Site icon ETHIO12.COM

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያ

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያሀገራችን ኢትዮጵያ የህልዉና ዘመቻ ላይ መሆኗ የሚታውቅ ነዉ። በዚህም በኢትዮጵያ ህልዉና አደጋን ለመከላከል፣ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋት እና ሉዓላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መዉስድ አስፈላጊ ሆኗል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲም በአዋጅ በተሰጠዉ ስልጣን እና ኃላፊነት መሰረት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የኢንፎርሜሽን እና የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን ሲመዘግብ እና ሲቆጣጠር የቆየ ቢሆንም አሁናዊ ይዞታን ለማወቅ እና እነዚህ የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እና ገብረ-አበሮቻቸዉ ለሽብር ዓላማ እንዳይውሉ መሳሪያዎቹን እንደገና መመዝገብ እና በሚመለከተው አካል እጅ ስለመኖሩ ማወቅ ኤጀንሲዉ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽን እና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ እናሳስባለን።

1. ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች

• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)

• ኮምፓስ (Compass)

• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS)

2. ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች

• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)

• ሳተላይት ስልክ (satellite phone)

3. ቪሳት እና ቢጋን

(A very small aperture terminal

(VSAT) and

Broadband Global Area network (BGAN))

4. ድሮኖች (Drones)

እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ

በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ ይጠበቅበታል።

አካባቢያችንን ነቅተን እንጠብቅ!! የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ

Exit mobile version