Site icon ETHIO12.COM

መንግሥት የዘር ማጥፋት እንዳልፈጸመ፣ረሃብን ለጦርነት እንዳልተጠቀመ በዓለም ዐቀፍ ሪፖርት ተረጋገጠ

UN HRC

የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ መገናኛ ብዙኃንና መንግሥታት በኩል እየቀረበበት ያለውን ‹በትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል› ክስ ዓለም ዐቀፉ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽኖች የጋራ ምርመራ ሪፖርት ውድቅ እንዳደርገው በሪፖርቱ ይፋ አደረገ።

የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ደጋፊ የሆኑ ምዕራባዊያን መንግሥታትና ድርጅቶች እንዲሁም መገናኛ ብዙኃን ከአጋራቸው ሕወሓት ብቻ በሚወስዱት ሀሰተኛ መረጃ መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል ሲሉ ቢከርሙም ሪፖርቱ “መስረተ ቢስ” ብሎታል።

የጋራ ምርመራ ሪፖርቱ የተሰራው በኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጥምረት ነው እንደሆነ የግኝቱ ውጤት ሪፖርት መረጃ አመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት በተደጋጋሚ ሲከሰስባቸው የነበሩ እንደ ጾታዊ ጥቃትንና ረሃብን ለጦርነት ዓላማ መጠቀም ክስም በሪፖርቱ ውድቅ መሆኑ ተመክቷል።

ይልቁንም ሪፖርቱ ‹‹የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ›› ሲል የገለፃቸው የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር የዋሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዲሁም ሌሎች ንፁሃንን ብሔርን መሰረት ባደረገ መልኩ ጥቃት መፈጸማቸውንም አረጋግጧል፡፡ይህም እስከዛሬ ያልተገለጹ የሽብር ቡድኑን ብዙ ጥፋቶች የሚያሳይና መንግሥት ሲያቀርባቸው የነበሩ መረጃዎችን ተዓማኒነት የሚያሳድጉ ሆነዋል።

ሪፖርቱ በርካታ ጉዳዮችን አጥርቶ ያሳየ በመሆኑ ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉት አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሪፖርቱን አስመልክቶ ያሳዩትን አቋም ዋልታ እንዲህ ዘግቦታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍሎች የፈጸመው ጥቃት ላያ ያደረጉትን ጥናት ውጤት በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉ ገለጹ፡፡

የሁለቱ ኮሚሽኖች የጋራ ጥናት በትግራይ መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመፈፀሙን ማረጋገጡንም በበጎው አንስተውታል፡፡ሪፖርቱም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብና ፆታዊ ጥቃትን እንደጦርነት መሳሪያ አለመጠቀሙን ቢያረጋግጡም ጠላቶቻችን ግን ዛሬም እኛን በሀሰት ሊከሱ ያለእረፍት ያሴራሉ ብለዋል፡፡

ሪፖርቱ መንግሥት ሆን ብሎ የትግራይ ሕዝብ ሰብኣዊ እርዳታ እንዳይደርሰው አስተጓጉሏል የሚለውን ክስ እውነት የሚያደርግ መረጃ ማግኘት አለመቻሉንም አሳውቋል፡፡መንግሥት ሪፖርቱ ከሸፈነው ጊዜና ስፍራ አንፃር እንዲሁም አንዳንድ ድምዳሜዎች ላይ የማይስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ተቋማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው የሽብር ቡድኑን እውነተኛ ስዕል ለማሳየት ያደረጉትን ጥረት አበረታተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥምር ምርመራው ሪፖርት ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተሰነዘሩ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን አካቷል በሚል ማዘናቸውን በመገለጽም መንግሥት ምርራው ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንደሚቀበለው ገልጸዋል፡፡በሪፖርቱ የማንስማማባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ሰነዱ እያደረግነው ላለው የጥቃት ሰለባዎችን የመድረስ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈንና የመከላከያ እርምጃዎች የመውሰድ ጥረት አጋዥ እንደሆነ አድርገን እንወስደዋለን ብለዋል፡፡በጦርነቱ ንጹሃን ሰብኣዊ ክብርና ነፃነታቸው መገፈፉ ልብ ሰባሪ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡


ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ …
ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ …
የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
 አንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ …
የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
የስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት …
ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች …
Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
The Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to …
Exit mobile version