Site icon ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ “ሰራዊታችን የደረሰበት ጉዳት የለም፤በቅርቡ አዲስ አበባ…”

tplf looted
ፎቶ – የትህነግ ሰራዊት ከወረራቸው አካባቢዎች ዘርፎ ሊወጣ ሲል መንገድ ተዘግቶበት የዘረፈውን ጥሎ ሲሸሽ የተነሳ – ምንጭ መከላከያ

“አሸባሪ” ተብሎ የተስየመው ትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው በአማራና አፋር ክልል በመልሶ ማጥቃት ምን ጥቃት እንዳልደረሰባቸው አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ሊያጠቃ የመጣውን ሃይል በሙሉ የትህነግ ሃይል ሙሉ በሙሉ እንደመሰሰና በቅርቡ አዲስ አበባ ከመግባት የሚያግዳቸው ሃይል እንደሌለ አስታውቀዋል።

በትናትናው ዕለት ከትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋር ወይይት ያደረጉት አቶ ጌታቸው፣ አሸባሪው ድርጅታቸው ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ሲያስታውቁ በወረራ ይዟቸው የነበረውን ስፍራዎች እንዴት እንደለቀቁ አልተናገሩም።

ሰሞኑንን በርካታ ቦታዎች መለቀቃቸውና በትህነግ ሃይል ላይ ከፍተኛ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት መድረሱን፣ በርካታ መማረካቸውንና የተረፈውም ወራሪ ሃይል ተከቦ መውጣት እንደማይችል በተደጋጋሚ የተለቀቁት ቦታዎች በምስል እየታዩ፣ አርሶ አደሩ ምስክርነት እየሰጠ፣ የወደሙ ሃብትና መሰረተ ልማቶች እየታዩ ምስክርነት ስለመቅረቡ አቶ ጌታቸው አልተጠየቁም።

በደፈናው የትህነግ ሃይል የሪፕብሊካን ጋርድ ሳይቀር ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን አቶ ጌታቸው የገለጹት እጃቸውን ከጃቸው ጋር በማፋጨት ነው። ” እጅግ ያሳዝናል” ሲሉ በተደጋጋሚ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም በመጥራት ሰራዊታቸው ጭንቅላት ለይቶ የሚመታ ብቃት እንዳለው ያስታወቁት አቶ ጌታቸው “የአማራ ልዩ ሃይል የመዋጋት አቅም የለውም” ሲሉ ተደምተዋል። የትህነግ ሃይል በርካታ ቀያይ ኮፍያ ከገደላቸው የሪፐብሊካን ሃይል ወታደሮች ላይ ቢረከበም መጠኑ ሰፋፊ ስለሆነ ለጭንቅላታቸው እንደበዛባቸው አመልክተዋል።

ድራማ በሚመስል አገላለጽ ውይይታቸውን ያደረጉት አቶ ጌታቸው፣ አዲስ አበባ ለመግባት የሚከላለክላቸው አካል እንደሌለም አስታውቀዋል። አቶ ጌታቸው ከዳር እስከዳር በተደጋጋሚ “አሸባሪ” በሚል የተቃውሞ ስልፍ እያደረገ ስላለውና በመቶ ሽህ የሚቆጠር ሰራዊት በፈቃደኛነት በሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ ማስለጠኛ በምግባቱን አስመልክቶ ምንም አላሉም። ወደ አዲስ አበባ መግባት እንደሚችሉ ከመናገራቸው ውጭ እንዴትና በየት በኩል ህዝቡን አምልጠው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አላመለከቱም።

“በተለመደው የጥያቄና መልስ መርህ ሳይሆን በርካታ ቦታዎችን በመልቀቃቸው ሳቢያ የተፈጠረውን የስነ ልቦና ሽንፈት ለማስታገስ የተሰጠ የሚመስል ውይይት ነው” ያሉ፣ ስለተማረኩ አዋጊዎች፣ ስለወደሙ የሕዝብ ሃብቶችና የጤና ተቋማት እንዲሁም በጅምላ በትህነግ ተፈጁ ትብለው ምስክርነት ስለሰጡ ወገኖች አቶ ጌታቸው አልተናገሩም። በውይይቱም አለመጥየቃቸውን አምለክተዋል። እናም ዓላማው ግልጽ ነው።

“ከአርሶ አደሩ ጋር ችግር የለብንም” ያሉት አቶ ጌታቸው ልማቶችን እንደማይነኩ ደጋገመው አመልክተዋል። ይሁንና ሰራዊታቸው በርካታ መሰረተ ልማቶችን፣ አንድ ከተማና ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተጠይቀው አላስተባበሉም። ከወረሩት ስፋራዎችና ከተሞች የትኞቹ አሁን ድረስ በትህነግ እጅ እንደሚገኝ ይፋ አላደረጉም። የአማራ ክልል ግን ነጻ የወጡ ከተሞችንና አካባቢዎችን በስም ዘርዝሮ በምስል አስደግፎ ይፋ እያደረገ ነው።

