Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ በትህነግ ላይ ቃታ ሳበች፤ የዜጎች ርብርብ ውጤት አስገኘ

በ H.Res.445 አዋጅ

በአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል። የውሳኔው መግለጫ አሜሪካ የህወሃት ጉዳይ እንዳበቃለት መገንዘቧን የሚያመላክት ነው። “ጦርነቱ ቶሎ ካላበቃ የአጎዋ ገበያ ዕድልን ያስተጓጉላል እና መፍትሄው ድርድር ነው ከሚሉት በስተቀር በዲጂታል ዘመቻው በተደጋጋሚ የተስተጋቡት መልዕክቶች የተቀበሉት ሆነው ነው ያገኘኋቸው። በዚህም የቲወተር ዘመቻው ስኬታማ ሆኗል ማለት ይቻላል።

በትላንትና ዕለት የፀደቀው H. Res 445፣ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት ጦርነት መነሻው ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መሆኑን አምኗል። የአሜሪካ ባለስልጣናት እያወቁ ሆን ብለው ሊያምኑ ያልፈለጉትን ቁልፍ ጉዳይ ማመናቸውና ውሳኔያቸው ላይ ማስቀመጣቸው አሜሪካ በትህነግ ላይ ቃታ መስዳቧን የሚያመላክት ሆኗል።
በውሳኔ ሃሳቡ ህወሓት ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናትን ለጦርነት መጠቀምን በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስቧል። ህወሓት በሀይል ወርሮ ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ያለቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣም በአፅንኦት ጥሪ አቅርቧል።

አዋጁ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ለትግራይ የሚደርሰው ሰብዓዊ ርዳታ በተቀላጠፈ መልኩ እንዲደርስ ይጠይቃል። ህወሓት የሰብዓዊ ርዳታ ተሽከርካሪም ሆነ ርዳታውን ከመዝረፍ እንዲታቀብም ይጠይቃል። ህወሓት ከኦነግ ሸኔ የፈጠረውን ጥምረት ያለቅድመ ሁኔታ እንድያፈርስ በመግለጫው ተቀምጧል።

አሜሪካ በዚህ ደረጃ ላንፀባረቀችው የአቋም ለውጥ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጫና ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበረው ከመግለጫው ይዘት መታዘብ ችያለሁ። ጦርነቱ በፖለቲካ በብሄርና በታሪክ ጓዞች ይበልጥ እንዲወሳሰብ ሆኗል የሚለው መግለጫው እዚህ ላይ የተጠቀሱ ጉዳዩች ከተለያዩ አካላት ውይይቴ የተገነዘብኩት ነው ያሉት ካረን ቤዝ ናቸው። ይኸውም አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ የተጫወተውን ጉልህ ሚና እንድናስታውስ ያደርገናል። ሲል ማስታወሻውን ያኖረው እስሌማን ዓባይ – የዓባይ ልጅ ነው።

Exit mobile version