Site icon ETHIO12.COM

‹‹በውስጥም ፤በውጭም የተጋረጡ ችግሮችን ለማሸነፍ በጋራ መቆም ያስፈልጋል››

‹‹በውስጥም ፤በውጭም የተጋረጡ ችግሮችን ለማሸነፍ በጋራ መቆም ያስፈልጋል›› – ዶክተር ራሔል ባፌ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ

ኢትዮጵያ በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች እየተፈተነች የምትገኝበት ጊዜ እንደመሆኑ መደማመጥ፣ መነጋገርና በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ገለጹ፡፡

ዶክተር ራሄል ባፌ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች እየተፈተነች የምትገኝበት ጊዜ እንደመሆኑ መደማመጥ፣ መነጋገርና በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ የውስጥ ችግሮቻችንን በተቻለ ፍጥነት በመፍታትና በአንድነት በመቆም የሚመጡ የውጭ ጫናዎችን በጋራ መመከት ያስፈልጋል፡፡

መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተመሰረተው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እንዲካተቱ መደረጉ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲደመጡ እና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

መስከረም 24 የተካሄደው የመንግሥት ምስረታ በብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ የተካሄደ ቢሆንም ሕዝቡ ኢትዮጵያ የራሷ ጠንካራ መንግሥት እንዲኖራት ያስቻለበት ቀን ነው፡፡ ከክልል እስከ ፈዴራል ባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እንዲሳተፉ መደረጉ ደግሞ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲደመጡ እና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት እንዲኖር የሚያግዝ ነው፡፡(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version