Site icon ETHIO12.COM

” ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት አለን ” ሜ/ጀ ይልማ

በኢትዮጵያ አየር ኃይል የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑና የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው ከፍተኛ መኮንኖች ፣ መስመራዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርዓት ተከናወኗል ።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ይልማ መረዳሳ ፣ አየር ኃይል ከተቋማዊ ሪፎርሙ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመጥን ተቋም ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ፣ በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻውም አስደናቂ ገድሎችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት አለን ያሉት ዋና አዛዡ ፣ በቀጣይም ሀገራችንን የሚዳፈር ማንኛውም ኃይል ላይ አስተማሪ ቅጣት በመስጠት ተልዕኳችንን በብቃት ለመወጣት የዕለቱ ተሿሚዎች የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ብ/ጄ ይታያል ገላው በበኩላቸው ፣ በውስጥና በውጭ ኃይሎች የተደቀኑብንን ፈተናዎች በፅናት በማለፍ በአዲስ ዓመት የሽብርተኛውን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ህዝባችንን ደጀን አድረገን የህልውና ዘመቻ የምናደርግበት ወቅት በመሆኑ የማዕረግ ሹመቱ ልዩ ነው ብለዋል።

በዕለቱ ከሰራዊቱ አባላት በተጨማሪ የተሿሚ ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን ፣ የአየር ኃይል ኦርኬስትራም ለመድረኩ ድምቀት የሆኑ ሀገራዊ ዜማዎችን አቅርቧል።

ይታያል ምህረት
ፎቶግራፍ ጌታቸው አበራ

Exit mobile version