Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ዓለም “ይድረስልን”አለ፤ ጦርነቱ በሁሉም ግንባር ቀጥሏል፤ ሁለት ወረዳዎች ተለቀቁ

“ጦርነት አማራጭ አይደለም … ከጦርነት የሚገኝ አንድም ነገ “ሕልውናውን ለማረጋገጥ ጦርነቱን ማሸነፍ ግዴታ ነው” ትህነግ

“በሁሉም ግንባሮች ግዙፍ ኃይል ተንቀሳቅሷል” ይላሉ አቶ ጌታቸው። “በየትኛው ግንባር ጥቃት ሊከፍቱ እንደሚችሉ እርግጠኛ አይደለንም” ሲሉ ለሮይተርስ ነግረዋል። ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በርሃኑ ጁላ ስለጦርነቱ መረጃ የሚባል ነገር እንደማይሰጥ አስታውቀዋል። አየር ሃይል ቀድሞውንም ጀምሮ አይተነፍስም። ሊደበቅ የማይችል አንድ ሃቅ አለ። ከፍተኛ የተባለ ጦርነት እየተካሄደ ነው።

በውጭ ቀነ ቀጠሮ አስቀምጠው ኢትዮጵያን ሊያቅቡ የሚያስፈራሩ፣ የተባበሩት መንግስታት ጣልቃ ሰራዊት እንዲገባ የሚጠየቁ ድምጻቸው በሚሰማበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ጦር የመልሶ ማጥቃት መጀመሩን ተከትሎ የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ወደ ሚድያ ተመልሰዋል። በማያወላዳ ቋንቋ በአየር፣ በምድርና በከባድ መሳሪያ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑንን በይፋ ማስታወቃቸውን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዛሬ ማለዳ ላይ አቶ ጌታቸው በአማራ ክልል በሚገኙት ገርገራ፣ ወገል ጤና፣ ወርጌሳ ለማጥቃት የሞከረውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል መክተው ከቀድሞው ይልቅ ተጨማሪ ቦታ መያዛቸውን አስታውቀው ነበር። በስላቅ የማይቻለውን ጉዳይ የመሞከር ያህል እንደሆነ አስመስለው ይህን በገለጹ ቅጽበት ውስጥ መግለጫ አስከትሏል። መግለጫው “የተከፈተብንን ጥቃት የዓለም መንግስታት ያውግዙ” ሲል ጥሪ አቅርቧል። በዚህ ሰዓት ለትግራይ መድረስ እንደሚገባቸውም አመልክቷል።

ይህ መግለጫ በወጣበት ቅጽበት መንግስት ይፋ ባያደርገውም ደህናና አምደውርቅ ከተማ ነጻ መውጣታቸው ታውቋል። በቀጣይም ጥቃቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል።

“የትግራይ የውጭ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት” የሚል ስም የተሰጠው አካል ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መንግስት አዲስ ወታደሮች መልምሎ፣ አስለጥኖ፣ ከባድ መሳሪያ ታጥቆ አዲስ ጥቃት መጀመሩን አመልክቷል። ከጥቅምት አንድ ቀን ጀምሮ በሁሉም አቅጣጫዎች ጥቃት መከፈቱንም ገልጿል። “ከጦርነት ምንም የሚገኝ ነገር የለም” ሲል ድርድርን ያመላከተው መግለጫ ለዓለም መንግስታት ጥሪ አሰምቷል። ጥቃቱም በከባድ የጦር መሳሪያ፣ በታንክ፣ በሮኬቶች፣ በድሮኖች እንዲሁም በተዋጊ ጀቶች ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን ደጋግሞ አመልክቷል።


READ MORE STORIES


ሙሉ ማጥቃቱ ከመጀመሩ በፊት የትህነግ ሃይሎች ባሉባቸው አካባቢዎች በአየርና በከባድ መሳሪያ ድብደባ መካሄዱን የተለያዩ ሚዲያዎች የዕርዳታ ሰራተኞችን ዋቢ አድርገው መናገራቸው ይታወሳል።

አየር ሃይል ለትህነግ ሳይሆን በስፋት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጉን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ” ድሮን አሻንጉሊት ነው” በሚል አቶ ጌታቸው ይዛለፉ እንደነበር ያስታወሱ የትህነግ መግለጫና “የድረሱልን ጥሪ” ጥቃቱ ጠንካራ መሆኑንን አመላካች እንደሆነ ጥቁመዋል።

ድርጅቱ በመግለጫው እንዳለው ግን ጥቃቱ ከፍተኛ ቢባልም፣ የዓለም መንግስታትን ቢጣራም ” ሰራዊታችን ለመከት በቦታው ላይ ነው” ብሏል። ሰላም ወዳድ እንደሆኑ ጠቅሰው ተገደው በሚገቡበት ጦርነት ራሳቸውን ለመከላከል ሁሉንም ለማድረግ ብቃት እንዳላቸው ያስታውሳል።

