Site icon ETHIO12.COM

ሃይሌ “ትህነግ በጦር ወንጀለኛነት መጠየቅ አለበት” – አብይ አሕመድ ቤታቸው ተመለሱ

አጫጭር ዜናዎች

“ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታል ማውደም በጦር ወንጀልኝነት መታየት አለበት”፡- አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

አሸባሪው ሕወሃት “ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እጅግ አስነዋሪና በጦር ወንጀለኝነት መታየት ያለበት ድርጊት ነው” ሲል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናገረ፡፡“ማን ከማን ጋር እንኳ እንደተጋጩ የማያውቁ ህጻናትን ትምህርት ቤት ማውደም በምን ይገላጻል?” በማለት ነው በምሬት የጠየቀው፡፡

አትሌቱ በአማራ ክልል በዋግ ኸምራ ዞን ፃግብጂ ወረዳ በዳስ ጥላ ለሚማሩ ህጻናት ያስገነባው ትምህርት ቤት በመውደሙ እጅግ እንዳዘነም ነው የገለጸው፡፡አትሌት ሻለቃ ሃይለ ገብረስላሴ ለኢዜአ እንደገለጸው ትምህርት ቤቱን ለመገንባት ከገንዘብ ወጪ በላይ በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈ የሚገልጸው አትሌቱ፤ የትምህርት ቤቱ መውደም በአካባቢው ማህበረሰብ ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ ይቆጠራል ነው ያለው፡፡

አትሌቱ ያስገነባውን ጨምሮ በአካባቢው በርካታ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች መውደማቸውን ጠቅሶ፤ ይህም የአሸባሪው ህወሃትን “የክፋት ጥግ ያሳያል” በማለት አስረድቷል፡፡በየትኛውም ዓለም በሚካሄዱ ጦርነቶች ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎችን ዒላማ ማድረግ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑንም አትሌት ሻለቃ ሃይለ ገብረስላሴ ተናግሯል፡፡ትምህርት ቤቱም ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ህጻናት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ከሳዑዲ አረቢያ 454 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

ከሳዑዲ አረቢያ፣ ጂዳ 137 ህጻናትን ጨምሮ 454 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢፕድ

የጃፓን አምባሳደር አድናቆት ለገሱ

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ኢትዮጵያ የገጠማትን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት እናደንቃለን ብለዋል።ኢትዮጵያ ጃፓንን ጨምሮ ከሌሎች አገሮች ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ግዜ እየዳበረ መምጣቱም የሚደነቅ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የጀመረችው የልማት ጉዞ በፈጣን ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።የአገርን ሉአላዊነት የማስከበር ሂደቱ ከገጠማት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ መሆኑን ተገንዝበናል ሲሉም አምባሳደሯ ገልጸዋል።

የተለያዩ ችግሮች በማደግ ላይ ያሉም ሆነ ያደጉት አገራትን ሊያጋጥም እንደሚችል ጠቅሰው፤ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና ታልፈዋለች ብለዋል።አምባሳደሯ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የልማት፣ የፍቅርና አንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንመግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ እና ጋና በሁለትዮሽና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ጋና በሁለትዮሽና የጋራ ትኩረት በሆኑ የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በቅርበት እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእሳቸውና ለልዑካቸው በአክራ በሚገኘው ቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስላደረጉት ውይይት ለፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አዶ አድናቆቴ ይድረሳቸው በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰፍረዋል።ኢትዮጵያ እና ጋና በሁለትዮሽ እና የጋራ ትኩረት በሆኑ የአፍሪካ ጉዳዮች አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ገልሰዋል። የዳካርና አክራ የስራ ጉብኘታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

Exit mobile version