እሳቸው ይህንን ውይይት በሚያደርጉበት ወቅት አስተያየት ሲያካፍሉ የነበሩ የትህነግ ቁልፍ ደጋፊ የሚባሉ በግንባር ሽንፈት እየደረሰ መሆኑንን ጠቅሰው የተቀያየሩትን የማህበራዊ ገጽ ቅጂ እየለጠፉ “አቤት ውሸት” ሲሉ ነበር።

አቶ ጌታቸው ” መዋጋት አይችልም” ያሉት የአማራ ልዩ ሃይል ቀጣይ እጣው መደምሰስ እንደሆነ ደጋግመው ተናግረዋል። ከወር በፊት ጎንደርን፣ ባህር ዳርንና ደብረብርሃንን ተቆጣጥረው ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ በቲወተር ገጻቸው ደጋግመው ያስታወቁት አቶ ጌታቸው ብቻ ሳይሆኑ፤ የሚዲያና የማህበራዊ ገጹን የሚመሩት ነጮች ጭምር ነበሩ። መከላከያው ዋጋ እንደሌለው፣ ልዩ ሃይሉ የመዋጋት ብቃት እንደሌለው የገለጹት አቶ ጌታቸው ያሉት ተጋባራዊ እንዳይሆን ማን እንዳገዳቸው አልገለጹም።

“ድሮንም ቢመጣ ጦረንቱን አይቀይረውም” በሚል አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል። ይህን እንጂ በአፋር ግንባርም ሆነ በአማራ ግንባር ከአየር ስለደረሰው ጥቃት አየር ሃይል ላለው ማስተባበያ አልሰጡም።

በንግግራቸው መካከል እጅግ አድርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚኮንኑትና ለሳቸው ሲባል የሚደረግ ጦርነት እንደሆነ በመጥቀስ ህዝብ ጦርነቱን በማውገዘ ” አልዋጋም” እንዲል ጥሪ አቅርበዋል። በቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፈለ ጊዜ መብራት፣ ስልክ፣ ባንክ የመሳሰሉት አገልግሎቶች መክፈት ብቻ ለሰላም እንዲቀመጡ በቂ መሆናችውን ያስታወቁት አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል ያስቀመጡትን ስምንት ነጥቦች ለምን እንደቀየሩ ይፋ አላደረጉም።

The federal forces counteroffensive restarted after Addis Ababa lifted the unilateral ceasefire it declared late June. መንግስት ጥሎት የነበረውን የተናጠል ተኩስ አቁም ካነሳ በሁዋላ መልሶ ማጥቃት መጀመሩን ያስታወቀው አሶሲየትድ ፕሬስ ለመቀለ ቅርብ የሆኑት አላማጣና ኮረምን መያዛቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸውም ሆኑ ትህነግ ይህንን አላስተባበሉም። ከተተቀሱት ከተሞች ቀጥላ ያለችው አንድ ቀበሌ ስትቀር ቀጣይዋ ከተማ መቀለ ነች።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የጦር ግንባር ዜናዎች ሙሉ በሙሉ ስለመቀየራቸው የውጭ ሚዲያዎች ሳይቀሩ እየገለጹ ነው። ትህነግ አንድ መንደር ሙሉ በሙሉ ማውደሙ፣ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄዱ ቦታና እየተጠቀሰ በሰዎች ምስክርነትና በሳተላይት መረጃ ይፋ እየሆነ ነው። ይህንን አስመለክቶ አቶ ጌታቸው ያሉት ነገር የለም። ይህ የጦር ወንጀል ስለመሆኑ ግን በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ሊጥ፣ ሌማትና ዱቄት ሳይቀር እየሰረቃቸው እንደነበር በሚያሳዝን ሁኔታ ስለገለጹት፣ ከብቶቻቸው ስለተጨፈጨፉባቸው አርሶ አደሮች ለቅሶና ምስክርነት ምን ያላሉት አቶ ጌታቸው ” የማይታጠፍ ሃይል አለን” ሲሉ ወደ አዲስ አበባ ለመገስገስ የሚያዳግታቸው አንዳችም ሃይል እንደሌለ ደጋግመው ተናግረዋል።

መንግስት በበኩል በሙሉ ማጥቃት ትህነግን ታሪክ የማድረጉን ዘመቻ ለመጀመር የዝናቡን ጋብ ማለትና የጭቃውን መጥገግ እንደሚጠባበቅ በስፋት እየተነገረ ነው።

Exit mobile version