Site icon ETHIO12.COM

“ደሴ እንገናኝ” አቶ ጌታቸው፤ ሰቆጣ ነጻ ወጣ

አቶ ጌታቸው ረዳ ” ደሴ እንገናኝ” ባሉ በሶስተኛው ቀን ሰቆጣ ነጻ መሆኗንን ነዋሪዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ከስፍራው አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ለዚህ የሰጡት ምላሽ የለም። ከመመከት ወደ ማጥቃት የተሸጋገረው የኢትዮጵያ ሃይል እግር በእግር እየተከተለ እያጠቃ መሆኑ ተመልክቷል።

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪግንባር እያለ ራሱን የሚጠራው ሃይል፣ ስሙ እንደሚያመልክተው ለምን ወደ አፋርና አማራ ክልል ገብቶ ጥቃት እንደሚፈጽም ሲጠይቅ ” ለትግራይ ሕዝብ ስጋት የሆኑ አካላት በሙሉ ስጋት የማይሆኑበት ደረጃ እስኪደርሱ ጥቃቱ ይቀጥላል” ሲሉ በተደጋጋሚ የሚናገሩት የድርጅቱ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ” ግንባር እየመረጠ ይመታል” ያሉት ሰራዊታቸው ደሴ እንደሚገባ ያስታወቁት በፊስ ቡካቸው ነበር።

በግጥምና በቅኔ አጅበው ” ደሴ እንገናኝ” ያሉት አቶ ጌታቸው ወልደያ ሙሉ በሙሉ ነጻ መውጣቷ ከስፋራው በቴሌቪዥን ነዋሪዎች አስተያየት እይሰጡ ባለበት ወቅት በመሆኑ ቀጠሯቸውን ባሰፈሩበት ስር ብዙ “ፉተታ” የሆነ መልስ ተመልሶላቸዋል። ደጋፊዎቻቸው በበኩላቸው ” ጀጋኑ” እያሉ እንደወትሮው በአበባና በልብ ቅርጽ አሞግሰዋቸው ነበር።

ይህ በሆነ በሶስተኛው ቀን ነው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር “ለሰቆጣ ወጣቶች እና ለመላው የዋግ ጀግኖች ለከፈላችሁት መስዋእትነት ታላቅ የክብር ምሥጋናዬን አቀርባለሁ” ሲሉ የሰቆጣን ነጻ መውጣት አስመልክቶ ለድሉና ድሉን ላስገኙት “ክብረት ይስጥልን” ያሉት። አቶ አገኘሁም ሆነ የአማራ ክልል ሚዲያ የሰቆጣን ነጻ መውጣት ይፋ ቢናገሩም ከትህነግ ወገን እንደ ድርጅት፣ አቶ ጌታቸውም እንደ ግለሰብ ይህ እስከታተመ ድረስ በማስተባበልም ሆነ በማረጋገጥ ያሉት ነገር የለም።

ትህነግ ምንም ባይልም የአማራ ልዩ ኃይል፣ የዋግ ሚሊሻና ወጣቶች ባካሄዱት የተቀናጀ ዘመቻ የሰቆጣ ከተማና አካባቢውን ከአሸባሪው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ወራሪ ሃይል ነጻ ማድረጋቸውን ተረጋግጧል። በስፍራው እንደነበሩ የጠቀሱ የሚዲያ ባለሙያዎችም ምስክርነት ሰጥተዋል። ለአካባቢው ቅርብ የሆኑና ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆኑ ቤተሰቦቻቸው ጋር በመደወል ከደሴ የጠራ መረጃ ማግኘታቸውን ለዝግጅት ክፍሉ መስክረዋል።

በዘመቻው “የወገን ጦር ወራሪውን የትህነግ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል” ሲል አማራ ሚዲያ ዘግቧል። በአሁኑ ጊዜም የማጽዳትና የአሰሳ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አሚኮ ሰቆጣ በመገኘት መታዘበቡን አስፍሯል።የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ለልዩ ኃይሉና ሚሊሻው ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን፣አሚኮ ያነጋገራቸው ወጣቶች የዋግ ሚሊሻና ወጣቶች ዘመቻው እንዲሳካ ያደረጉት ተጋድሎ ለድል ማብቃቱን እንዳስደሰታቸው፣ድሉ የመላው ሀገሪቱ እስከሚሆን ድረስ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ንጉሡ ማሩ ከሰቆጣ ዜና አሰራጭቷል።

“ለሰቆጣ ወጣቶች እና ለመላው የዋግ ጀግኖች ለከፈላችሁት መስዋእትነት ታላቅ የክብር ምሥጋናዬን አቀርባለሁ” ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በትዊተር የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። “ዛሬ ጀግናው የአማራ ክልል ኀይል ለቀናት በአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን ተይዞ የነበረውን የሰቆጣ ከተማ ተቆጣጥሮታል። ለሰቆጣ ወጣቶችና ለመላው የዋግ ጀግኖች ለከፈላችሁት መስዋእትነት ታላቅ የክብር ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ትህነግ ይደመሰሳል! እናሸንፋለን !” ብለዋል።
Read more

ሰሃላ ሰይምትን እና ዝቋላን በሚያካልለው የተከዜ ወንዝ ኮሪደር ተገን አድርጎ አካባቢውን ሲዘርፍ የነበረው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን አባላት በአካባቢው ሚሊሻ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

የአሸባሪው ትህነግ ቡድን አባላት ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ በስሃላ ሰየምት እና ዝቋላ አካባቢ የዘረፉትን ሃብት እና ንብረት ወደትግራይ ለማሸሽ ጥረት ላይ እያሉ በድንበር አካባቢዎች መሽጎ የነበረው የአካባቢው የሚሊሻ አባላት እና ወጣቶች ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል፡፡

ከስሃላ ሰየምት ተባሮ ወደ ዝቋላ የገባውን የአሸባሪ ቡድን በመደምሰስ የምዕራብ እና የምስራቅ በለሳ ሚሊሻዎች ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡

የሰሃላ ሰየምት እና ዝቋላ ወረዳዎችም ከአሸባሪ ቡድኑ በማስለቀቅ በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ቁጥጥር ስር ገብተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ከፍያለው ደባሽ -ከስሃላ ሰየምት

AMC

Exit mobile version