Site icon ETHIO12.COM

ኤርሚያስ «የሤራ ትንታኔ» ለክሱ ዋስትና እንዲያገኝ አደረገው

ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው። ይህ ማለት አማራውን እንዴት አድርጎ መሳል ይሆን?”


“የህወሃት አገልጋይ” በሚል ልዩ መለያው የሚታወቅው፣ በበረከት ስምዖን አስተምህሮ ተቀርጾ የተሠራ የሚባለውና ከዚሁ ፈጣሪው ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንደነበረው በርካታ መረጃ የሚቀርብበት ኤርሚያስ ለገሠ፤ በአበበ ገላው ለተከፈተበት “የስም ማጥፋትና ሃሰተኛ ዘገባ” ክስ ወጪ ለመሸፈን ትህነግ በተዘዋዋሪ እጁን እያስገባ መሆኑ ተሰማ። 

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በዚህ ደረጃ ለኤርሚያስ ወጪ ለመሽፈን የወሰነው በነበራቸው ግንኙነት መነሻ ብቻ ሳይሆን በቀጣይም አገልግሎቱን “በሚወርድ መደብ” መሠረት ለመቀጠል በመስማማት ነው።

“ስም በማጥፋትና የሃሰት መረጃዎችን በማውጣት” በሚል ጭብጥ አበበ ገላው ኤርሚያስ ለገሠ ላይ ክስ መመሥረቱን ተከትሎ ኤርሚያስ የግል ንብረቱ ባደረገው የ360 ዩትዩብ በገሃድ ጭንቀቱንና ፍርሃቱ ሲያሰማ ቆይቷል። በተለይ በክሱ እንደተመለከተው አበበ የጠየቀው የጉዳት ካሣ ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በመሆኑ ከብያኔ በፊት ስምምነት ይደረግ (ሴትልመንት ይሁን) ቢባል እንኳ የሚከፍለው ካሣ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠር እንደሚሆን አስተያየት የሰጡ የህግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

የዚህን ክስ ጉዳይ በተመለከተ ብሩክ ይባስ የሚባለው የ360ና የኤርሚያስ ባለሟል፣ በራሱ ስም የጎፈንድሚ አካውንት ከፍቶ ብር እየሰበሰበለት ይገኛል። አንዳንድ የታክስ ባለሙያዎች እንደሚሉት ብሩክ ለራሱ ጥቅም የማይውል ገንዘብ መሰብሰቡ ዓመቱ መጨረሻ ላይ በአገር ውስጥ ገቢ (IRS) በግብር ጉዳይ የሚጠየቅበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ኤርሚያስ ይህንን አስቀድሞ በመገመት (በማወቅ) በራሱ ስም መሰብሰብ የሚገባውን “ራስን ማዳን” በሚባለው ሥሌት ብሩን በብሩክ ይባስ ስም መሰብሰብን መርጦ ሊሆን እንደሚችል የቀድሞ ተሞክሮውን የሚያውቁ ጠቁመዋል።

ኤርሚያስ የገንዘብ ማሰባሰቡ ከመጀመሩ በፊት የተከፈተበት ክስ እጅግ ያስፈራው በመሆኑ እሸነፋለሁ፤ እስር ቤት እወርዳለሁ በማት እንዲሁም የአሜሪካ እስር ቤቶች በአብዛኛው ወንዱ ተበላሽቶና ወንድነቱ አጥቶ የሚወጣበት በመሆኑ ይህንንም በመፍራት ይመስላል ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነበር። እንዲያውም በኑዛዜ መልክ “በዚህ ክስ በእኔ ንዝህላልነት ከተሸነፍኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ 950ሺህ ዶላሩን እንደሚከፍልልኝ አልጠራጠርም” ሲል ተሰምቶ ነበር።   

ኑዛዜውን ተከትሎ የገንዘብ ማሰባሰቡ ከተጀመረ በኋላ የመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የትህነግ ሰዎች ለኤርሚያስ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ነው። ኤርሚያስ ልክ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ አሁንም ተቃዋሚና ተንታኝ በመምሰል የትህነግን ዓላማ በፕሮፓጋንዳ መንዛቱን እስከቀጠለ ድረስ ይህንን ብቻ ሳይሆን የወደፊቱንም ወጪ እንደሚሸፍኑ ቃለ መግባታቸውን የጎልጉል የአሜሪካ ተባባሪ ዘጋቢ አመልክቷል። ይህ ዋስትና የተሰጠው ኤርሚያስም ከቀፈደደው ፍርሃት በመውጣት “በውል ሰነዱ” መሠረት ትህነግ የሰጠውን የቤት ሥራ በብቃትና በቅልጥፍና መወጣት መጀመሩ በመረጋገጡ ነው። ለዚሁም ታማኝነቱን ለማጉላት፣ ቁርጠኛነቱን ለማጽናት በቀዳሚነት ሰለባ ያደረገውም ትህነግ “ሒሳብ አወራርድበታለሁ” ያለውን የአማራ ሕዝብ ነው። 

