረደ አንደሆነ ያትታል። ይህ ” እብድ ውሻ” ሲል ይቀጥላል ” ይህ እብድ ውሻ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ምድር ካልተወገደ ዕረፍት አይኖርም” ሲል ከያዘው ቦታ በማስለቀቅ ብቻ መዘናጋት የሚባል ነገር እንደማይኖር ያሳታውቃል።

በወረረው ስፋራ የተደቆሰ እንደሆነ ያስታወቀው የክልሉ መልዕክት ፣ ትህነግ ላም ከነጥጃዋ በመግደል የክፋት ሁሉ አስፈጻሚ የሰይጣን ደቀ መዝሙር መሆኑንን ያመልክታል። አያይዞም ይህ የሽንት ጨርቅ ሳይቀር እየሰረቀ ያለው ቡድን (ከስካሽ ውሻ) “… ከምድረ ኢትዮጵያ ተጠርጎ እስኪወገድ ድረስ ክፋቱንና ክፉዎችን በመቅበር ህልውናና ሉዐላዊነታችንን የማስከበር ተጋድሏችን እንደጎመራ ይቀጥላል” ብሏል

ወረራ ፈፅሞባቸው በነበሩ ከተሞች ውስጥ በህጻናት ሴቶች ላይ ጭምር የፈጸማቸው የአስገድዶ መድፈር ነውረኛ ድርጊቶች፤ ከመንግስት ተቋማት እስከ ግለሰቦች ዱቄት፣ ሊጥ እና የአራስ ሽንት ጨርቅ ድረስ የወረደው ዝርፊያው የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ማንነቱን ብቻ ነው….

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሰጡት መረጃ ሙሉ ሃሳብ እንደሚከተለው ይነበባል።

“ክፋት የመሰንበት እድል ካገኘ የውድመት ቁልል ይፈጥራል፡፡ ይህን እውነታም የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ሰሞነኛ የጥፋት ዘመቻ ይመሰክራል፡፡

በኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ታሪክ ውስጥ ትህነግን የመሠለ በክፉዎች ህሊና ለክፋት ሥራ ተጸንሶ፤ በክፉ ተግባራት ላይ ተወልዶ ያደገ እንዲሁም አድጎ ያረጀ የእኩይ ማኅበርተኞች ተፈጥሮ አያውቅም፡፡

ይህ የክፋት አምባሳደር ከጥፋት እና ከክፋት ሥራዎች ውጭ ህልውና የለውም፡፡ በመሆኑም አሁን በስተእርጅና ዘመኑ ግማሽ ጎኑ በመቃብር ጉድጓድ ውስጥ በወደቀበት ሰዓት እንኳን በየደረሰበት ቦታ ሁሉ ከክፋት እና ከጥፋት ድርጊቶች በስተቀር ለማሰብም ሆነ አሻራውን ለማኖር ተስኖት ከነ ክፋት ስራዎቹ በከፈን እየተጠቀለለ ይገኛል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በወረራ ሰርጎ በገባባቸው የአማራም ሆነ የአፋር ክልል መሬቶች ውስጥ የፈጸማቸው ግድያዎች እና የንብረት ውድመቶች የንጹኃንን ደም በማፍሰስ ከሚያገኘው የእርኩስ መናፍስታዊ እርካታ በስተቀር ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ትርፍ የላቸውም፡፡

በድህነት ማነቆ ውስጥ ለ27 ዓመታት ሲያማቅቃቸው የነበሩ የደሃ ደሃ አርሶ አደሮችን ጎጆ በማቃጠል፤ ላሚቷን ከነጥጃዋ ከታሰረችበት በረት ውስጥ በአውቶማቲክ የጦር መሣሪያ ተኩሶ መግደል የአሸባሪው ትህነግ ተልዕኮ ከጥልቁ የክፋት ውቅያኖስ የተቀዳ መሆኑን ከማረጋገጥ በስተቀር ቅንጣት ታክል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም የጦር ሥልት አዋቂነትን አያሳይም፡፡

