Site icon ETHIO12.COM

ሕዝብ ትህነግና መዋቅሩ ላይ ሙሉ ክተት እንዲጠራ ተጠየቀ፤ የደሴ ወጣቶች ወደ ግንባር አቀኑ

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የሰው ጎርፍ ማሰለፍ የፈጸመውንና እየፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋና ወረራ ተቋቁመው እየተፋለሙ ያሉ የአፋር ወጣቶች በትህነግና በመላው አገሪቱ ባሉ መዋቅሮቹ ላይ ክተት እንዲታወጅ መጠየቃቸው ተሰማ። ትህነግ በመላው ትግራይ ክተት አውጆና መላውን ህዝቡን ወታደር እንዳደረገ በገሃድ አስታውቆ በሰው ጎርፍ ወረራ መፈጸሙን በማስታወሰ ኢትዮጵያም ሕዝቧን ለክተት ማስነሳት እንዳለባት ተመልክቷል።

ይህን ሲሉ ምን ማለት እንደሆነ በማህበራዊ ገጽ አድራሻቸው ጥያቄ የቀረበላቸው ወጣቶች ውጊያው ግንባር ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ስፍራ ለሆዳቸው በተገዙና በድርጅቱ መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት በጥምረት የሚካሄድ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ስውር ደባ ሊገታ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የግንባሩ ፍልሚያ ሳይሆን ከግንባር ርቀውና ሕዝብ መካከል ሆነው ሽብር የሚነዙ፣ መረጃ የሚሰጡ ወገን መስለው በሁለት ቢላ የሚበሉት ላይ ሕዝብ በየአለበት የበኩሉን ተግባር እንዲወጣ መንግስት ሁሉ አቀፍ ክተት ሊያውጅ እንደሚገባ ማሳሳሰባቸውን ነው ወጣቶቹ ያስታወቁት።

ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ለወረራ የሚመጣውን የትህነግ ሃይል በጋሊሶማ እንዳደረገው እንዲያደርግ እንደምይፈቅዱ፣ ሁሉም ወደ ግንባር ለመሄድ መወሰናቸውን እንዳረጋገጡ አመልክተዋል። ንቅናቄም ተጀምሯል።

“ኢትዮጵያ አሸባሪ ላለችውና አሸባሪነቱን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ደጃቸው ድረስ እየመጣ በገሃድ ያሳየው ቡደን እየቀለበች፣ ከባድ መኪና ከነነዳጅ እየሰጠች፣ መድሃኒትና ባለሙያ እየላከች፣ ገንዘብ እንድትልክ እየተደረገች፣ በከተማም በንብረት ሽያጭ ስም ከፍተኛ ሃብት እየተመዘበረች መልሳ የምትወጋ አገር ” ሲሉ በርካቶች ዓለም ምን ያህል ቢታወር ይህን ሁሉ በደል እንደፈረደባት የማይገባቸው በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።

“በጥንካራ ኢትዮጵያ ላይ የትህነግ አሳብና ዓላማ ተግባራዊ ሊሆን ስለማይችል ኢትዮጵያን ማድከምና አቅሟን ማሳነስ ዋና ዓላማ አድርጎ የያዘው ትህነግ ከግብጽ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ፈጥሮ አገሪቱን እይመሰ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። በተግባርም በግብጽ ሚዲያ ቀርበው አቶ ጌታቸው ይህንኑ ማረጋገጣቸው አይዘነጋም። ይህ ሃይል ነው ዳግም ኢትዮጵያን እንዲገዛ በውጭና በውስጥ የተሰገሰጉ ተከፋዮችና የድርጅቱ የመቅዋቅር ሰዎች እየተጉ ያሉት” አቶ ሲሳይ ሃይሌ መናገራቸው አይዘነጋም።

በሌላ ዜና “አሸባሪው ህወሓት በሚያሰራጨው የሀሰት ወሬ ሳንረበሽ ወራሪውን ፊት ለፊት በመፋለም ህልውናችንን ለማረጋገጥ ግንባር ዘምተናል” ሲሉ የደሴ ከተማ ወጣቶች አስታወቁ።የከተማዋ ወጣቶች ዛሬ ውይይታቸውን ከጠናቀቁ በሁዋላ ወደ ግንባር ተመዋል።

ከዘማቾቹ መካከል ወጣት አሊ ይማም ለኢዜአ እንደገለጸው፤ አሸባሪው ህወሓት በአገርና በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ጥፋትና ግፍ የህብረተሰቡን የመኖር ህልውና አደጋ ላይ ጥሏል፡፡የሽብር ቡድኑ በየጊዜው በሚነዛው የሀሰት ወሬ መረበሽ እንደማይገባ የጠቆመው ወጣት አሊ፤ ”በሀሰት ወሬው ሳንደናገጥ ተደራጅተን ቡድኑን ለመፋለም ወደ ግንባር እየዘመትን ነው” ብሏል።”እኛ ሸሽተን ማን መስዋት ሆኖ ነጻ ሊያወጣን ነው” ያለው ወጣቱ፤ “መሞት ካለብንም ተወልደን፤ ቦርቀንና ጭቃ አቡክተን ባደግንባት ከተማችን ላይ መስዋእት እንሆናለን እንጅ ታሪክ አናበላሽም” ብሏል።

አሸባሪው ቡድን በሀሰት ፕሮፓጋንዳው ያሰበውን እንዳያሳካ ወጣቶቹ እንደሚሰሩ ገልጿል።ወጣት መሰረት ኃይሌ በበኩሏ ”ሁላችንም ወደ ግንባር በመዝመት ቡድኑን በመደምሰስ አካባቢያችንን ነጻ እናወጣለን” ብላለች፡፡

በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ሁለንተናዊ ጥቃት ለመመከት እናቶች ልጆቻቸውን መርቀው መላክና ደጀን መሆን እንዳለባቸው አመልክታለች።”የምንችለውን ጠጠር ወርውረን ኢትዮጵያን መታደግ እንጅ በወሬ ተፈትተን የቡድኑን ምኞት ማሳካት የለብንም” ያለው ደግሞ ወጣት ኤርሚያስ እሸቱ ነው፡፡”ሀገር በጠላት ተወራ፣ ሰው ከመኖሪያ ቀየው እየተፈናቀለና እየሞተ እንዲሁም በጥረቱ ያፈራው ሀብትና ንብረት እየተዘረፈና እየወደመ እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ወቅት አይደለም” ሲል ተናግሯል።

”ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ እንጅ መደናገጥና መረበሽ የለበትም” ያለው ወጣቱ ለሰራዊቱ ትጥቅና ስንቅ በማቀበል የኋላ ደጀንነቱን ማጠናከር እንዳለበት ጠቁሟል።

Exit mobile version