Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ለዳግም ” የሰው ጎርፍ ጥቃት” መዘጋጀቱ ታውቆ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ

ትህነግ ለዳግም ” የሰው ጎርፍ ጥቃት” መዘጋጀቱ ታውቆ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ። ይህ የተሰማው ሰሞኑንን በተለያዩ ግንባሮች ሽንፈት የገጠመው ትህነግ በውስጡ ጉምጉምታው እየበዛ መሆኑን ተከትሎ በሚስጡር ይፋ ያደረገው መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ የመንግስት ሃላፊዎች ባደረጉት ንግግር ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድህንነት አማካሪ አቶ ገዱ ” ይህን ሃይል ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በወጉ እየተሰራ ነው” ሲሉ በደሴ ተገኝተው ተናግረዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የጸጥታ ሃላፊዎች መረጃው እንዳላቸውና ህዝብን በማስተባበር፣ በማደራጀትና፣ አዳዲስ ሃይል በመጨመር ትህንግ ከክልሉ ወጥቶ እንዳይበተን ዝግጅት መደረጉን ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል። መንግስት አሁናዊ አቋሙንና ዝግጅቱን ስለሚረዳ ሙሉ ማጥቃት መጀመሩን የሚናገሩ ደግሞ ጥንቃቄ መልካም ቢሆንም ትህነግ የሚፈራ አቋም እንደሌለው ማወቅ እንደሚያስፈልግ ያሳስባሉ።

በመጀመሪያው የሰው ማዕበል ከወራራቸው የአማራና የፋር አብዛኛ ስፍራዎች ኪሳራ ደርሶበት የተባረረው ትህነግ ዛሬ ከመቀለ ሰራዊት ሲያጓጉዝ እንደነበር መረጃዎች ተሰምተዋል። ለትንቃቄ እንዲሆን በትግርኛ በተካሄዱ ስትራቴጅ ነደፋ ስብሰባዎች ሰርገው የገቡም መረጃ እያካፈሉ ነው ይህን ይመልከቱ።

የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድንና- የሳይበር ውይይታቸው

አቻምየለህ ታምሩ “ከፋሽስት ወያኔ መንደር የተገኘ መረጃ” ሲል የሚከተለውን አስፍሯል።

1) ፋሽስት ወያኔ ሌላ ዙር ፍጅት እንዲፈጽሙና ኢትዮጵያን እስከወዲያኛው እንዲያፈርሱ በገፍ ያሰለጠናቸውን አዲስ አንበጣ ሠራዊቶቹን በሁሉም አቅጣጫ አንድ ጊዜ በማሰማራት ድንገተኛና መብረቃዊ ያለውን ማዕበላዊ ጥቃት ለመፈጸም አዲስ እቅድ ማውጣቱን ለእድምተኞቹ አስታውቋል፤

2) ሾልኮ ከወጣውና በትግርኛ ከተላለፈው ሚስጥራዊ መልዕክት ለማወቅ እንደቻልነው ፋሽስት ወያኔ ድንገተኛ ያለውን አዲስ ጥቃት ለመሰንዘር ያቀደው በአገር ውስጥና በውጪ አገር የሚኖሩት እድምተኞች ወራሪ አንበጣ ሠራዊታቸው ከሰሞኑ በተለያዩ ግንባሮች ባጋጠመው መከላከል እንዳይሆኑት ሆኖ አፈር ድሜ በመጋጡ ”ያለምንም ጥቅም ልጆቻችን አስፈጃችሁብን” የሚል መካረር በመካከላቸው በመፈጠሩ ይህንን መካረር ለማርገብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፤

3) ስለዚህ ወገኔ ሆይ የድል ጥይት መተኮስን እና መሸላለሙን ትተህ የተሳሳተውን አርመህ፣ ጉድፍህን ጠርገህ፣ አንድነትህን አጠንክረህ የጎደለውን በመሙላት፤ የላላውን በማጥበቅ፤ የተኙትን በመቀስቀስና የነቁትን ይዞህ ለወደፊት ለመሮጥ አደረጃጀትህ ከመቼውም ጊዜ አጠናክረህ አዲስ ጥቃት ለመሰንዘር እየመጣብህ ያለውን ጠላትህን በተጠንቀቅ ጠብቅ፤ ዝግጅትህን አስተካክል! ሒሳብ ሊያወራርድና አገርህን ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን ለመውረድ የተማማለው ወራሪ አንበጣ ሠራዊት የጎደለውን በመሙላት ባዲስ የወረራና የፍጅት እቅዱ ለመመለስ ቁርጥ አድርጓልና የገባ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት እንዳይወጣ አድርገህ ቀጥተህ ወደናፈቀው ሲዖል ለማውረድ በሚገባ ተዘጋጅ።

መረጃውን ለጥንቃቄ መጠቀም እንጂ ከዛ የዘለለ ፍርሃቻ አግባብ እንዳልሆነ የሚጠቅሱ ምሁራን ደጋግመው የሚሉት ሕዝብ አንድ መሆኑን ነው። ሕዝብ አንድ ሆኖ በነመሳቱ በደጀን፣ በሎጂስቲክ፣ በሃይልና ጫናን በምቋቋም ከትህነግ ጋር ሊወዳደር ስለማይችል አሁን በተያዘው ፍጥነት ማጣደፍ እንደሚገባ ነው። በሌላ በኩል ትህነግ የመደራደሪያ አቅሙን ለማስፋት እንደሚንቀሳቀስ መገመት እንደሚገባ ተመልክቷል።

ትህነግ ቅድመ ሁኔታውን በሙሉ አስወግዶ ድርድር እንዲደረግ በሚጠይቅበት በአሁን ወቅት፣ የጀርመን ሬዲዮ ባሰራጨው የእንወያይበት ክፍለ ጊዜ ቅድመ ሁኔታ እንዳለ በማስመሰል ጠያቂዎቹ ሲወተውቱ መስማት ትህነግ ምን ያህል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻው ላይ ለመመልስ እየተጋ መሆኑን እንደሆነ ያመለከቱ” በዚህ ቅስቀሳ የሚበረግግ ሳይሆን ይበልጥ ሃይላና ጉልበት የሚያሰልፍ አደረጃጀት ላይ ማተኮር ግድ ነው” ብለዋል።

Exit mobile version