ETHIO12.COM

እነ 360 የሃሰት ዘገባቸው ይፋ ሆነ፤ ፖሊስ በድጋሚ ቪዲዮ ይፋ አደረገ

ሃብታሙ አያሌው ተቀጥሮ የሚሰራበትና ኤርሚያስ በአበበ ሲከሰስ ለሌላው ተቀጣሪ ብሩክ አሳልፎ የሰጠው 360 የሚባለው የዲጂታል ወያኔ አካል ከቤተ ክህነት ተገኘ ተብሎ በፖሊስ የቀረበውን የጦር መሳሪያና ጥይት ” አሚሶም ድሮ ያወታው ነው” በሚል በሃብታሙ አያሌው አነሳሽነት መንግስትን አጭበርባሪ አደርጎ በማቅረብ ሲተችና ምስል ሲያዘዋውር ነበር።

በእስር ቤት በዱላ ይሁን በሌላ የመቀመጫ ህመም እንደደረሰበት ሲናገርና ራሱን በቃሬዛ ላይ አድርጎ ” ድረሱልኝ ” ሲል የነበረው ሃብታሙ አያሌው፣ በ1997 ድምጽ ተሰረቀ ብለው ጎዳና በወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ አጋዚ የሚባለው የትህነግ ታማኝ ሰራዊት ግንባ ግንባር እየመታ ሲጥል ” ህግ የጣሱ ናቸው ደግ አደረጉ። እርምጃው ይቀጥላል” ያለው ታጋይ ኤርሚያስ በጋራ ሆነው ከቤተ ክህነት የተገኘውን መሳሪያ መንግስት እንዳጭበረበረ አድርገው ያቀረቡበትን ምክንያ አነጋግሯል።

ሃብታሙ አያሌው ምስሉን ዜናውን ካሰራጨው ኢቢሲ ወስዶ የቆየ የአሚሶም ዜና ላይ በመለጠፍ ፖሊስ ከቀደመ የአሚሶም ዜና ላይ እንደወሰደ አደርጎ ባማስመሰል የህግ ማስከበሩን ስም ሲያጠፋ የዋለበት ምክንያት እወነታውን በሚረዱ ወገኖች ዘንዳ ግልጽ አልነበረም።

መቀመቻው በትህነግ መርማሪዎች በምን መልኩ ጉዳት እንደደረሰበት ባያስረዳም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ምስል በማሰራጨት በአገር ወዳዶች ጥረት ወደ አሜሪካ ያቀናው ሃብታሙ አያሌው፣ በዛ ደረጃ ጉዳት አድርሶብናል ላለው ትሀንግና መዋቅሩ ለምን በዚህ መልኩ መሟገት እንደፈለገ ለበርካቶች እንቆቅልሽ ነው። አለያም ትርክቱ ሁሉ ቅንብር ወይም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ እንደሆነ አድርጎ ለመውሰድ አስገዳጅ እየሆነ ነው። በርካታ አስተያየት ሰጪዎች “ቤተሰብ ስላለው፣ ልጆች ስለፈራ ከዚህ አልፎ መናገርና ደረሰብኝ ሲል የነበረውን ጉዳት መተንተን አስፈላጊ አይደለም” በማለት እንደሚናገሩት የሃብታሙ ጉዳይ ከማስገረም ያለፈ ነው።

የአዲስ አበባ የኢሃዴግ ወጣቶች ክንፍ መሪ እንደነበር አምኖ የሚናገረው ሃብታሙ አያሌው የወግ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቆርቋሪ፣ በተግባር ግን እምነት አልባ እስኪመስል ” ከብት ያኮላሸውን” እንዲሉ ትህነግ ስር ተለጥፎ ማቀንቀኑ ለእምነቱ ተከታዪች ስድም ጭምር ነው።

ካድሬ እንዲነዳት በተደረገችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሽጉጥ የሚታተቅ ጳጳስ ተሹሞላት በነበረችው ቤተክርስቲያን፣ በህይወት ያሉት ጳጳሷ እንዲሰደዱ በተደረጉበት ቤተክርስቲያን ዙሪያ ምንም የማይለው፣ ለስሙ ከመነፈሳዊ ኮሌጅ መመረቁን የሚናገርው ሃብታሙ ጨዋ በሆነበት ፖለትካ የኦርቶዶክስ ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ አስተውለው ለሚጓዙ ህመም ነው። በተለይም ዛሬ አማራው ላይ የህልውና ፈተና በተጋረጠበትና የትህነግ ወገን በሆኑት እነ ሻለቃ ዳዊት፣ ታምራት ላይኔና ልደቱ አያሌውን እቅድ ለማስፈጸም በፈተራ ዘመቻ ላይ መሳተፉ በርካቶችን አሳዝኗል።

