Site icon ETHIO12.COM

«አሸባሪው ህውሃት በማፈግፈግ የመጨረሻ ሞቱን እየተጠባበቀ ነው»

የጋይንት ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ገድል አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ ይጠናቀቃል

“ከደብረ ታቦር እስከ ጨጨሆ በተካሄደው ውጊያ በአሸባሪው ህውሃት ላይ የተመዘገበው አኩሪ ድል በቀጣይ ተልዕኮም ይደገማል ሲሉ የ34ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ያለው አድማስ ገለጹ።

ክፍለ ጦራቸው ከ33ኛ ክፍለ ጦር ጋር በመተጋገዝ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ተጠግቶ የነበረውን የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ተከታትሎ በመምታት ደብረ ዘቢጥ ተራራ ላይ እንዲወሸቅ ሆኗ።

እንደ ኮሎኔል ያለው አድማስ ገለጻ በደብረ ታቦር ዙሪያ፣ በጋሳይ፣ በክምር ድንጋይና በጉና አካባቢዎች በተካሄደው ውጊያ አሸባሪው ቡድን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ 120 ኪሎ ሜትር በማፈግፈግ ደብረ ዘቢጥ ተራራ ላይ መሽጎ የመጨረሻ ሞቱን እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር ፍቅር ስሜትና እልህ አሸባሪውን ቡድን እግር በእግር እየተከታተለ በማደን ላይ የሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በቀጣይም በቀሪ ስፍራዎችም ባለበት ቦታ ተከታትሎ ድባቅ እንደሚመታው ጠቁመዋል።

በደብረ ታቦር ግንባር ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ያሰማራው በርካታ ቁጥር ያለው ሃይል በአምስት ቀናት ውስጥ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ መሆኑ ቀጣይ አቅም እንዳይኖረው ማድረጉንም ተናግረዋል።

በዚህም አሸባሪው ቡድን አሉኝ የሚላቸውን አዋጊዎችና ወሳኝ ሃይሎቹን በመደምሰስና በምርኮ ያጣው ሃይል የአማራ ክልልን ሃብትና ንብረት በመዝረፍ ለመክበር የነበረውን ከፍተኛ ፍላጎት በግንባሩ በተመዘገበው ድል መምከኑን ተናግረዋል።

ለተገኘው ድልም በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ያለው ህዝብ በስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እያደረገ ያለው ደጋፍ መሰረት መሆኑን ገልጸው ይህም ቀድሞም የነበረውን የሰራዊት የውጊያ ብቃትና ህዝባዊ ወኔ እያጠናከረው መሆኑን አስረድተዋል።

“አሁን ላይ መሳሪያ ያለው የጋይንትና የአካባቢው ህዝብ ጠላትን መዋጋት ጀምሯል” ያሉት ኮሎኔል ያለው፣ በዚህም ከጉና ተራራ ጀምሮ ተበታትኖ የነበረውን የጠላት ሃይል ለቅሞ ማጽዳቱን በማሳያነት አቅርበዋል።

የጥላትን የወረራ ጥቃት ተከታትሎ በማምከን ላይ ከሚገኙት የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አባላት አንዱ የሆኑት የ34ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ፀሐፊ ሻምበል ደርብ ወንድምሰው እንደሚሉት ሰራዊታችን በተሻለ ቅንጅት ጠላትን በመምታት ከሙትና ቁስለኛነት እንዲሁም ከምርኮኛነት የተረፈው ወደ መጣበት ተመልሷል።

ከአዛዣችን የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመፈጸምም በአጭር ጊዜ ውጊያ ደብረ ዘቢጥ ተራራ ላይ እንዲወሸቅ መደረጉን ተናግረዋል።

እስከ አሁን በተደረገው ውጊያም በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሶበታል ያሉት ሻምበል ደርብ በጣም ብዙ ጀሌዎቹ ቢደመሰሱበትም የአሸባሪነት ፍላጎቱን ለማሟላት አሁንም የትግራይን ወጣት እየማገደ መሆኑን አመልክተዋል።

አሁን ላይ ሰራዊታችን ከህብረተሰቡ በሚደረግለት ድጋፍና እያስመዘገበ በመጣው ድል በከፍተኛ የውጊያ ወኔና ሞራል በተለመደው ጀግንነቱ ቀሪ የቡድንን አባላት እንደሚደመስስም ገልጸዋል።

ጀግና ኢትዮጵያዊያን እያሉ ሃገር ካላፈረስኩ በማለት በንጹሐን ላይ የሽብር ድርጊቱን እየፈጸመ የሚገኘው ቡድን በተግባር እየተካሔደ እንዳለው ሁሉ በአሽር ጊዜ ውስጥ የጸጥታ ስጋት በማይሆንበት መልክ እንደሚደመሰስም ጠቁመዋል። – (ኢዜአ)

Exit mobile version