” ጦርነት አማራጭ አይደለም” ሲል የጀመረው መግለጫ የትግራይ ሃይሎች የተከፈተባቸውን ጥቃት እየመከቱ መሆኑንን፣ ጦርነቱን በማሸነፍ ህልውናን ማረጋገጥ እንደሚችሉ አመልክቷል። አክሎም ” የዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ የመጨረሻውን ማጥቃት እንዲያወግዝና በዚህ ወሳኝ ሰዓት ላይ ለትግራይ ሕዝብ ድጋፍ እንዲሰጥ እንጠይቃለን” ሲል ጥሪ አሰምቷል። የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም ሲጠየቁ ምን በማድረግ እንደሚተባበሯቸው በመግለሻው አልተብራራም።

ለአገር ውስጥም ሆነ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ምንም ያልተነፈሰው የኢትዮጵያ መንግስት ” አሸባሪ” ካለው ሃይል ጋር እንደማይደራደር በይፋ ማስታወቁና ጦርነቱን በአጭር ጊዜ እንደሚጠቀልለው ማስታወቁ አይዘነጋም።

የአማራ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ባለፈው ሐሙስ በትዊተር አምዳቸው “በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ችግር ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ነፃ ለማውጣት በሁሉም ግንባሮች የማያዳግም ኦፕሬሽን በየትኛውም ጊዜና ሰዓት ሊደረግ ይችላል” ሲሉ በይፋ አስታውቀው ነበር።

አልጃዚራም በጋው ሲወጣ መንግስት ሙሉ ጥቃት እንደሚከፍት መስማትይ አመልክቶ ነበር። ሌሎች ሚዲያዎችም በዚሁ ሃሳብ ዙሪያ በስፋት የጦርነት ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር ሲያስታውቁ እንደነበር አይዘነጋም።

ያለ አንዳች ድብቅ መንግስት በሚዲያ ሰራዊት ሲመለምልና ሕዝቡ በፈቃደኛነት ሲተም ያሳይ ስለነበር ዜናውን ለሚሰሩት አካላት መረጃው ግራ የሚያጋባ አልነበረም። ይህንን ዝግጅት ነው አሁን መግለጫው አዲስ ውቀታደሮች ተመልምለው፣ ከባድ መሳሪያ ታጥቀውና ተደራጅተው አዲስ ጥቃት ጀመሩ ሲል ያስታወቀው።

“አብዛኛው የአየር፣ የድሮን እና የመድፍ ድብደባዎች” በአማጺያኑ ላይ መፈጸማቸውን እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች በሰሜን ጎንደርና በሰሜን ወሎ ዞኖች ውስጥ መሰማራታቸውን ከኤኤፍ ፒ መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ አስታውቋል። እንደተባለውም ዛሬ እግረኛው ሰራዊት ሁለት ወረዳዎችን አስለቅቆ ወደተቀራው አካባቢ እየተጠጋ መሆኑ ተሰምቷል። ደህናና አምደውርቅ ወረዳን እጁ ያስገባው የመከላከያ ሰራዊት አገኘ የተባለውን ድል መንግስትም ሆነ ክልሉ በይፋ አልገለጹም። ጦርነት ስለመጀመራቸው እንኳን አልተነፈሱም።

ከሁለት ቀን በፊት “በሁሉም ግንባሮች በኩል ግዙፍ ኃይል እየተንቀሳቀሰ ነው. . . በየትኛው ግንባር ጥቃት ሊከፍቱ እንደሚችሉ እርግጠኛ አይደለንም” ሲሉ የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ በስልክ መናገራቸውን ቢቢሲ ጨምሮ አመልክቷል። ይህ እስከታተመ ድረስ መንግስት ያለው ነገር የለም።

አሜሪካና አውሮፓ ህብረት ሁሉም ወገኖች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲያመሩ መጠየቃቸው አይዘነጋም። መንግስትንና አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ሃይል እኩል መመልከቱ የአሜሪካንን መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦርናጌ መናገራቸው አይዘነጋም።

ኢትዮጵያን ደግፈው የቆሙ አገራት ሰላም እንዲወርድ ፍላጎት እንዳላቸው፣ ንግግር ቢደረግ እንደሚደግፉና እንደሚያግዙ ሲያስታውቁ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማክበር፣ የውስጥ ጉዳይዋ ውስጥ ጣልቃ መግባትም እንዲቆም በመሳሰብ ነው።

የአሜሪካንና አብዛኛው አውሮፓ አገራት ድጋፍ ያለው ትህነግ ይህ ድጋፉን ወደ አንድ የሚጨበጥና አሁን ከገባበት ” የመጨረሻ ” ካለው ጥቃት እንዲታደጉት እየተየቀ ይመስላል። መግለጫውን ተከትሎ የአገራቱ ምላሻ እስካሁን ይፋ አልሆነም።

Exit mobile version