ፖሊስ ከቤተ ክህነት ያገኘውን መሳሪያ ሲቆጣጠር ሕዝብ እውነቱን እንዲረዳ በቪዲዮ እያሳየ መሆኑ እየታወቀ፣ ምስሉም ግልጽ ሆኖ ሳለ የኢቢሲ ዜና ያሰራጨውን ምስልና በመቁረጥ የቀድሞ የአሚሶም ዜና ላይ በመለጠፍ ፖሊስን ሃሰተኛ የማድረጉ ፍላጎት ከየት መጣ? እንዴት መጣ? እነማን ይህን ጉዳይ በዚህ መልኩ እምዲጭበረበር አዘዙ ወይም ፈለጉ የሚለው ሃሳብ ቁልፍና ማንም ዜጋ ሊያውቀው የሚገባ ነው።

ሓብታሙ ኣያሌው ከኢቢሲ ላይ ያለውን ፎቶ ኣሚሶም ላይ ለጥፎ መንግስት ውሸታም ነው ሲል ኣመሸ፤ ቪዲዮውን ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱና ፍርድዎን ይስጡ። ሃቅ ላይ በመምርኮዝ መንግስትንም ሆነ አመራሮቹን መተቸት እየተቻለ በዚህ ደረጃ፣ አሁን ባለንበት ወቅት የቅጥፈት ዜናና ትንታኔ ለምን ተመረጠ? የሚለውን አንባቢ ፍረድ… ለነዚህ አካላት ብር እያዋጣህ አገር አልባ ለመሆን የምትጣደፍ ሁሉ ተማርበት። ቪዲዮውን መመልከት ምን ያህል እነ ሃብታሙ እንደዋሹ ለመረዳት በቂ ነው። መረዳት ብቻውን ግን ግብ ሊሆን አይገባውም። ለምን በዚህ ደረጃ መዋሸትና ፖሊስን በዛሬ ወቅት ማንቋሸሽ አስፈለግ የሚለውን ጥያቄ መመለስም ግድ ይላል…

https://fb.watch/9nGlGtae_L/

ሓብታሙኣያሌውከኢቲቪላይያለውንፎቶኣሚሶምላይለጥፎ

https://fb.watch/9nGlGtae_L/

የፀጥታ አካላትን ተግባር ማጣጣል እና ለራስ ዓላማ ለማዋል መሞከር ተገቢነት የለውም -ፖሊስ

የፀጥታ አካላት ከህዝብ ጋር በመተባበር እያከናወኑ የሚገኙትን ውጤታማ ተግባር ማጣጣል እና ከእውነት በመሰወር ለራስ ዓላማ ለማዋል መሞከር ተገቢነት እንደሌለው የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት የንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ በህዝብ ጥቆማ የተገኙ ጥይቶች አስመልከቶ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የፀጥታ አካላት ከህዝብ ጋር በመተባበር እያከናወኑ የሚገኙትን ውጤታማ ተግባር ማጣጣል እና ከእውነት በመሰወር ለራስ ዓላማ ለማዋል መሞከር ተገቢነት የለውም!

አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት የንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1ሺህ 800 በላይ ጥይቶች እንደተያዙ ህዳር 9 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ፖሊስ የፌስ ቡክ ገፅ እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን መረጃው መተላለፉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የፀጥታ አካላት ከህዝብ ጋር በመተባበር እያከናወኑ የሚገኙትን ውጤታማ ተግባር ለማጣጣል እና ትክክለኛውን መረጃ ከእውነት ሰውረው የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ውሸቶችን እና ሌሎች ተገቢነት የሌላቸውን ወሬዎች እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡

መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተቋማቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ጦር መሳሪያ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ይታወቃል፡፡

ነገር ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ ከተገኙት ጥይቶች መካከል ከ1ሺህ 300 በላይ የሚሆኑት የቡድን መሳሪያ የሆነ የብሬን ጥይቶች ሲሆኑ እነዚህ ጥይቶች ሊገኙ የሚገባው በፀጥታ ተቋማት እጅ ብቻ ከመሆኑም ባሻገር ለተቋማት ጥበቃ አገልግሎት በፍፁም የማይፈቀዱ በመሆናቸው ይህንን በምርመራ ለማጣራት እና ለማረጋገጥ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ ማጣጣል እና ህዝብ በፀጥታ ስራ ላይ እያደረገ የሚገኘውን ተሳትፎ ዋጋ ማሳጣት አግባብ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያምናል ፡፡

በወቅቱ በቁጥጥር ስር የዋለው የንብረት ግምጃ ቤቱ ሰራተኛም የክላሽ-ኮቭ ጥይቶች ናቸው ተብሎ በመዝገብ ፈርሞ እንደተረከበ ለፖሊስ ቃሉን ሰጥቷል፡፡

በብረበራው ወቅት የተቀረፀውን ምስልም ከዚህ ፅሁፍ ጋር የለጠፍነው እውነትን ክደው የሃሰት ወሬ እየፈበረኩ ህዝብን ለማደናገር የሚፈልጉ አካላትን ሴራ ለማጋለጥ ጭምር በመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ለሃሰት መረጃዎች ጆሮ ሳትሰጡ መረጃ እና ጥቆማችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የዘወትር ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ዜናው በከፊል ከኤፍ ቢ ሲ የተወሰደ ነው።

Exit mobile version