Site icon ETHIO12.COM

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘ

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አውግዟል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደነበርም ነው የጠየቀሰው።

የአሜሪካ መንግስትም የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል

  1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።
  2. የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።
  3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሷል።

እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።

  1. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል።
  2. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን አበረታቶታል ብሎ መንግስት ያምናል።

የማዕቀቡ አላማ የተፈጠረው ቀውስ እንዲቆም ለማስገደድ ከሆነ፣ የአሜሪካ መንግስት እና የዓለም ማህበረሰብ ትክክለኛ ማዕቀብ እና ተጨማሪ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ኢላማው በህወሓት ላይ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ መንግስት በፅኑ ያምናል።

ስለዚህ የአሜሪካ መንግስት በኤርትራ ላይ የወሰደውን ማዕቀብ እንዲሰርዝ እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፈተናዎች ዋነኛ መንስኤ የሆነውን አሸባሪውን ህወሓት በመቃወም እርምጃ እንዲወስድ በአፅንኦት እንጠይቃለን ማለቱን መግለጫው አመላክቷል።

EBC

Exit mobile version