ETHIO12.COM

የባህር ዳር ወጣቶች የአገር መከላከያን እየተቀላቀሉ ነው

የባህር ዳር ወጣቶች የህልውና ዘመቻ ጥሪን በመቀበል የአገር መከላከያን ለመቀላቀል እየጎረፉ መሆኑንን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አመልክቷል። በምስል እንደሚታየው ጥሪውን የተቀበሉትና ጀግናው የአገር መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑት ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ ነው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ መዋጋት የሚችሉትንም ሆነ እድሜያቸው የማይፈቅደውን በማስለፍ ሰፊ ሃይል ይዞ ወደ ጦር ሜዳ እንደሚገባ፣ ሰፊ ምልምል በማሰማራት በተለመሳሳይ ሰዓትና ጊዜ ሰፊ ወረራ እንደሚፈጽም በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። የሰው ማዕበል በማጉረፍ ወረራ እንደሚፈጽም በማስታወቅ አማራ ክልል ክተት ማወጁም ይታወሳል። የአማራ ክልል ከተት ካወጀና ህዝብን ማደራጀት ከቻለ በሁዋላ ከመከላከያ፣ ልዩ ሃይልና ፋኖ ጋር በመቀናጀት፣ ሚሊሻና ወጣቶችን በማሳተፍ ሰሜንና ደቡብ ጎንደርን ነጻ ሊያወጣ መቻሉን ማስታወቁም አይዘነጋም።

ትህነግ አሁን ላይ ሃይሉን አስተባብሮ በማይጸብሪና ደቡብ ወሎ ግንባር ወረራውን አጠናክሮ መቀጠሉ፣ ዘረፋ፣ ንብርት ማውደምና ከዘረፋ የተረፉ መሰረተ ልማቶችን ማፈራርስ ላይ በመሰማራቱ ይህን ሃይል እስከመጨረሻ ለማስወገድ በቂ ሃይል እንደሚያስፈልግ፣ ዘም ከተባለ ሲያሻው ሁል ጊዜ ንጽሃንን እንደሚገድል፣ እንደሚያሰቃይና የአገር ሃብት ከማውደም ወደሁዋላ እንደማይል በመጥቀስ ነበር ወጣቱ የመከላከያ ሃይልን እንዲቀላቀል ጥሪ የቀረበው።

ይህንኑ ጥሪ ተከትሎ የከተማዋ የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ” ለአባልነት የተመዘገቡ እጩ ሰልጣኞች በባህርዳር ከተማ ደረጃ ምልመላ እና ማጣሪያ ተደርጎላቸው ወደ ስልጠና ቦታ ሊላኩ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል” ብሏል።

READ MORE STORIES

Exit mobile version