Site icon ETHIO12.COM

“ለድርድር የሚቀርብ ሉዓላዊነት፤ ለገበያ የሚቀርብ አገር የለም”

“ለድርድር የሚቀርብ ሉዓላዊነት፤ ለገበያ የሚቀርብ አገር የለም” ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት አስታወቁ።

የምክር ቤቱ አባላት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የአሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔ አስነዋሪ አገር አፍራሽ አቋም በጽኑ እንደሚቃወሙ አመልክተዋል።

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እኩይ ተግባር እና የኦነግ ሸኔን አፍራሽ እንቅስቃሴ ለማስወገድ መንግስት እና ህዝብ የሚያደርጉትን ጥረት እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመደገፍ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።

አሸባሪ ቡድኖቹ ሙሉ ለሙሉ እስኪደመሰሱ ድረስም በማንኛውም የጸጥታ ማስጠበቅ ተግባር ላይ የሚሣተፉ መሆኑንም ገልጸዋል።

ህዝቡም የአሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔንና ሀገር አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመቀልበስ የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሁለቱ የአሸባሪ ቡድኖች በህዝብ ላይ እያደረሱ የሚገኙትን በደል ተረድተው ማውገዝ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ፓርቲዎቹም ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው የሁለቱን አሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለማስወገድ በጋራ እና በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

(ኢዜአ)

Exit mobile version