ETHIO12.COM

ኮንስበርግ አምስት ገድሎ ሁለት ያቆሰለው ዴንማርካዊ ሃይማኖት ከአክራሪነት ጋር እየተያያዘ ነው

በኮንስበርግ ድንጋጤና አለመረጋጋት ሰፍኖ እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራዊ አስታውቋል። ሰላማዊ ህይወት መለያዋ በሆነችው ኖርዌይ እንዲህ ያለው አደጋ የሚፈጥረው ስሜት እጅግ የገዘፈ ነው። በጁላይ 21. 2011 ብሪቪክስ የሚባለው የወቅቱ 32 ዓመት ጎልማሳ ስልሳ ዘጠኝ ታዳጊዎችን በግፍ ከጨፈጨፈ አስራ አንድ ዓመት በሁዋላ ይህ ዜና መሰማቱ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ፖሊስን ጠቅሶ ኖርዋይ ዛሬ የተሰኘው ድረገጽ እንዳስነበበው ወንጀሉን የፈጸመው የ37 ዓመት ዴንማርካዊ ሃይማኖቱን ወደ ሙስሊምነት የቀየረና ከግለሰቡ ጋር የተያያዙ የአክራሪነት ስጋቶች ወይም ምልክቶች ነበሩ።

ተጠርጣሪውን አስመልክቶ በ2021 የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ፣ ይሁን እንጂ ከዛ በፊት ሪፖርቶች ደርሰዋቸው እንደነበርና በሪፖርቱ መሰረት ክትትል ይደረግ እንደነበር ለቬጌ ያመለከቱት የደቡብ ምስራቅ ክልል ፖሊስ ሃላፊ ኦሌ ብረድሩፕ፣ ደጋንና ቀስት በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎችን የገደለውና ያቆሰለው ይህ ተጠርጣሪ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው አመልክተዋል።


 The man charged with the deadly Kongsberg attack is a 37-year-old Danish citizen

The man charged with the murders in Kongsberg has been questioned. “He is cooperating with the police and providing details about the incident,” his lawyer said on Thursday. 


ጥፋቱ መፈጸሙን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች አቅጣጫ ለማስተካከልና ስጋቶችን ለማስወገድ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ሲያዝ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ከማሰማቱ ውጪ የተጎዳ ፖሊስም ሆን ሌላ አካል አለመኖሩን አመልክቷል። ተጠርጣሪው ተያዞ ወደ ድራመን መጓጓዙንናየሚመለከተው ክፍል ፍሬድሪክ ኑማን የተባሉ ጠበቃ እንደተመደቡለትም ተጠቅሷል።

ጠበቃው ደንበኛቸው / ተጠርጣሪው ስለሆነው ሁሉ አስፈላጊውን መረጃ በዝርዝር ለመስጠት እንደሚተባበር አስታውቀዋል። ኖርዌይ ዛሬ The man charged with the murders in Kongsberg has been questioned. “He is cooperating with the police and providing details about the incident,” his lawyer said.
ከሐሙስ በፊት በነበረው ምሽት ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው በኮንግስበርግ የሚኖረው የዴንማርክ የ 37 ዓመት ዜጋ መቼ ወደ ሙስሊምነት እንደተቀየረ አልተገለጸም።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን አስመልክቶ ከማክረር ጋር የተያያዙ መረጃዎች ለመጨረሻ ጊዜ የደረሰው በ2020 መሆኑን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ክትትሉን ለምን አጠናክሮ እንዳልቀጠለ እስካሁን በወጡ መረጃዎች አልተገለጸም። ይህ የበርካቶች ጥያቄ ሲሆን ፖሊስ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ተሰናባቿ ጠቅላይ ሚኒስትርና ከፍተኛ ባለስልጣኖች ይህን አሳዛኝ ግድያ አስመልክተው ሃዘናቸውን ገልጸዋል። በ2011 ድፍን ኖርዌይን ሃዘን ያለበሰው የኦትያ ደሴት የጅምላ ጭፍጨፋ ወደሁዋላ ያስታወሰው ይህ የኮንስበርግ ሃዘን ለቀጣዩ ጥንቃቄ እንደ አንድ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ይገመታል።

photo – Norway today

Exit mobile version