ETHIO12.COM

መከላከያ አላጠቃሁም አለ፤ ከተጀመረ ግን “ተጠቃሁ” ለማለት ጊዜ የሚሰጥ እንደማይሆን አመልከተ

የአገር መከላከያ ትህነግ ያሰራጨውን መግለጫ የተለመደ ቅጥፈት እንደሆነ አመልክቶ በተባለው ደረጃ ሙሉ ጥቃት እንዳልጀመረ አስታወቀ። የመከላከያ ሰራዊታችን በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ግን “ተጠቃሁ” ብሎ ለመናገር እንኳ ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ እንዳለበት አመልክቷል።

ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ። የጁንታው የድረሱልኝ ጥሪ …

አሸባሪው ትህነግ በሰጠው አሁናዊ መግለጫው “…የኢትዮጵያ ሠራዊት በአነስተኛ ወይም ትናንሽ ማጥቃት ሲፈፅም የቆየውን አሁን ላይ በከባድ መሳሪያ፣ በአየር ኃይል ታግዞና ሁሉንም የፀጥታ ኃይሎች አቀናጅቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ነው።…” ይላል።

የጦርነቱን ዓላማ ሲገልፅም “…በትግራይ ህዝብ ላይ ዳግም ወረራ ለመፈፀም፤ ሰቆቃውን ለማብዛትና ለማጥፋት እንዲሁም ውጊያውን ትግራይ መሬት በማድረግ ሊጨርሰን ነው ” ይላል።

ይህንን ባለበት አንደበቱ “…የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሠራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል…” ይላል። “ተጠቃሁ” ከሆነ ወደፊትና ወደ ጎን እንቅስቃሴ አለ ማለት ሲሆን፣ “አኮማትሬያለሁ” ግን ተዘርግቶም ሆነ ወደፊት መንቀሳቀስ የማይችል አድርጌዋለሁ ማለት ነው።

ሽብርተኛው ሁልጊዜ ውሸት ቀለቡ ነው፡፡ አንድ ነገር ሲፈልግ መጀመሪያ የሚያቅደው “እንዴት ልዋሽ” ብሎ ነው ፡፡ ቅጥፈቱ ደግሞ እልም ያለ ከመሆኑ የተነሳ “ይታወቅብኝ ይሆን? ” የሚል ጭንቀት የለበትም ፡፡

የዛሬው ፈሊጥ ደግሞ “አይናችሁን ያዙ ላሞኛችሁ” ዓይነት ሆኗል ፡፡ ለጋላቢዎቹ “መጠነ ሰፊ ጥቃት ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ” እያለ ሲማጸን ፤ ለሚጋልባቸው ደግሞ “አኮማትሬያለሁ” እያለ መዘላበድ ሆኗል ፡፡ ይህ መንታ ምላስ እራሱ ወሮና አጥቅቶ ህዝብ ያጎሳቆለው ሳያንስና ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልሙን በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እና በመላው የፀጥታ ኃይላችን አልሳካ ሲለው፤ በተለመደ ውሸቱ ዓለምን ለማደናገር የድረሱልኝ ጥሪውን ያቀርባል።


Read more stories


“እንጦጦ እንደርሳለን” ያለ ኃይል ፣ ተገልብጦ “ድረሱልን…!” ወሮ “ተወረርን…!” አጥቅቶ “ተጠቃን…!” እያለ ውሸት የማያልቅበት ኃይል ነው። የመከላከያ ሰራዊታችን በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ግን “ተጠቃሁ” ብሎ ለመናገር እንኳ ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት። የዚህ አሸባሪ የጁንታ ቡድን ውሸትና ማደናገሪያ እድሜው የመሸበት የቁራ ጩኸት ነው። በመሆኑም ህዝባችን በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስታቸው ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደው ድጋፍ እንዳይለየን እንላለን።

ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም

የአየር ሃይል አዛዥ በበኩላቸው የሰንደቅ ዓላማን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚከተለውን ብለዋል።

“ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለው የእድገት ጎዳና ያሰጋናል በሚሉ የውጭ ጠላቶቻችን ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በማበር ህዝባችን ላይ የደቀኑትን አደጋ በመቀልበስ ለኢትዮጵያ ህዝብ ድል የምናበስርበት ቀን ሩቅ አይሆንም ”

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ይልማ መርዳሳ14ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዲሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ነው ይህን ያሉት።

አሁን እያካሄድነው ባለው የህልውና ዘመቻ አየር ኃይል የጁንታውን አከርካሪ እየሰበረ እንደሚገኝ የገለፁት ዋና አዛዡ ፣ ትጥቆቻችንን በማዘመን ፣ ምቹ የስራ ቦታን በመፍጠርና ተልዕኳችንን መሰረት በማድርግ ወደ ፊት ለሚገጥሙን ማንኛውም ግዳጆች ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁነታችንን በማረጋገጥ በላቀ ሁኔታ ግዳጃችንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ከተገኙ የሰራዊት አባላት መከካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ፣ ሰራዊትና ሰንደቅ ዓላማ የማይነጣጠሉ ድል ሲያደርግ ከፍ አድርጎ የሚያውለበልባት የኢትዮጵያዊነትና የአሸናፊነት ምልክታችን ነች ብለዋል።ይታያል ምህረት ፎቶግራፍ ፅጌ ዳዊት

አቶ ጌታቸው በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ የተበተነው መግለጫ ይፋ ከመሆኑ በፊት በወገልታ፣ ውርጌሳና ሓሮ ግንባር ጦርነት እየተካሄደ መሆኑንን በማለዳ በቲውተር ገጻቸው አስፍረው ነበር። “የመጨረሻ ተብዬው የአብይ ማጥቃት” ሲሉ አቃለው፣ ማትቃቱ መቀልበሱና ሃይላቸው ተጨማሪ ቦታዎችን በተጠቀሱት ግንባሮች መያዙን ገልጸው ነበር።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሃላፊዎችን ተቅሰው የሰው ማዕበል በማስለፍ ያደረጉት የማትቃት ሙከራ የማይሰራ መሆኑንና ትግራይ እንደምታሸንፍ አመልክተው ነበር። በዚያው ቅጽበት ባሰራጩት መግለጫ አዲስ መታደሮች በመመልመል፣ በጀት፣ በድሮንና በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እንደተከፈተባቸው ለዓለም ህብረትሰብ በመግለጽ ” ድረሱልን” ማለታቸው ተሰምቷል።

መከላከያ ባወጣው አጠር ያለ መግለጫ ” እንጦጦ እደርሳለሁ” ያለ ሃይል ዛሬ ” ደረሱልኝ” ማለቱ ያረጀበት ቅጥፈቱ መሆኑንን አስታውቆ፣ መከላከያ ፈልጎ ማጥቃት ካወጀ ” ተጠቃሁ” ለማለት እንኳን ጊዘ እንደማይኖር አመልክቷል። አያይዞም ይህ የተለመደ ጩኸት ስለሆነ ሕዝብ ድጋፉን እንዲቀጥልና መንግስትን እንዲሰማ መክሯል። መግለጫው ማደናገሪያ መሆኑን ደጋግሞ ያስታወቀው መከላከያ ትህነግን “ራሱ ወሮ እራሱ የሚያለቅስ” ብሎታል።

“በሽፍታ ደረጃ ከሚወጋው መንግስት ነዳጅ፣ ቀለብ፣ ሃብት፣ በጥቅሉ ሙሉ ሎጂስቲክ የሚደረግለትና ይበልጥ ድጋፍ እንዲሰተው ባደባባይ የተባበሩት መንግስታት ሳይቀር ጥብቅና የቆመለት አሸባሪ ድርጅት ቢኖር ትህነግ ነው” በሚል በርካቶች ግራሞታቸውን እየገለጹ ነው።

Exit mobile version