Site icon ETHIO12.COM

ሱዳን “ተጠቃሁ” አለች፤ በሱዳን በኩል የመጣ ታጣቂ ተደመሰሰ

ሱዳን ኢትዮጵያ እንዳጠቃቻት በማስመሰል “የድረሱልኝ” ጥሪ አቅርባለች። ጥሪዋንና አቤቱታዋን የተለያዩ የአርብ አገር ሚዲያዎችና የምዕራብ መገናኛዎች ተቀብለው አጋርተዋል። ከኢትዮጵያ ወገን በግልጽ ምላሽ ባይሰጥም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል የማጥቃት ሙከራ ቢያደረግም ሙሉ በሙሉ መመታቱ ታውቋል።
ሱዳን ሰልጥኖ ድንበር በጣስ ወደ ኢትዮጵያ ያቀና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል በድንገት ጥቃት መፈጸሙን ከስፍራው ነዋሪዎች ጠቁመዋል። ይህ ሰፊ ቁጥር ያለው የትህነግና ሀይልና የውጭ ዜግነት ያላቸው ታጣቂዎች፣ ድነገተኛ ጥቃት ለማድረግ ቢሞክሩም በስፍራው በንቃት የሚጠባበቀው የመከላከያ ሃይል መብረቃዊ ምላሽ በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንደ ደመሰሳቸው ታውቋል። ሱዳን በዚህ ውጊያ ተሳታፊ የነበሩ ሃይሎቿ ስለተገደሉባት “ተጠቃሁ” ስትል ጩኸት ማሰማቷ ነው የተመለከተው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በተለያዩ ግንባር ደረሰበት የተባለውን ጥቃት ተከትሎ መከላከያ በሱዳን ድንበር የሳሳ ሃይል ያሰለፈ የመሰላቸው ሃይሎች በቅንጅት የከፈቱት ማጥቃት በአጭር ጊዜ ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተመልክቷል። የአገር መከላከያ ኤታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ ለኢሳት እንዳስታወቁት ” እኛ ሱዳንን የምናጠቃበት ምክንያት የለም” ካሉ በሁዋላ ” ሙከራ የሚያደርጉ ካሉ ራስን መከላከል ግድ ነው” ሲል አስታወቀዋል። የተገዙ ሃይሎች እንጂ ሱዳንና ኤትዮጵያ ሁሌም ችግራቸውን በሰላማዊ መነገድ የሚፈቱ ወዳጅ አገሮች መሆናቸውን አመልክተዋል።

የትህነግን ሃይል ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ሽፋን ሊሰጥ የሞከረው መሆናቸው የተገለጸላቸው የሱዳን ወታደሮች አብሮ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከመገለጹ ውጭ ሰራዊቱ ዘልቆ ወደ ሱዳን ስለመግባቱ የተባለ ነገር የለም።

አል አለሚና የገዳሪፉ አልሰባህ የተሰኘው ሚዲያ የኤርትራ፣ የአማራና የኢትዮጵያ ሀይል በጥምረት ሆነው የሱዳን ወታደሮች ላይ ተኩስ ከፍተው ብዙ ወታደሮች መግደላቸውን እንደዘገቡ ሱሌማን አብደላ ትርጉሙን አስፍሯል። ይህንን ፕሮፓጋንዳ ሮይተርስን ጨምሮ የአረብ አገራ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል። የሱዳን ወታደሮች ሽፋን ለመስጠት በተነደፈ ኦፕሬሽን መመታታቸውን ለማስተባበልና ” ተጠቁ” ለማለት የተሰራጨውን ዜና አስመልክቶ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

Exit mobile version