Site icon ETHIO12.COM

የተቀደደው ተሰፍቶ በቀናት ድል እየተመዘገበ ነው፤ አዲስ አበባ ከተተ

ቀደም ሲል በተሰራ መጠነኛ ስህተትና ሰርጎ ገቦች ከደጋፊዎቻቸው ነዋሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ወስደውት የነበረው የበላይነት እየተቀለበሰ መሆኑ ተሰማ። “የተቀደደው ተስፈቷል” ሲሉ መረጃ ያደረሱን እንዳሉት በየግንባሩ የጥምር ጥቃት ተከፍቷል። ድልም እየተጨበጠ ነው። አዲስ አበባ ከተተ።

በጋሸና ግንባር እያጸዳ ያለው ሃይል ወደ ወልደያና ደላንታ አቅጣጫ እየገፋ መሆኑ ታውቋል። ዝምታ ተመርጦና መረጃ ተዘግቶ እየተካሄደ ባለው ፍልሚያ አየር ሃይል መንገድ እያጠራ ለእግረኛው ያለማቋረጥ ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተሰምቷል።

ተማምለውና ቃል ቆርጠው እንደተነሱ የተነገረላቸው የአፋር ጀግኖች ” የምድር ድሮኖች” ከመከላከያ ጋር ከኮምቦልቻ ገስግሶ ካሳጊታ ድረስ የሄደውን የትህነግ ወራሪ ሃይል አንገዋለውታል። የተረፈውም ከቡርቃና ባቲ ተባሯል። ከአፋር ቀጥታ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ማጥቃቱ ወደፊት ቀጥሏል።

ደሴና ኮምቦልቻን ወደ ነዋሪዎቻቸው ለመመለስ ብርቱ ተጋድሎ እየተደረገ ነው።

በየራያ ጀግኖች እርስታቸውን መያዛቸውን ግን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው እንደማይገለጽ ያስታወቁት የመረጃው ባለቤት የወገን ሃይል አድማሱን በማስፋት ወደ ጎብዬና ወልዲያ እየገፉ እንደሆነ ተመልክቷል። የሀብሩ፣የወረባቦና አካባቢው ኃይልም ወሰኑን እያጠራና እያጸዳ መሆኑ ታውቋል።

የክተት ጥሪውን ተከትሎ የጎንደር ፋኖና ሚኒሻ ወደ ግንባር እየተመመ ሲሆን ሸዋ ቀበቶውን አስሮ እያጠናቀቀ በከሚሴ የሚልከሰከሰውን ሃይል ሊያጸዳ ጉዞ ለመጀመር ሰዓት እያየ ነው።አዲስ አበቤም “ከተማ ለምኔ” ብሎ ወደ ግንባር ለመዝመት ዛሬ በአዲስ አበባ ቃል ገብቷል። ” ሞት ወይም ነጻነት ያሉ ዜጎች በየአቅጣጫው ወደ ግንባር እየተመሙ ነው።
ኤርሚያስ ቶኩማ እንደሚለው “ከሚሴ የሚደረገው የሸኔ የጫጉላ ሽርሽር ዋጋውን እያገኝ ነው” እውነታውና ብዙ ዝርዝር ያልተነገረለት ጉዳይ ይህ ሆኖ ሳለ ” አዲስ አበባን ለመያዝ ተቃርበዋል፣ ተቃርበናል፣ እየቀረብን ነው ” በሚል የሚነዛው ወሬ ተራ የቅስቀሳ ስራ እንደሆነም አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሃገር መከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እያከናወነ ነው።ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ ከከተማዋ የተውጣጡ ወጣቶች ሽኝት ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች የከተማዋ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የተደረገው ሽኝት አስደማሚ እንደነበር የነበሩ በአካል የነበሩ አስታውቀዋል። ከአመራሩም ሰላሳ ወደ ግንባር ለመቀላቀል ተሸኝተዋል።

የትህነግን የህዝብ ማዕበል በታላቁ የሕዝብ ማዕበል ለማምከን የተያዘውን ዕቅድ ተከትሎ የውጭ አገር ጫናው ተባብሷል። የትህነግ ደጋፊዎችም ቢሆኑ እንደቀድሞው ፉከራ ላይ አይደሉም። ሁኔታውን የሚያጤኑ እንዳሉት ቀጣዩ ጦርነት ቀለበቱን እያጠበበ ሲሄድ የሚሆነው ያስፈራል። ትህነግ ከልኩ በላይ በማሰብ 120 ሚሊዮን ሕዝብ ለመውረር የያዘውን ጤናማ ያልሆነ ዕቅድ ቢመረመር የተሻለ እንደሆነ የሚመክሩ አሉ። ጣት መቀሳሰሩ ቀርቶ ሌሎች አማራጮችን ቢያይ እነደሚሻልም ይመክራሉ። ትህነግ በወረራ በገባባቸው ስፍራዎች ሁሉ የፈጸመው ተግባር የፈጠረው ቁጣ እንዲረግብ መሰራት እንዳለበት የሚመክሩት ወገኖች በምስኪኖች ህይወት ቁማር ሊቆም እንደሚገባ ደጋግመው እያሳሰቡ ነው። ሰው ደጅ ድረስ የመጣ ሃይል “ለምን ጥቃት ተፈጸመብኝ” ቢል ሰሚ የለውምና የትህነግ አመራሮች ታሪካዊ ውሳኔ እንዲወስኑ፣ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ከሆነ ከሁሉም ወገን የሚረግፈው ምስኪን ይተርፋል ቀሪው ጉዳይ የህግና የህግ ብቻ ይሆናል።

ሌላ ዜና

የእብናት ወረዳ ዘማቾች ሽኝት ተደረገላቸዉአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ነዋሪዎች የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ቡድን ለመፋለም ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።

አሸባሪውና ወራሪው ቡድን በአማራ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ሊበቃ ይገባል፤ከእንግዲህ በኋላ አሸባሪውና ወራሪውን የትግራይ ኃይል የሚሸከም ትክሻ የለንም፤ አርሶ አደሩ ማምረትና ወልዶ ማሳደግ የሚቻለው የአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል ግብዓተ መሬት ሲፈጸም ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ቡድኑ ሴቶችን እየገደለ፣ እየደፈረ እና የአርሶ አደሩን ሀብት እየዘረፈ መኖር የለበትም ብለዋል፡፡ ይህንን ወራሪ እና ሽብርተኛ ኃይል በአጭር ጊዜ ድባቅ በመምታት ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ነፃ ለማውጣት በቁርጠኝነት መነሳታቸውን ተናግረዋል። ነፃነቷን ጠብቃ ለዘመናት የኖረችውን ኢትዮጵያ በጡት ነካሹና አሸባሪው ቡድን ተወራለች፤ ሕዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ በአንድነት ከተነሳ ግን አሸባሪ ኃይሉን በአጭር ቀን መደምሰስ ይችላል፤ለዚህም በነቂስ መነሳታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእብናት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሙሉጌታ ይማም በበኩላቸዉ÷ ነጻነቷ ሉዓላዊነቷ እና ክብሯ የተጠበቀ ሀገር ከአያቶቻችን እንደተረከብን ለሚቀጥለው ትውልድም ከነጻነቷ፣ ሉዓላዊነቷ እና ክብሯ ነው ልናስረክብ የሚገባው ብለዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ሕዝቡ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተፋልሞ ነጻ እንዳይወጣ የሐሰት ወሬ በሚያናፍሱ የውስጥ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል፤ እንዲህ ዓይነት ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላትም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version