Site icon ETHIO12.COM

ሸኔ እየተበተነ ነው -“መንገድ ስተናል፤ቅጥረኛ እየሆን ነው፣የኦሮሞን ሕዝብ እናክብር”

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እየተከፋፈለ አምስተኛው ደረጃ ላይ ሲደርስ ” ኦነግ ሸኔ” ተባለ። ኦነግ ቁጥር አምስት ማለት ነው። መሪውም አቶ ዳውድ ኢብሳ ነበሩ። በትግራይ በኩል አቶ ስብሃት አቀባበል ያደረጉለት የኦነግ ሰራዊት “ለምን በትግራይ በኩል አገር ቤት መግባትን መረጠ?” የሚለው ጥያቄ ዛሬ ይፋዊ መልስ ያገኘ ቢሆንም እያደር ይፋ የሚሆኑ ጉዳዮች ስለመኖራቸው በስፋት ይደመጥ ነበር።

አቶ ዳውድ ” ይቅርታ ሰጪና ጠያቂ የለም” ሲሉ በይፋ የመንግስትን ገዢነት ማናናቅ በጀመሩ ማግስት የትጥቅ ትግል ዜናና የሃዘን ወሬ መሰማት ጀመረ። ኦነግ ሸኔ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ሲያስታውቅ፣ እነ አቶ ዳውድ ” ጦር የለንም። እኛን አይወክልም” በሚል ጫካ የተደበቀው ኦነግ ሸኔና፣ ከተማ ህንጻ ውስጥ ቁጭ ያለው ኦነግ ሸኔ የተለያዩ አካላት እንደሆኑ በተደጋጋሚ መረጃ ይሰጥ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህ መካከል ጃል መሮ በቪኦኤ ብቅ ብሎ ራሱን አስተዋወቀ። ቀደም ሲል ኦነግ ሸኔ ወደ አገር ቤት ሲገባ አብረው የመጡት አቶ ዱጋሳ በከኮ “የቀድሞ ኦነግ ሰራዊት መሪ ) ወዲያው ከአገር መውጣታቸው ተሰማ። እሳቸው በውጭ ያለውን የኦነግ ሸኔ ሃይል በማደራጀት የትጥቅ ትግሉን እንዲመሩ ተደርጎ ኡጋንዳ ከሁለት የትህነግ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ መደረጉን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ያስታወሳሉ።

ዱጋሳ ኡጋንዳና አውሮፓ እየተመላለሱ ሃብትና እርዳታ በማሰባሰብ ሸኔ አቅም እንዲገነባ ተደረገ። የዜናው ሰዎች እንደሚሉት ለውጡን ተከትሎ የኦሮሚያ ገዢ ፓርቲ የጸዳ ስላለነበር ኦነግ ሸኔ ኦሮሚያ እንዳሻው የመሆን እድል ተመቻቸለት።

ማዕከላዊ መነግስት ራሱን እያጸና፣ ኦሮሚያም በጥብቅ ክትትል ራሱን እያጸዳ ሲሄድ ኦነግ ሸኔ በድብቅ ከትህነግ ጋር እየሰራ መሆኑን በመኮነን ምክትሉ አቶ አራርሳ በሚመሩት ስብሰባ አቶ ዳውድ ታገዱ። ውሎ አድሮ አቶ አራርሶ ቢቆላና አቶ ቀጀላ አደባባይ ወጥተው አቶ ዳውድ ከትህነግ ጋር አብረው እንደሚሰሩ፣ ቢመከሩ አልሰማ ማለታቸው፣ ጦርነትና ሰላምን አጣቅሶ አንድ ላይ መሄድ የድርጅታቸው መርህ እንዳልሆን ቢነገራቸውም አልሰማ በማለታቸው ፓርቲው እሳቸውን ለማገድ መገደዱንይፋ አደረጉ። ሌሎች በርካታ ክሶች ሰንዘረውም ነበር።