በማይድን በሽታ ተቀስፎ የነበረውን መለስ ዜናዊ በዓለም አደባባይ በማዋረድ ሞቱን ያፋጠነውን አበበ ገላው ትህነጎች፣ ደጋፊዎቻቸውና አገልጋዮቻቸው በሙሉ እጅግ እንደሚጠሉት ይታወቃል። በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሊበቀሉት፣ ሒሳብ ሊያወራርዱ እንደሚፈልጉ ከዚህ በፊት የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሁሉም ሳይሳካ የለውጥ ማዕበል ገፍቶ መቀሌ ያደረሰው ትህነግ አበበ ላይ ጥርሱን እንደነከሰ ባለበት ሰዓት ነው ኤርሚያስ ጩኸቱን ያሰማው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪዎች በሥልጣን ባሉበት ወቅት ከዛቻ የዘለለ ምንም ሊያደርጉ ባለመቻላቸው ዛሬ ይህንኑ የቆየ ምኞታቸውን ለማሳካት አሁን ኤርሚያስን በመደገፍ የበቀል በትራቸውን ለመሠንዘር መዘጋጀታቸውን ነው ዘጋቢያችን ያመለከተው። አንዱና አመቺ ሆኖ ያገኙት ደግሞ በዲጂታል ወያኔነት ሲያገለግላቸው የነበረውን ኤርሚያስ ለገሠን በገንዘብ በመደጎም ነው። ኤርሚያስም “እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል” በሚለው መርህ እንደሚንቀሳቀሰው ዲጂታል ወያኔ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ነጥሎ መምታት ዋና ተግባሩ እንዳደረገ በየቀኑ የሚያቀርበው ፕሮግራም ህያው ምስክር ነው።

“አዲስ የሚመሠረተውን መንግሥት ኢሕጋዊ ነው” ማለት፣ አማራ የተረጋጋ ክልል ሆኖ እንዳይቀጥል ፕሮፓጋንዳ መዝራትና በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ የትህነግን ወንበዴ ሽፍታ ማንነት ማግነን፣ ቀጣዩ የ“ሤራ ትንታኔ” አጀንዳው አድርጎ  ኤርሚያስ እየሠራ ያለውም በዚሁ በተገባለት ዋስትናና እሱም በገባው የመታመን ቃል ኪዳን እንደሆነ ከትህነግ ሰዎች ቅርብ ከሆኑ መስማቱን ገልጾ ዘጋቢያችን ያስረዳል።

በፍጥነት፣ በተመረጡና በተለያ አማራውንና የአማራን ማኅበረሰብ ማዕከል አድርጎ ወደ ሥራ የገባው ኤርሚያስ፣ በትህነግ ጭፍሮች ወረራ ሰላም በሚኖርበት ምድሩ ላይ በሞት፣ በዝርፊያ፣ በጅምላ ጭፍጨፋ፣ በስደት፣ በመፈናቀልና በረሃብ መሰቃየቱ ሳያንሰው፣ ኤርሚያስ ከጥቂት ቀናት በፊት (መስከረም 14/ሴፕቴምበር 24) ፕሮፓጋንዳውን በሚረጭበት ብቸኛው ሚዲያ “የአማራ ብልጽግና መንግሥት መመሥረት ይችላልን?” በሚል ርዕስ የአማራን ሕዝብ ሲያዋርድ መዋሉ ለዓላማቸው ለቀጠሩት ጮቤ ሲያስረግጥ በርካቶችን ግን ክፉኛ አስቆጥቷል።

የባለቤቶቹ አቋም ምን እንደሆነ በግልጽ በማይታወቅውና ጸረ መንግሥት፣ ጸረ ሕዝብና ጸረ ኢትዮጵያ ሃሳቦች በትጋት ያለማሰለስ ከሚያስተላልፈው የመረጃ ቲቪ ጋር ቁርኝት ያለው የኤርሚያስ 360 ከላይ በተጠቀሰው ቀን የአማራ ክልል እንዳይረጋጋ የሚያደርግ “የሤራ ትንታኔ” ሲሰጥ ነበር። ኤርሚያስ ከተናገራቸው ውስጥ ሁለቱ የሚከተሉት ይገኙበታል፤ አንደኛው፤ መንግሥት ከተመሠረተ በኋላ የአማራ ሕዝብ የትግል ማዕከሌ ነው ያለውን ጉዳይ (የወልቃይትን ማለቱ ነው) በብልጽግና ተወስኗል ወይም የሆነ የጦርነት ሳቦታዥ (ሰንካላ ምክንያት) ተፈጥሮ ለቅቆ ይወጣል፤ “ማርክ ማይ ወርድ ለዚህ ንግግሬ ሪስክ እወስዳለሁ” በማለት ለብሩክና ከአፉ ለሚለቅሙት በሥልጣን ተናግሯል።

