Site icon ETHIO12.COM

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት – ማሳሰቢያ!!

ከባህርዳርከተማአስተዳደርየፀጥታምክርቤትኮማንድፖስትየተላለፈአስቸኳይመልዕክት፦

1ኛ. ከዛሬ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት የስራ ቀናት በባህርዳር ከተማ የሚገኝ ያልተመዘገበ ማንኛውም የግል የጦር መሳሪያ በአካባቢያችሁ በሚገኝ ሚሊሻ ጽ/ቤት በአምስት ቀናት ውስጥ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን።

2ኛ. በጦር ግንባር በነበረ ዘመቻ ላይ ማንኛውንም የጦር መሳሪያና ትጥቅ ይዛችሁ ወደ ከተማ ለተመለሳችሁ፦

ግንባር የመሄድ ፍላጎት ያላችሁ መንግስት ባወጣው አደረጃጀት ታቅፋችሁ ወደ ግንባር እንድትሄዱ እናሳስባለን።

ከፀጥታ ሃይሉ ውጭ መሳሪያ ይዞ በከተማችን በተለያዩ ስፍራዎች ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም አካል በፀጥታ ሃይሉ ተጠያቂ መሆኑን እናሳስባለን።

3ኛ. በፋኖ አደረጃጀት ለሰለጠነ ማንኛውም የታጠቀ ሃይል፦

በፋኖ አደረጃጀት ሰልጥናችሁ ወደ ግንባር የመሄድ ፍላጎት ያላችሁ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ገብታችሁ እንድትዘምቱ እያሳሰብን ከተማ አስተዳደሩ ማንኛውንም የሎጅስቲክ ድጋፍ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን።

በፀጥታ ምክር ቤቱ ወይም በሰላምና ደህንነት ቢሮ ስምሪት ሳይቀበል መሳሪያ ታጥቆ በከተማችን በተለያዩ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ይዞ ሲንቀሳቀስ የተገኘ በፀጥታ ሃይሉ ተጠያቂ መሆኑን እናሳስባለን።

4ኛ. ከተለያዩ የጦርነት ቀጠናዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማችን ባህርዳር ስለ መጡ ግለሰቦች፦

ተፈናቃዮቹ ለተፈናቃይ በተዘጋጀው መጠለያ ካንፕ እየተመዘገቡ እንዲገቡ እያሳሰብን። ይህ ካልሆነ ደግሞ ማንኛውም ቤት አከራይ የተከራይ ግለሰቦችን መታወቂ ኮፒ በማድረግ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያሳውቅ እናሳስባለን።

ይህም የሚሆንበት ምክኒያት በተፈናቃይ ስም ሰርጎ ገቦች እንዳሉ ስለተደረሰበት ለከተማችን ደህንነት ነው።

ማሳሰቢያ፦

ከላይ የተዘረዘሩትን ሀሳቦች በአምስት ቀን ውስጥ ተግባራዊ በማያደርግ ግለሰብ ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልፃለን ።

ኢትዮጵያ ትቀጥላለች፣
ጠላቶቿ ይቀበራሉ!!

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት (ኮማንድ ፖስት)

Exit mobile version