Site icon ETHIO12.COM

ከክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የቀረበ ጥሪ «መሪውን ያጀገነ ህዝብ የታሪክ ተቋዳሽ ይሆናል!»

በኢትዮጲያ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመተባበር ባደረገው ተጋድሎ ኢትዮጲያን በደምና አጥነት ጠብቆ ያቆየ ህዝብ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡

በዚሁ ሀገረ-መንግስት ግንባታ፤ ሀገራዊ ነጻነትና ሉኣላዊነትን አስጠብቆ ለማስቀጠል በተደረገው ተጋድሎ በርካታ መሪዎችን ያፈራና ያጀገነ፤ በነዙሁ ጀግኖች መሰዋትነት ኢትዮጲያ ታፍራና ተክብራ እንድትኖር ያደረገ ህዝብ ነው፡፡

በሁሉም የትግል አውድ የተፈጠሩ የኦሮሞ ጀግኖች በአሸናፊነታቸው ሀገራቸው ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ መድረክ ስሟ ገኖ እንዲናኝ፤ ሰንደቋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ፤ ስመ ገናና ኩሩ የጀግኖች ሀገር ሆና እንድትታውቅ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ወታደር ሆነው ጦር በመምራት ወራሪና ከሃዲ ባንዳን የሀፍረት ካባን አከናንበዋል፡፡ በአለም አቀፍ አስፖርታዊ ውድድሮች ኢትዮጲያን ከፍ አድርገዋታል፡፡ በግብርናውም አርሰው ከማብላት አልፈው ለሀጋራዊ ምጣኔ ሀብት የብረት ምሰሶ የሆኑ በርካታ ጀግና አርሶ አደሮችም ተፈጥረዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ በሚወዳት ሀገር ህልውና እና ሉአላዊነት ላይ አደጋ በተጋረጠበት ዘመን ሁሉ መሰዋትነት በመክፈል ሀጋረዊ ህልውና እንዲቀጥል ለመሰዋትነት የሚሽቀዳደሙ ጀግኖችን ያፈራ ህዝብ ነው፡፡

የኢትዮጲያዊያን እልፍ አላፍ የጀግንነትና የአልበገሬነት አርማ፤ የጥቁር አፍሪካዊያን የነጻነት ተምሳሌት የሆነው የድዋ ድል ታሪክ በአለም ድንቅ የታሪክ መዝገብ እንዲመዘገብ በተደረገው ሁሉ አቀፍ ተጋድሎ የኦሮሞ ጀግኖች ከፍተኛ አስተዋጽዎ አድርገዋል፡፡

ይህ በመሆኑም በጥቁሮችና ነጮች መካከል የነበረው የበታችነትና የበላይነት መሰተጋበር ምዕራፉ በመዘጋት የነጻነትና የእኩልነት ጸሃይ በአፍሪካ ምድር እንዲፈነጥቅ ምክንያት ሆኖዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የነ አድዋ፤ ማይጨው፤ ካራማራና የመሳሰሉት የጀግኖች ውሎ ማስታወሻ ህያው ምስክር ናቸው፡፡

ከቅርብ ታሪክ አንጻርም የኦሮሞ ቄሮ እና ቀሬ እስናይፐር ሳይበግረው፤ እስርና እንግልትን ሳይታክት፤ የወንድሙና እህቱ ሞት ይባሱኑ እንደብረት ጠንክሮ በመቆም በከፈለው ከፍተኛ መሰዋትነት ለ 27 አመታት የኢትዮጲያን እዝብ ሲዘረፍና ሲያሰቃይ የኖረውን ስግብግብ ጁንታ ከስር መሰረቱ በመንቀል ለኦሮሞ ህዝብና ለመላው የኢትዮጲያ ህዝቦች የሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥ ጉልህ ድርሻ አበርክተዋል፡፡

ዛሬም እንደትላንቱ የተደቀነብንን ሀጋራዊ የህልውና አደጋ ለመመከት እየተደረገ ባለው ሁሉ አቀፍ ተጋድሎ የኦሮሞ ወጣቶች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ያስተላለፉትን ሀገር አድን ጥሪ በመቀላቀል የወያኔና ግብረ አበሮችን ቀብር ለማፋጠን በጀግንነት ወኔ ለሀጋራዊ ክብር መሰዋትነት በመሽቀዳደም ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህም ዛሬም እንደትላንቱ የአባቶቻቸውን የጀግንነት ፈለግ የተከተሉ ጀግና ሆነው የሚያጀግን አዲስ ተውልድ መፈጠሩን ያሳያል፡፡

ሀጋረዊ ነጻነነትና ሉኣላዊነትን ማስከበር የሁሉም ተውልድ ግዴታ ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ይህ ተውልድ ጀግኖ የሚያጀግን መሪ ታድሎዋል፡፡ ከጀግና መሪ ጎን የቆመ ህዝብ ደግሞ ታሪኩን ያድሳል፡፡

ገናና፤ነጸና አይበገሬ ህዝብ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ መሪውን የበለጠ ያጀግናል፡፡መሪውን ያጀገነ ህዝብ የታሪክ ተቋዳሽ ይሆናል ፡፡

በመሆኑም የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ የ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ የጀግንነት ፈለግ በመከተልና የሀገር መከላከያን በመቀላቀል ዘሬም እንደትላንቱ የባቶቻችሁን የጀግነነት ታሪክ እንድትደግሙ በ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስም ጥሪዬን አስተላልፋለው፡፡

ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት
ህዳር 22/2014
ፊንፊኔ

Exit mobile version