Site icon ETHIO12.COM

የደቡብ ክልላ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ

መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡

የክልላችን ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን አሸባሪው የትህነግ ሴራ በማክሸፍ የሀገራችንን ህልውና በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ይሆናሉ!!

በተንኮል ተውልዶ በሴራ ፖለቲካ ጥርሱን የነቀለው ራሱን የትግራይ ህዝን ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሰየመው ዘራፊና አጥፊ ቡድን ለ27 አመታት ሙሉ በክልሉ ህዝቦች ብሎም በመላው ኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸመው በደልና ክህደት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

ይህ መርዛማና እኩይ ተግባሩ ባንገፈገፋቸው መላው ኢትዮጵያዊያን መራር ትግል ከህዝቦች ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የተደረገው አሸባሪው ቡድን ያለፉት 3 አመታት የለውጥ ሂደታችንን ለመቀልበስ ያልሸረበው ሴራ አልነበረም። በክልላችን በዚህ የሽብር ቡድን አቀናባሪነት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ተቀጥፏል፣ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል፣ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳት አድርሷል::

በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ዜጎችን በመጨፍጨፍ፣ የእርስ በርስ ፍጅቶችን በመጠንሰስ፣ ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገርችንን ቀንደኛ ጠላትና ባንዳ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።

ይህ በቀቢጸ ተስፋ የተሞላ ቡድን አሁንም ይህን እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል በአማራና አፋር ክልል ህዝቦች የማያቋርጥ የህልውና ስጋት ደቅኖ ይገኛል። ይህ ህገወጥ ቡድን ጠቤ ከተወሰኑ ክፍሎች ጋር ነው ቢልም ዋነኛ ግቡ ሀገራችንን ማፍረስ እንደሆነ እሙን ነው።

ይህም ብቻ ሳይሆን ዛሬ በአማራና አፋር ክልሎች የጀመረውን የሽብር፣ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ መድፈር፣ ዘረፋና የሌብነት ተግባር በእነዚህ አካባቢዎች ተገድቦ የሚቀር እንዳልሆነ መታወቅ አለበት።

ይህ ሰውበላና ዘራፊ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ እድሜ ልክ ለመበደል እና የራሱን ጀሌዎች ብቻ በሀብት ማማ ላይ ከፍ ለማድረግ ሩቅ አልሞ ቢጓዝም ለውጥ ናፋቂው እና በቡድኑ የደረሰበት በደል ያንገሸገሸው የሀገራችን ህዝብ ባሳየው ታላቅ ትግል አሸባሪው ቡድን ከማዕከላዊ መንግስት በስልጣን እንዲገለል ተደርጓል።

ላለፉት 27 ዓመታት የህዝባችንን ደም እንደ መዥገር ተጣብቆ ሲመጥ የነበረው ይህ ጁንታ ቡድን ዛሬም እኔ ያልነገስኩባት ሃገር ትፍረስ፣ ለኔ ያልተገዛ ህዝብ ይጥፋ በሚል ማንነቱን ያሳየ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋና ውድመት እያደረስ ይገኛል።

ይህ የጥፋት ቡድን ትውልድን ሲያመክን የኖረ፣ ከውጭ ጠላት በላይ የኢትዮጵያን ክብር ያዋረደ ሰው በላ ስርአት እስከወዲያኛው ታሪክ ሆኖ እንዲቀር የጠነከረ አንድነት ያስፈልጋል።

ይህንን የሽብር ቡድን አምርሮ መዋጋት ደግሞ አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ መላው የክልላችን ህዝቦች ቡድኑን በመገርሰስ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ማስተላለፍ ይወዳል።

ጀግኖች አባቶቻችን በደም እና በአጥንት ያቆዩልንን ገናና ሀገር ማንም ከምድር ተነስቶ በመሰረተው ተራ የሽብር ቡድን ሊያፈርስ አይችልም ።

ይህ የሽብር ቡድን ሀገርን ከብተና ዜጎቻችንን ደግሞ ከእልቂት መታደግ የምንችለው በጀግኖች ወጣቶቻችን እና በመላው ህዝባችን መራራ ትግል ብቻ ነው።

መታሰር፣ መሰደድ፣ መሞት፣ ተገዶ መደፈር፣ በአንጡራ ላብ ያፈራነው ሀብት በወሮ በላው ቡድን መዘረፍ እና መሰል የሰቆቃ ጊዜያት እንዲያበቃ ለሀገራችን ህልውና በቁጭት እና በአትንኩኝ ባይነት ስሜት መታገል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።

ዛሬ እንዳሻን የምንኖርባትን ሀገር እንደው በዋዛ አልተረከብንም ጀግኖች አባቶቻችን በዱር በገደሉ እየተዋደቁ የአሁኑን ማንነታችንን አስረክበውናል።

ይህችን ገናና ሀገር ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ያለንን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም ይህንን ሰው በላ ቡድን ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ ይጠበቅብናል።

ውጊያችን ከጁንታው ጋር ብቻ ሳይሆን ከዚህ አጥፊ ቡድን ኢትዮጵያን የመበተን እኩይ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከተጋቡ የውጭ እና የውስጥ የጥፋት ተባባሪዎችም ጭምር እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን።

ስለሆነም መላው የክልላችን ህዝቦች የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎችንና ሰርጎ ገቦችን መከታተልና የአከባቢያችሁን ከምንም ጊዜ በላይ ነቅታችሁ እንድትጠብቁ፣ በግንባር እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለክልል ልዩ ሃይሎች፣ ለምልሻዎችና ለተፈናቀሉ ወገኖች ስታደርጉ የቆያችሁትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም በክልላችን ያለንን ብዝሀነት በመጠቀም ሊያባላን ያሰፈሰፈውን የጠላት ሃይል ግብአተ መሬት ለመፈጸም መላው ህዝባችን በአንድነት እንዲንቀሳቀስ፣ የክልላችን ወጣቶችም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ: አከባቢያቸውን ተደራጅተው በንቃት እንዲጠብቁ: በየደረጃዉ ያለዉ አመራርም የክልሉን ጸጥታ አካላት፣ ወጣቶች እና ምልዓተ ህዝቡን በማስተባበር በግንባርቀድምትነት እንዲረባረብና ለማይቀረው ድል ያለንን ሁሉ ምንም ሳናስቀር ጠላትን ለመመከትና ሀገርን ለማዳን በማዋል ለሚደረገዉ ፍልሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ወስኗል፡፡

Exit mobile version