Site icon ETHIO12.COM

ጉራፈርዳ ወጣቶች ማኅበረሰቡን ይቅርታ ጠየቁ።

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶ ማህበረሰቡን ይቅርታ ጠየቁ፡፡

በተሳሳተ የሀሰት ትርክት ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር የተሳተፉ ወጣቶች ‘በድለናችኋል ይቅር በሉን’ ሲሉ የሃይማኖት አባቶችን እና የአገር ሽማግሌዎችን በመያዝ ማኅበረሰቡን የፀጥታ አካላትን እና አመራሮችን ይቅርታ ጠይቀዋል።

በወጣቶቹ ከዚህ በኋላ ግጭት እና አለመግባባትን በማስወገድ በጋራ ለመስራትና ለማደግ እንተጋለን ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ተከስቶ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ባህላዊ የእርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በሙሉ አቅማችን ወደ ልማት በመግባት የባከነውን ግዜ የሚያካክስ ልማታዊ ተግባር በመፈፀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በውስጥና በውጭ ያሉ ፀረ ሠላም ኃይሎች ሀገራችንን የጦርነት ቀጠና ውስጥ አስገብተው ከልማታችን ለማስቱጓጎል የሚሸርቡትን ሴራ ህዝባችን ባለው የሠላም እሴት እያመከነው ነው ብለዋል።

በዞኑ ተፍጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ያስከተለው መጠነ ሰፊ ችግር በማስወገድ እንደቀድሞው አንድነታችንን አጠናክረን በአዲስ መንፈስ ወደ ልማት መግባታችንን የምናውጅበት ትልቅ ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል ethio FM
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Exit mobile version