ETHIO12.COM

የአሸባሪውን ሸኔ እኩይ አላማ የተረዱ የቡድኑ አባላት በይቅርታ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቀሉ።

በምዕራብ አርሲ ዞን ሄባን አርሲ ወረዳ የአሸባሪውን ሸኔ እኩይ አላማ የተረዱ የቡድኑ አባላት በይቅርታ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቀሉ።

የአሸባሪው ሸኔ ጋር እኩይ ዓላማ የማይጠቅም በመሆኑ ወጣቶች ከቡድኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመተው ህብረተሰቡን በይቅርታ እንዲቀላቀሉ የአካባቢው አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሀደ ስንቄዎች ያቀረቡት ጥሪ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል።

አሁን በይቅርታ ህብረተሰቡን የተቀላቀሉ ወጣቶች ከአሸባሪው ህወሓት የሽብር ተልዕኮ ወስደው ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት በማድረሳቸው መጸጸታቸውን ገልጸዋል።

ወጣት በዳኔ ዋርዮ ዛሬ እጁን በሰላማዊ መንገድ የሰጠው የሽብር ቡድኑን እኩይ ተግባር በመረዳቱ መሆኑን ገልጿል።

ከቡድኑ ጋር መቀጠል እንደሌለበት የተገነዘበው ወጣት በዳኔ ሌሎች ጓደኞቹን በመቀስቀስ ወደሰላማዊ ኑሮ መመለሱን ገልጿል።

ሌሎች ከቡድኑ ጋር የተሰለፉ ወጣቶችም ፈለጉን ተከትለው ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ መክሯል።

ካለማወቅና ግንዛቤ ከማጣት የተነሳ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሰልፎ የነበረው ሌላው ወጣት ጀርመን ቃሲም በተመሳሳይ ወደ ሰላማዊ ህይወት መምጣቱን ተናግሯል።

ሌሎችም ልክ እንደሱ ግንዛቤ ሳይኖራቸው ወደ ሽብር ቡድኑ መቀላቀላቸውን ገልፆ፤ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል።

የሄባን አርሲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወል ዋፎ እንዳሉት፤ ወጣቶቹ በፈጸሙት የሽብር ድርጊት ተፀፅተውና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ዛሬ ከማህበረሰቡ ጋር በይቅርታ መቀላቀላቸው ትክክለኛ ውሳኔ ነው።

ወጣቶቹ በአካባቢያቸው ልማት ንቁ ተሳታፊ በመሆን የበደሉትን ማህበረሰብ እንዲክሱ አሳስበዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሃጂ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወጣቶች የአሽባሪዎች እኩይ ዓላማ በመረዳት እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ መስጠት መጀመራቸው ተናግረው፤ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው የሚገኙ ወጣቶች የጓደኞቻቸውን ፈለግ ተከትለው ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

OBN

Exit mobile version