አቶ ዳውድ በበኩላቸው ” ከመንግስት ጋር ሆነውና በመንግስት ተደልለው” ሲሉ ክሳቸውን አስተባበለው ያባረሯቸውን ማገዳቸውን አስታወቁ። በዚህ መካከል ምርጫ ደረሰና ማስፈርት ማሟላት ባለመቻላቸው ወይም ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደው እንዲመጡ የታዘዙትን ባለማሟላታቸው ድርጅቱ ከመርጫ ወጣ። ይህ ሲሆን ጎን ለጎን “ሸኔ” ስሙን ቀይሮ ” የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ነኝ” ብሎ በቪኦኤ በኩል አዲሱን ስሙን ይፋ አደረገ። ቪኦኤ ” ማን ነህ? ከየት ነህ? ለምን? እንዴት? … ? ሳይል አዲሱን ስም መለያ አድርጎ ሪፖርት መስራት ጀመረ።

ትህነግ ወረራ ከፈጸመ በሁዋላ ቁጥር 2 የተባለውን ኢአሃዴግ ለማቋቋም ውስጥ ውስጡን ሲሰራ ቆይቶ ከኦነግ ሸኔ ጋር ስምምነት መፍጠሩን ያፋ ሲያደርግ አስቀደመው ከዳውድ ኢብሳ ጋር ያልተስማማሙት ወገኖች ” ድሮም የምናውቀው ነው” ሲሉ ጉዳዩ አዲስ እንዳልሆነባቸው አስታወቁ።

ዜናው በመላው ኦሮሚያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሲሆን፣ የትህራይ ነጻ አውጪ ግንባር ኦሮሞ ላይ በጅምላና በተናጠል የፈጸመውን በደል እያነሱ ስምምነቱ ” ክህደት” ሲሉ የሚያጣጥሉ በዙ። ኦነግ የተሸፋፈነለት ጉዳይ ሁሉ ከዳውድ ኢብሳ ጋር እየተያያዘ በነባር የኦሮሞ ታጋዮች ይፋ ሆነ። የኦነግ መሪ የነበሩት አቶ ገላሳ ዲልቦ ነዲ ገመዳን ማን እንዳስበላቸው፣ ምርጥ የሚባሉ የኦሮሞ ልጆችን ስም ዘርዝር እየሰጠ ማን ለአደጋ እንደዳረጋቸው የተናገሩት ሌሎች ከሰጡት መረጃ ሁሉ ከበደ።

በዚህ መካከል ነው እንግዲህ ሸኔ ውስጥ ጉዳዩ ያልገባቸው “ምን እየሆነ ነው” ሲሉ የጠየቁት። ለዝግጅት ክፍላችን መረጃ የሰጡት የድርጅቱ የውጭ ድጋፍ ሰጪ የነበሩ “ኦነግ ሸኔን የሚደግፉ አሁን ላይ ተከፋለዋል። አገር ቤትም ጫካ ያሉት እየተበተኑ ነው። ለመንግስት ጥያቄ አቅርበው እጅ የሚሰጡ ይኖራሉ” ብለዋል። አያይዘውም ” መንገድ ስተናል፤ ቅጥረኛ እየሆንን ነው፤ የኦሮሞን ህዝብ እናክብር፣ ልዩነትን በስለጠነ መነገድ በመፍታት ህዝብን ከችግር እንታደግ” በሚል ከትህነግ ጋር በይፋ የተደረገውን ስምምነት የተቃወሙ እየመከሩ መሆኑንን አመልክተዋል።

እንደ መረጃው ባለቤት የሸኔ አደረጃጀቱና የመዋቅሩ ግንኙነት፣ በየስፍራው ያለው ሴል መረብ የሚያስረዳው መረጃ መንግስት እንጅ ሳይገባ እንዳልቀረ ነው። ኩማ ወይም ጃል መሮ ሳይሆን ዋናው መሪ ሌላ እንደሆነ ያስታወቁት እኚሁ መረጃ ሰጪ፣ በሰፊው ወይም አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብ አሁን ላይ በኦነግ ሸኔ ውሳኔ ደስተኛ አለመሆኑ ለክፍፍሉ ዋና ምክንያት እንደሆነ አመላክተዋል።

ሰሞኑንን የሸኔ ታጣቂዎች በሃሳብ ልዩነት እርስ በርስ ተታኩሰው መገዳደላቸውን አዲስ ዘመን መረጃ ያቀበሉትን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

Exit mobile version