Site icon ETHIO12.COM

ከ466 ዕርዳታ ጭነው መቀለ ካመሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ትህነግ የለቀቃቸው 38 ብቻ መሆናቸው በተመድ ይፋ ሆነ

የዕርዳታ እህል ለማድረስ ወደ መቀሌ ከተላኩት የጭነት ተሽከርካሪዎች አብዛኞቹ እንዳልተመለሱ የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቢሮ አስታውቋል። ድርጅቱ ይህን ባስታወቀበት ቅጽበት የነጋገርናቸው እንዳሉት የጭነት ተሽከረካሪዎቹ ወደ ትግራይ ሲጓዙ የደርሶ መልስ ነዳጅ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱና የነዳጅ ችግር እንደማይገጥማቸው አመልክተዋል።

ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቢሮ በቲውተር ገጹ እንዳመለከተው እስካሁን ወደ ትግራይ ዕርዳታ ቀለብ ጭነው ከተጓዙእት 466 የጭነት መኪኖች ውስጥ ወደ መሃል አገር የተመለሱት38 ብቻ ናቸው።

በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል የዕርዳታ ዕህል እንዲያደርሱ እስካሁን466 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ ቀለብ አራግፈው የተመለሱት 38 ብቻ መሆናቸው በስራው ላይ እክል እንደሚሆነበት አመልክቷል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ወደ ትግራይ ካቀኑት ሳምንት 149 ተሽከርካሪዎችን 428 የጭነት መኪኖች ሳይመለሱ መቅረታቸውን ያመለከተው የተባበሩት መንግስታት የአዲስ አበባ ቢሮ፣ የተሽከርካሪዎቹ አለመመለስ ዕርዳታ ለተጎጂዎች የማድረስ ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገበትም ይፋ ተናግሯል። ይሁን እንጂ አላወገዘም ወይም ድርጊቱን በምን መልኩ እንደሚያየው አላስታወቀም።

ያነጋገርናቸው የእርዳታ ዕህል ስርጭት ዘርፍ ውስጥ በቅርብ የሚሰሩ እንዳሉት የጭነት መኪኖቹ የጫኑትን አራግፈው ላለለመመለስ ምንም ምክንያት ሊቀርብባቸው እንደማይችል ነው።

ነዳጅ የደርሶ መልስ እንደሚሞሉ፣ ይህም የተለመደ ተግባራቸው እንደሆነ፣ ባይሆንም የትግራይን ወቅታዊ ሁኔታ ስለሚረዱ ተዘጋጅተው እንደሚሄዱ አመልክተዋል። ከዚህ ውጭ የቴክኒክ ችግር ቢያጋጥም እንኳን ከ466 ተሽከርካሪ፣ 428 ሊበላሽ እንደማይችል አስረድተዋል።

የተባበሩት መንግስታት እንዳሳሰበው ጠቅሶ ያሰራጨውን መረጃ ተከትሎ አዲስ ዘመን “አሸባሪው ህወሓት ተሽከርካሪዎችን በመውሰድ ለጥፋት ተግባሩ መፈፀሚያ እያዋላቸው እንደሆነ የሚያሳዪ መረጃዎች ከሳምንታት በፊት ሲወጡ ነበር” ብሏል። ካልፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ ትህነግ ለርዳታ የሚሄዱ ከባድ መኪኖችን ለወታደራዊ ተግባር እንደሚጠቀምባቸው ሲገለጽ ነበር።

የተባበሩት መንግስታት ይፋ ላደረገው መረጃ ትህነግ በይፋ የሰጠው ምላሽ ይህ እስከታተመ ድረስ አልተሰማም።

Exit mobile version