የጎፈንድሚው ቋት በፍጥነት በትህነግ እየሞላ ሲሄድ ኤርሚያስ የተናገረው የአማራን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ ያዋረደና የናቀ ነው። በቤተ እምነት ውስጥ ከመመገብ ጀምሮ እስከ መጸዳዳት የረከሰ ተግባር የፈጸመውን፣ እርጉዝ አስገድዶ የደፈረውን፣ አዛውንትን አንገላትቶ የገደለውን፣ ከአስር ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ለመድፈር ብሎ አልቻል ሲለው በጠርሙስ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በደቦ የደፈረውን፣ የካህናትን ሚስት ካህኑ ፊት የደፈረና የገደለውን፣ እንስሳትን ከነህይወታቸው የበለተውን፣ መብላት ያቃተውን እንስሳት የረሸነውን፣ ማሳ ላይ ያለ ሰብል ማቃጠል ሲያቅተው ረጋግጦ ቡቃያ ያወደመውን፣ የጎተራ እህል በአይጥ እንዲወድም ድመቶችን የፈጀውን፣ የዱር አውሬ የቤት እንስሳትን እንዲበላ ውሾችን እያሳደደ በጥይት የደፋውን፣ ቦሃቃ ከፍቶ ሊጥ የጠጣውን፣ ከበዓል ተርፎ የተቀመጠ ድፍድፍ እንደ ከብት የተጋተውን፣ የትህነግ ጭፍራ ምሳሌ አድርጎ አማራውም ይህንን የአደረጃጀት ሞዴል መከተል አለበት ብሏል።

ይህ በሰው አእምሮ ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ባለፉት ጥቂት ወራት የፈጸመውን፤ ከዘረፋ የተረፈ መሠረተ ልማት፣ ሆስፒታል፣ ክሊኒክ፣ ትምህርት ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ያወደመውን፤ ሙሉ ቤተስብ የጨረሰውን፣ አቅመ ደካሞች ሳይመርጥ ችጋሩን ያራገፈ፣ ሙሉ ከተማ ያወደመ፣ “እኔ ካልበላሁ ጭሬ እደፋለሁ” በሚል ስሌት የተገነባ፣ በደም የተለወሰና በንጹሃን ነፍስ የሚጠይቅ የትህነግ አረመኔ ሽፍታ ስብስብን ነው ኤርሚያስ “እንደ ሞዴል፣ እንደ ምሳሌ ሊወሰድ ይገባዋል” በማለት ሲያውጅ የነበረው በሚል በርካታ ማሳያዎችን በመዘርዘር ኤርሚያስ በበላውና ቃል በተገባለት ልክ አማራው ላይ መዝመቱን የተቆጡ ያስታውቃሉ። ይህንን እኩይ “ምክር” የሰጠው ደግሞ ለአማራ ሕዝብ መሆኑ ኤርሚያስ ለማን እንደሚሠራ በግልጽ የሚመሰክር እንደሆነ ያመለክታሉ።

ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው።   

ኤርሚያስ “ሕዝባዊ” ሲል ያሞካሸው ሊጥ የሚሰርቅ ጭፍራ መሆኑ ባደባባይ እየታየ፣ ባልን ገድሎ ሚስትን እንዳታለቅስ ከልክሎ ከአስከሬን ጋር ለቀናት የሚያሳድር ሰብዓዊነት ጭራሽ ያልዘራበት ልክ እንደ ራሱ ሁሉ በእነ በረከት አምሳልና መለስ ጣዕረ ሞት ዓምድ የተዋቀረውን የደም መጣጮች ስብሰብ መሆኑንን በመጥቀስ የተቆጡ የራሳቸውንም ወገኖች ዘልፈዋል።

በዚህ የኤርሚያስ ንግግር እጅግ የተበሳጩ እንደሚሉት በዚህ ደረጃ ለሚያዋርዳቸው የትህነግ አፈቀላጤ “አማራ ነን” የሚሉ ከአስተያየት ጀምሮ የሚያደርጉት ድጋፍና ዕርዳታ እጅግ አሳፋሪና ወራዳ የሚያስብል መሆኑንን ያስታወቁት በቁጭት ነው። የአማራን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ “የሊጥ ሌባ” ሆኖ በትህነግን ጭፍራ ልክ እንዲደራጅ ኤርሚያስ “ቤስት ፕራክቲስ ነው” ብሎ ሃሳብ ሲያቀርብ እንዴት ኃይላችንን እንደናቀ መገንዘብ የማይችሉ ሁሉ ጤናቸውን መላ ሊሉ እንደሚገባ አስተያየት የሰጡ አመልክተዋል።

