Site icon ETHIO12.COM

ጀነራል አበባው ሰሜን ወሎ መከሩ ፤❝ዝግጅቱ ለሚጋልቧቸውና ገዢዎቻቸው ነው❞ ሌ.ጄ ባጫ

“አልመለስም” ብለው ነበር እዛው ኤርትራ ድንበር ከተበተነው ሰራዊት ጋር የቀሩት። በአየር ሄደው ቀድሞ ከሚያውቁት ሰራዊት ጋር ሲቀላቀሉ ባዩት የግፍ ጥግ “አነቡ” እልህ ውስጣቸውን አንድዶት ያለ አንዳች ማወላዳት ” አልመለስም” ሲሉ በሴራ እንዲለዩት ከተደረገው ሰራዊት ጋር ተቀላቀሉ። አበባ!!

ብዙ መናገር እንደማይወዱ የሚነገርላቸው ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አበባው፣ ባልደረባቸው የነበሩት ጀነራል ሰዓረ ሲያልፉ ” ኢትዮጵያዊ ስለሆነ፣ ኢትዮጵያን ስለወደደ ብቻ … ” ሲሉ አገዳደሉን ያመለከቱ ዕለት ይታይባቸው የነበረው ዕልህ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ነበር።

ኤታማዦር ሹም እንዳይሆኑ በሚል ሂሳብ ከመከላከያ የተሰናበቱት ጀነራል አበባው፣ መከላከያ ላይ ክህደት ከተፈጸመ በሁዋላ በርካታ አኩሪ ተግባራትን በአመራር ሰጪነት ከባልደረቦቻቸው ጋር ማከናወናቸውን በአውድ የሚያውቋቸው ይመሰክሩላቸዋል።

እኙን ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሰሜን ወሎ ግንባር ተገኝተው የጦር መኮንኖቻቸውን በመሰብሰብ መንፈሳቸውን እንዳካፈሏቸው፣ ልባቸውን እንደሞሉላቸው፣ ጉልበታቸውን እንዳደሱላቸውና ሰለ ቀጣዩ ” ጸረ ማጥቃት” እንዳማከሯቸው ታውቋል።

የአገር መከላከያ የማህበራዊ ገጽ እንዳለው ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሰሜን ወሎ ግምባር ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ መክረዋል። ለምንም የማይበገረው ሠራዊታችን ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት ለህይወቱ ሳይሳሳ በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን ክብር እንደሚሰጡትና እንደሚያደንቁት አስረድተዋል።

ሠራዊታችን በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ሀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። ጀነራል አበባው ለትግራይ ወጣቶችና ሚሊሻ አባላት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በተሰጠበት ማግስት ስለ ቀጣይ ግዳጅ አፈጻጸም ለመምከር ሰሜን ወሎ መግባታቸው ትርጉም እንዳለው ተጠቁሟል።

የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ፣ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ሀይል አንገት እያስደፋ የወረራቸውን አንዳንድ ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን አለቃቸው ፊት ተናግረዋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በህዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማህበረሰባችን ወደ ቀየው እንዲመለስ ለማድረግ ግምባር ላይ ያለው ሀይላችን የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው ብለዋል።ተቋሙም በአሁኑ ሰዓት ብቁ ሠራዊት በመገንባት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁንም ተናግረዋል።

ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ሰሜን ወሎ ግንባር ተገኝተው የመከሩት ምክትል ኤታማዦር ሹም አበባው፣ ሃይሉን አጠናክሮ ለሙሉ ኦፕሬሽን የተዘጋጀውን ጦር አመራሮች በሚያናግሩበት ወቅት የቡልቡላ ወታደራዊ ማሰለጠኛ ተቋም አዳዳዲስ ምልምሎችን አስመርቋል። በዚሁ የምረቃ ሰነ ስርዓት ላይ እንደተጠቆመው ኢትዮጵያ እየተዘጋጀች ያለችው ለትህነግ አይደለም። ይልቁኑም ትህነግን ለሚጋልቡት መሆኑ ነው የተጠቆመው።


READ MORE STORIES


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገው የሠራዊት ግንባታ ሂደት ዓላማው አሸባሪው ሕወሓትን ማሸነፍ እንዳልሆነና ይልቁንም ዝግጅቱ እነሡን ለሚጋልቧቸው ኀይሎች እንደሆነ ያስታወቁት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ናቸው። የቡልቡላ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮች የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው የተመረቁት።

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ባደረጉት ንግግር፤ ❝የእኛ ዝግጅት ለጁንታው አይደለም፤ ይልቁንም እነሱን ለሚጋልቧቸው ገዢዎቻቸው ነው❞ ብለዋል፡፡ሌተናል ጄነራል ባጫ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደምም መሰል ችግሮች ሲያጋጥሟት እንደነበር ገልጸው፤ በእነዚህ ጊዜያት ግን ባንዳዎች ሀገርን በማስጠቃት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው አስታውሰዋል።

በሁለቱም የጣሊያን ወረራዎች ወቅት ባንዶች ሀገርን በመውጋት ድርሻቸው ብዙ እንደነበር የተናገሩት ሌተናል ጄነራሉ፤ በሶማሌ ወረራ ወቅትም የዛሬው አሸባሪ ሕወሓት የሶማሌን ወረራ ከማውገዝ ይልቅ ለጠላት ወግኖ ነበር ብለዋል፡፡ሀገርን ማዳን የሚቻለው በቅብብል ነው ያሉት ሌተናል ጄነራል ባጫ፤ ይህ ትውልድም ባንዳውን ሕወሓትን ማስወገድ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በዚህ ጦርነት ላይ ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ዓላማ አላት ያሉት ሌተናል ጄነራል ባጫ፤ ❝ሀገራችንን አታፍርሱ የሚል ፍትሐዊ ዓላማ የተቀበለ 110 ሚሊየን ሕዝብ አለን፤ ድሆች ብንሆንም የሎጀስቲክ ምንጭ የሆነ ሕዝብ አለን❞ ሲሉ ተናግረዋል።❝ተመራቂዎች ድል አድራጊ የሆነውን ሠራዊት ተቀላቅላችሁ በቅርቡ ድል እንደምታበስሩ ተስፋ አለኝ❞ ብለዋል፡፡

የፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ መልዕክት ! ” ወድቃችሁ ስለምታቆሙን፣ ሙታችሁ ስለምታኖሩን ፣ ስግብግብነት እና ሌብነት በነገሱበት ዘመን ራሳችሁን አሳልፋችሁ ስለምትሰጡ፣ ሆዳሞች ከድሀ ሲቆርሱ በበረሀ በረሀብና ጥም የሁላችንም ደጀን ስለምትሆኑ ፣ እኔ ካልበላሁት ጭሬ ልበትነው ባዩ በበዛበት ሀገሬ ካንቺ በፊት እኛን ያስቀድመን ስላላችሁ፣ በጎጥ እና በመንደር ከፋፍለው ሊያባሉን ሲተጉ በኢትዮጵያዊነት ተሰባስባችሁ በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር አንዲት እናታችሁን ስለምትጠብቁ፣ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ከነፍሳችሁ አስበልጣችሁ ስለወደዳችሁ እናመሰግናችኋለን እናከብራችኋለን ። “ምንጭ : ፕሬስ ድርጅት

Exit mobile version