Site icon ETHIO12.COM

የጭካኔ ጥግ – በጣርማ በር መዘዞ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ በወረራ በቆየባቸው የአማራን የአፋር ክልል የፈጸመውን አስከፊና አስነዋሪ ተግባር ለመዘርዘር በርካቶች እንደሚቸገሩ በርካቶች እየተናገሩ ነው። በአፋር ንጹሃን ተጭፍጭፈዋል። መስጊድ ነዷል። ቁራን ተቃጥሏል። በርካታ ህጻናትና አረጋዊያን ቆስለው እርዳታ ሲደረግላቸው ታይቷል። የጅምላ አስገድዶ መድፈሩም እጅግ ጸያፍ ስለመሆኑ ከስፍራው የውጭ ሚዲያዎች ሳይቀሩ ሳይወዱ በግዳቸው አስታውቀዋ።

በአማራ ክልልም ነጻ በወጡ ከተሞች ነዋሪዎች ምን ሲደረጉ እንደነበር ሲመስክሩ ስሜትን የሚያንቅ ነበር። ዛሬ ከመዘዞ ጣርማ በር ነዋሪዎች የደረሰባቸውን ጠቁመዋል። ኢዜአ ከአዛዞ የዘገበውን ዝዝሩን ከስር ያንብቡ

“ኦፕራሲዮን ነበርኩ ሁለተኛ ሆዴን በጩቤ ሊቀዱት ሲሉ መከላከያ ደረሰልኝ” በማለት በጣርማ በር ወረዳ የመዘዞ ከተማ ነዋሪ የሆኑት መምህር አለምሸት ተፈራ የአሸባሪውን ህወሃት የጭካኔ ጥግ ገለጹ።የአሸባሪው ህወሃት ወራሪዎች ንጹሐንን በዱላ እንደሚቀጠቅጡም መምህር አለምሸት የደረሰባቸው መከራ አስከፊ መሆኑን በመግለጽ አብራርተዋል።

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች የሚያደርገውን የንጹሃን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት በሰሜን ሸዋ መዘዞ ከተማም ደግሞታል።

የሽብር ቡድኑ በጣርማበር ወረዳ መዘዞ ከተማ በቆየባቸው ቀናት ከዶሮ ጀምሮ የማሕበረሰቡን እንስሳት እያረደ በልቷል።

በከተማዋ ያሉ ሱቆችን ሙሉ በሙሉ ዘርፎ የቀረውን አውድሟል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ፋኖና ሚሊሻ አባላትን ምት መቋቋም ተስኖት ሲፈረጥጥ ዛሬም እንደትናንቱ ሁሉ ንጹኃንን በመግደል አረመኔነቱን አሳይቷል።

የመዘዞ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መኮንን አበሩ እንዳሉት፤ ወደ ከተማዋ ከገቡ ጀምሮ የንግድ ቤቶችን በኀይል እየሰበሩ ንብረት ጭነው ወስደዋል።

እቤታቸው በተቀመጡበት የመሳሪያ አፈሙዝ ግንባራቸው ላይ ተደቅኖ ኪሳቸው እንደተበረበረና የያዙት ገንዘብ እንደተወሰደባቸውም ተናግረዋል።

ይህ ብቻ አይደለም ቤት ያፈራውን ሁሉ መብላት መጠጣታቸው አልበቃ ብሎ የሚደፈሩ ሴቶች እንዲያመጡላቸው በመጠየቅ ከፍተኛ ስቃይ የሚያደርስ ድብደባ ፈጽመውባቸዋል።

ሌላው የከተማዋ ነዋሪ መምህር አለምሸት ተፈራ የደረሰባቸውን እንግልት ሲገልጹ “ሶስት ሆነው ወደ ቤቴ መጡ አንደኛው መሳሪያ አቀባብሎ ግንባሬ ላይ ደገነ፤ ሁለተኛው ሆዴ ላይ ጩቤ አነጣጠረ፣ ሽጉጥና ሌላ መሳሪያ አለህ አምጣ ሲል አስጨነቀኝ” ብለዋል።

“በሁተኛው ቀን ከቤቴ ውስጥ እንዳለሁ ከውጭ ቆለፉብኝ በመስኮት ስወጣ በመሳሪያ እያስፈራሩ የዱላ መዓት አወረዱብኝ” ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት መስማት የማትችል ህመምተኛና ምስኪን ሴት አስገድዶ በመድፈር የአረመኔነት ግብሩን በተግባር አሳይቷል።

የዚህ ጥቃት ሰለባ የሆነችው ይህች ሴት “ከአካል ጉዳተኛዋ ጓደኛዬ ለይቶ ወሰደኝ፣ ራሴን የማላውቀው ቤት ወድቄ አገኘሁት፣ በከተማው ምን ሲካሄድ እንደነበር አላውቅም፣ ከቀናት በኋላ ነው ወጥቼ መንቀሳቀስ የቻልኩት” ብላለች።

በመዘዞ የቀድሞ የፖሊስ አባል የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ግለሰብ በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በጭካኔ ተገድለዋል። በከተማዋ የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆነው ወድመዋል፣ የተዘጉ ቤቶች በራቸው በሀይል ተከፍቶ እቃዎች ተዘርፈው የቀሩት አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ ተደርገው ተበታትነዋል።

Exit mobile version