ኤርሚያስ የትህነግን ጭፍራ ለአማራው ሞዴል አድርጎ ባቀረበበት ሁኔታ ከውጪ ለትህነግ የሚዋደቁት እንደ ኖርዌጂያኑ ሼትል ትሮንቮል ዓይነቱ የስም ፕሮፌሰር ደግሞ ትህነግን በሌላ መልክ ለመቅረጽ እየታተሩ ናቸው። በተቀናጀ ሁኔታ እየተናበቡ የሚሠሩት የውጪዎቹ ሤረኞችና አገር በቀል ተቀጣሪዎች አጀንዳ ሲያስቀምጡ እንደ ትህነግ በመስመር ነው። 

ወራሪውን የትግራይ ሽፍታ “ቲዲኤፍ” ተብሎ እንዲጠራ የሰየመው ትሮንቮል፤ አሁን ደግሞ በትግራይ ምንም ዓይነት ነገር የለም ቲዲኤፍ ብቻ ነው ያለው ማለቱ፤ ኤርሚያስ የአማራው ኃይል በትግራዩ ሽፍታ ልክ እንዲቀረጽ መናገሩ፤ የመናበብ ውጤት መሆኑን በግልጽ እንደሚያሳይ ጉዳዩን የሚከታተሉ ይገልጻሉ።

ጎፈንድሚው አስቀድሞ የወጣለት ጣሪያ ወደ መድረስ ሲጠጋ ኤርሚያስ ቁጥሩ ከፍ ከማስደረግ ባለፈ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን የትህነግን አጀንዳ አክርሮታል። የአማራ ብልጽግና ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከፍራንስ24 ጋር ደደረጉትን ቃለምልልስ በመጥቀስ የአማራው ኃይል ድንበሩን መጠበቅ ብቻ ነው ያለበት እንጂ የትግራይን ወሰን ተሻግሮ የማለፍ ማንዴት (ሥልጣን) የለውም ኤርሚያስ ሲል ተደምጧል።

የብልጽግናው ሹም ለፍራንስ24 የተናገሩት “ትህነግን መቀሌ ድረስ ገብተን ሳንቀብር አማራው ኅልውና አያገኝም ይህንንም እንፈጽመዋለን” ነበር ያሉት። ይህ የእርሳቸው ብቻ ሳይሆን የኅልውና አደጋ የተጋረጠበት የእያንዳንዱ አማራ (የገበሬው፣ የከተማ ነዋሪው፣ የፋኖው፣ የሚሊሻው፣ የልዩ ኃይሉ) ፍላጎት እንደሆነ በየሚዲያው ሲሰማ የቆየ ጉዳይ ነው።

የትህነግ ሽፍታ ተከዜን አልፎ ወደ ጎንደር ሲገባ፤ የአፋርን ወሰን አልፎ ጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈጽም፣ ሰሜን ወሎ የአማራን ወሰን አልፎ አውሬነቱን በገሃድ ሲያሳይ ኤርሚያስ ትህነግ ማንዴት እንደሌለው አለመናገሩ ለአማራ ያለውን ሥር የሰደደ ጥላቻ ብቻ ሳይሆን ለትህነግ ምን ያህል ቆርጦ እየሠራ እንደሆነ የሚያመለክት ነው ሲሉ አስተያየት የሰጡ ተናግረዋል። 

ከዚህ ሌላ የአፋር ሠራዊት የትግራይን ወሰን አልፎ ከመቀሌ 30ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ጊዜ የአማራውን ኃይል ነጥሎ ወደ ትግራይ ለመግባት መብት (ማንዴት) የለውም ማለቱ ለአማራ አዛኝ መስሎ ለትህነግ ኅልውና የሚሠራ ለመሆኑ ጉልህ ማስረጃ ነው ተብሏል።           

ኤርሚያስ በቅርብ የሚያውቁትና የሤራ አስተሳሰቡን የተገነዘቡ ትህነግ ሲሞት፣ ሲቀበርና ከኅሊና ሲሰረዝ ሥራ እንዳይፈታ ግብጽ ልትከፍተው ወዳሰበችው የአማርኛ ሬዲዮ አገልግሎት በቅድሚያ ማመልከቻ እንዲያስገባ በመምከር ተሳልቀዋል። 

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Exit mobile version