Site icon ETHIO12.COM

በእነ አዲስዓለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾም ተወሰነ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በእነ ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾም ወሰነ፡፡ችሎቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀል መጠርጠራቸውን ተከትሎ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ ንብረት በሚል በአዲስ አበባ በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኘው መኖሪያ ቤት ይታገድልኝ በማለት ባቀረበው አቤቱታ ነው፡፡

ዐቃቤ ሕግ በአቤቱታው ከዚህ ከተከሳሹ ቤት የሚገኝ የኪራይ ገቢ ለሽብር ተልዕኮ እየዋለ በመሆኑ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ንብረቱ በገለልተኛ ወገን እንዲተዳደር ይደረግ በማለት አመልክቷል፡፡

ተከሳሹ ይህ ሊሆን አይገባም በማለት የተከራከረ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ የተከሳሹን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ቤቱ ገለልተኛ አስተዳዳሪ እንዲሾምለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡በጥላሁን ካሳ

Exit mobile version