Site icon ETHIO12.COM

የWHO ሰራተኞች በወሲባዊ ብዝበዛ ላይ መሳተፋቸው ተረጋገጠ

አንድ በገለልተኛ ኮሚሽን የተዘጋጀ ሪፖርት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተቀስቅሶ የነበረውን የኢቦላ ወረርሽኝን ለመግታት ተሰማርተው በሴቶችና በልጃገረዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ካደረሱ 83 የእርዳታ ሠራተኞች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች እንደሚገኙበት ማመልከቱን ቢቢሲ ዘገበ።

9 የአስገድዶ መድፈር ክሶችን ያካተተው ይህ በደል እአአ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ የደረሰ ሲሆን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ሠራተኞች የተፈጸመ ነው።

ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ከ50 በላይ የአካባቢው ሴቶች የወሲብ ጥቃት እንደተፈጸማቸውን ሪፖርት ካደረጉ በኋላ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን “ይቅርታ የማያሰጥ” ሲሉ ገልጸውታል።

ባለ 35 ገጹ ይህ ሪፖርት ምርመራ ከተደረገ በኋላ በገለልተኛ ኮሚሽን የተዘጋጀ ነው።

ሥራ ለማግኘት በልዋጩ ወሲብ እንዲፈፅሙ እንደተገደዱ የገለጹ በርካታ ሴቶችን ቃለ መጠይቅ ያደረገው ኮሚሽኑ ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት 83 ሰዎች መካከል 21ዱ በዓለም ጤና ድርጅት ተቀጥረው እንደሚሠሩ አረጋግጧል።

የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን በድርጅቱ ተቀጥረው የሚሠሩ የ4 ሰዎችን ውል ያቋረጠ መሆኑን ገልጾ ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ቃል ገብቷል።

ዶ/ር ቴድሮስ ለተጎጂዎችና ከጥቃቱ ለተረፉት በቀጥታ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ “እናንተን ለማገልገል እና ለመጠበቅ በዓለም ጤና ድርጅት ተቀጥረው በሚሠሩ ሰዎች በደረሰባችሁ ነገር አዝናለሁ። ወንጀለኞቹ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ሳይሆን ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ቀዳሚ ተግባሬ ነው” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-09-29-3

@tikvahethiopia

Exit mobile version