Site icon ETHIO12.COM

የጁንታው መደምሰስ አመላካቾች!!

በስልጣን ላይ በነበረ ጊዜ ከሀገርና ህዝብ በዘረፈው ገንዘብ ተማምኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተማማለው አሸባሪ ኃይል ፣ ፀሃይ እያዘቀዘቀችበት መሆኑን በርካታ አመላካች እማኞች ፍንትው ብለው መታየት ጀምረዋል። ለዚህ ማረጋገጫው ደግሞ ደብረፅዮን አደራድሩን ብሎ ለአንቶኒዮ ጉተሬዝ ፃፈ የተባለው ደብዳቤ አንዱ ነው።

በእርግጥ የጨነቀ ዕለት ሆኖበት እንጂ የአሸባሪው ህወሃት መሪም ይሁን ጀሌዎቹ ሰላምን አምርረው የሚጠሉ የሰይጣን ታላቅ ወንድም ስለመሆናቸው በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን የሠላም አማራጭ የቀበሩ ህልመኛ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

በጦርነት ተወልደው በጦርነት የኖሩት ህወሐታውያን መጨረሻውም በጦርነት እንዲያበቃ ወስነው በገዛ ሀገራቸው ዜጋ ላይ አፈሙዝ ማዞራቸው የክህደት ጥጋቸው አንድ ማሳያ ነው።

የሆነ ሆኖ በየጎሬው የደበቁትን መሳሪያ እና በደህና ቀን ያሸሹትን ገንዘብ ተጠቅመው በወንድም ህዝባቸው ላይ ጥቃት ቢያደርሱም ኢትዮጵያውያን ግን አሁንስ በቃን ብለው ሀገር በቀሉን ጠላት አምርረው ሊታገሉት ከፊት ለፊቱ ብረት ይዞ ከመጋፈጥ በዘለለ ያላቸውን ጥሪት እያዋጡ ግብዓተ መሬቱን ለማፋጠን እየተረባረቡ ነው።

በየአካባቢው ወጣቱ ተደራጅቶ ፀጥታውን ከመጠበቅ ባለፈ ልጆቻቸውን መርቀው ወደየማሰልጠኛው የላኩ ወላጆች እልህና ወኔ በየዕለቱ ወደጦር ግንባር የሚላኩ የዕርድ ከብቶች እናቶች የሚያዘጋጁት ስንቅ እንደዚሁም በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ስለአሸባሪው ህወሃት ክፋት የሚለቀቁ መልዕክቶች ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።

ኢትዮጵያውያንን እንዲህ በአንድነት እንዲነሱ ያደረጋቸው ጉዳይ ደግሞ በጭካኔው ወደር ያልተገኘለት ሸፍጠኛና አሻጥረኛው ህወሓት በስልጣን ላይ በነበረ ጊዜ ከሰራው ግፍ በዘለለ የብዙ ዓመታት ታሪክ ያላትን የጥቁሮች የነፃነት ተምሳሌትና የምስረቅ አፍሪካ አይን የሆነችው ሀገራችንን ለማፍረስ ሲኦል እወርዳለሁ ማለቱን ከመስማት በዘለለ ወደተግባር በመግባቱ ነው።

ጁንታው በወረራቸው የአማራና አፋር ክልል ንፁሃን ላይ የጅምላ ግድያ ከመፈፀም ባለፈ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ህፃናትን ደፍሯል። አካላዊ ቁመናው ሰዋዊ ቢመስልም ህሊና ቢስነቱን ቁልጭ አድርገው ካሳዩን አልተሰሜ ታሪኮች መካከል እንሰሳትን በአረር ማቃጠሉና የቻለውን ያህል ዘርፎ ያልቻለውን የህዝብ ሀብት በምቀኝነት ማውደሙ ሌላው ሒሳብ ማወራረጃ የጭካኔ ጅራፉ መሆኑን በሚገባ አሳይቶናል።

ሌላው የዚህ ቡድን አስገራሚ ጉዳይ በየኩሽናው የተገኘን ቡኮ እና ድፍድፍ እየተሸከመ መሔዱ ነው። ምናልባትም በሊጥ እና ድፍድፍ ዘራፊነቱ የመጀመሪያው ስለመሆኑ ታሪክን ለማገላበጥ ምርምር የሚጠይቅ ጉዳይም አይመስለኝም በእርግጠኝነት እሱ የመጀመሪያ ነውና።

ያለ የሌለ አቅሙን አቀናጅቶ የተጠቀመው ጁንታ በሀገር ቤት ከወሸመው ሸኔ ጀምሮ በውጭ ሀገር ካሉት ተንደባላዮቹ ጋር ተዳምሮ ሊያፈርሳት ያሰባትን ኢትዮጵያ ለማፍረስ ግን የሚፈቅድለት ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን አሁን እርግጠኛ ሆኗል። ለዚህም ማሳያው ቀደም ሲል በቁጥጥሬ ስር ናቸው እያለ ፎቶ የተነሳባቸው ቦታዎች በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና በፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም በህዝብ አንድነት ነፃ እየወጡ ነው።

የተበታተነው ኃይልም የኢትዮጵያውያንን የተባበረ ክንድ እየቀመሰ ነው። በየጎሬው የደበቃቸው ተተኳሾችም እየተመናመኑበት በየስርቻው የተወሸቁ የነዳጅ በርሜሎችም ባዶነታቸውን እያረጋገጡለት ነው። በተለይ በስሙ ሲነገድበት የኖረው የትግራይ ህዝብም ከእለት ጉርስ ማጣት ጋር ተያይዞ ኑሮው እንደ በረሃ ሀሩር አንድዶታል። ጥሞናውን በደንብ አጣጥሞታል። ማን ይሻለው እንደሆነም ከሊቀሰይጣኑ ወያኔ ክፉ ስራ በሚገባ ተረድቶታል።

በእርግጥ የትግራይ ህዝብ በፊትም ተገዶ እንጂ ወዶት አብሮ እንዳልኖረ የጁንታው ሰለባ ከሆኑት እነ ኢንጂነር እምብዛ ታደሰ መረዳት ይቻላል። ከክልሉ ውጪ በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖሩ ትግራዋዮችም በየጊዜው ይኸን ቡድን ከመቃወም ባለፈ ከገንዘብ ድጋፍ ጀምሮ ደም በመለገስ ዕለት ከዕለት ከኢትዮጵያውያን ጋር መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃም ከአንዴም ስምንት ጊዜ በዚህ ጉዳይ ስብሰባ የተቀመጠው የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ችግሮቿን እራሷ ትፍታ በሚሉ ከእውነት ጋር የቆሙ መንግስታት ድጋፍ ጁንታው ድንኳን ተክሎ ለቅሶ እንዲቀመጥ ማረጋገጫ ሰጥተውታል።

ይህ ሁሉ ነገር ተዳምሮ አሁን ላይ ያለው ኢትዮጵያዊነት እንደ አድዋው ሁሉ ተጋምዷልና የጁንታው መደምሰስም ስለተቃረበ እነሊቀ ሰይጣን ንሰሃ ይግቡ።

ሻምበል አብዮት ዋሚ
ፎቶግራፍ Google image

Exit mobile version