ትህነግ በየደረሰበት ቦታ ያገኘውን ሁሉ በመልከፍ ለመቧጨር እና ለመንከስ መቅበዝበዙ ከእብድ ውሻ የተለየ እውቀትም ሆነ ጉልበት የሌለው መሆኑን ከማስረዳት በስተቀር በአጥፊ ተቅበዝባዥነቱ ያሳካው ምንም አይነት ግብ የለም፡፡

ወረራ ፈፅሞባቸው በነበሩ ከተሞች ውስጥ በህጻናት ሴቶች ላይ ጭምር የፈጸማቸው የአስገድዶ መድፈር ነውረኛ ድርጊቶች፤ ከመንግስት ተቋማት እስከ ግለሰቦች ዱቄት፣ ሊጥ እና የአራስ ሽንት ጨርቅ ድረስ የወረደው ዝርፊያው የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ማንነቱን ብቻ ነው፡፡

ይህ ከውልደቱ እስከ እለተ ሞቱ ቀን ድረስ ምድረ ኢትዮጵያን በክፉ ሃሳብና ድርጊቶቹ የመረዘ አሸባሪ ቡድን በህይወት የሚቆይበት የሰዓታት እድሜ ባገኘ ቁጥር በህዝብና ምድራችን ላይ የሚፈጥረው የጥፋት ክምር ምን ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል፡፡

በአፋር ክልል በሴቶችና ህጻናት ላይ፤ በአማራ ክልል በአጋምሳ የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ የፈጸማቸው የጅምላ ግድያዎች የሚያሳስቡን ነገር ቢኖር ራሳቸውን ባበደ ውሻ ማእረግ ለጥፋት ያሰማሩትን የትህነግ አሸባሪ ቡድን ታጣቂና ሰርጎገቦች እንደ አበደ ውሻ የትም መቼም በምንም አይነት መንገድ የመደምሰስ ሥራ አስፈላጊነት ዛሬም አንገብጋቢ መሆኑን ብቻ ነው፡፡ ይህን የጥፋት አምባሳደር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ ህልውናችንን እና ሉዐላዊነታችንን ለማስጠበቅ የጀመርነው ክፋትና ክፉዎችን የማጽዳት ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

ያበደን ውሻ ሰፈር በማስለቀቅ ብቻ ከእብድ ውሻ በሽታ ሥጋት ነጻ መሆን እንደማይቻለው ሁሉ በትህነግ የሽብርተኞች ቡድን ላይ እየወሰድን ያለነው የማያዳግም እርምጃ የሚያበቃው የትህነግን ታጣቂዎች ከቦታ ቦታ በማሯሯጥ ሳይሆን በየትኛውም የኢትዮጵያ መሬት ላይ በህይወት እንዳይገኙ ማድረግ ስንችል ብቻ ነው፡፡

ስለሆነም ይህንን ግብ ማሳካት የሚችል ስነ ልቡናዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ዝግጁነታችን በእያንዳንዷ ቀን በእጥፍ እያሳደግን በአንድነት መጓዝ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡ እብዱ ውሻ እስካልተወገደ ድረስ ዝግጁ ከመሆን ውጭ ሌላ አዋጭ የሆነ ፍቱን መድኀኒት የለም፡፡

በመሆኑም በህልውና እና በሉዑላዊነታችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ በገባንበት ጦርነት ውስጥ በወልደያ፣ በደብረ ዘቢጥ እና ጋሸና ግንባር በአሸባሪው የትህነግ ታጣቂ ላይ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ እና ከመላው ብሄር ብሄረሰቦች የተውጣጡት የልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች እንዲሁም ሀቀኛ ፋኖዎች እየወሰዱት ባለው እርምጃ የትህነግ የክፋት ክምር እየተናደ ራሱ በቆፈረው የክፋት ጉድጓድ ውስጥ እየተቀበረ ይገኛል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከምድረ ኢትዮጵያ ተጠርጎ እስኪወገድ ድረስ ክፋትንና ክፉዎችን በመቅበር ህልውና እና ሉዐላዊነታችንን የማስከበር ተጋድሏችን እንደጎመራ ይቀጥላል፡፡”

ድል ለኢትዮጵያ!!
ድል ለአማራ!!!

Exit mobile version