Site icon ETHIO12.COM

ሁለተኛው ዘመቻ ማረፊያው መቀለ እንደሚሆን ይፋ ሆነ፤ ትህነግ እርስ በርስ መካሰስ መጀመሩ ተሰማ

ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግት እንደሆነ በተነገረለት የግንባር ንግግር ቀጣዩ የድል ሜዳ መቀለ እንደሆነ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታወቁ። “ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን “ሲሉ ያስታወቁት የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ “የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁ ዜና ነው” ብለዋል። ትህነግ ” የአብይ መውደቂያው እየተፋጠነ ነው” ሲል፤ ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ በውጥ መካሰስ መጀመሩን አስታወቀዋል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ዘመቻ በመከላከያ፣ በአማራና በአፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ በድል መጠናቀቁን የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ አሕመድ ሲያስታውቁ፤ ቀጣይ ዘመቻ እንደሚኖር ከመጠቆማቸው ውጪ ዝርዝር ጉዳይ አላነሱም ነበር። ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ትህነግ ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል እንደሚደረግ አስታውቀው ነበር።

ይህ ተከትሎ በጦር ግንባር በተካሄደ መድረክ ከፍተኛ መኮንኖች፣ አየር ወለዶችና ኮማንዶዎች እንዲሁም መላው በግናባሩ ያሉ መለዮ ለባሾች ፊት ቆመው “የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን” ሲል ቀጣዩ ዘመቻ ማረፊያው የት እንደሆነ አመልክተዋል። ጄነራሉ ሁሉንም ተዋጊ ሃይሎች በአጠቃላይ “የልዩ ዘመቻዎች ኃይል” ብለው ከተሩ በሁዋላ፣የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይልና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አጉልተው ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ የሽብር ቡድኑን የመደምሰስ ግዳጅ በድል መገባደድና ለቀጣይ ወሳኝ ተልዕኮ መነቃቃትን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ በግንባር በተካሄደ መድረክ ላይ ሌተናል ጄነራል ባጫ ይህን ማለታቸው ከየአቅጣጫው ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በወረራ የተያዙ አካባቢዎች ነጻ ከወጡ በሁዋላ የተፈጸመው ወንጀል፣ ዝርፊያና ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም አስገድዶ መድፈርና ውድመት ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ትህነግ እንደ ድርጅት እንዳይቀጥል የመንግስት ቀጣይ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል ሲጠበቅ ነበር።

ቀይ መለዮ ለባሾቹ በወሳኝ ወቅት አስቸጋሪና ፈታኝ ግዳጆችን በድል በመወጣት በደማቅ ቀለም የተፃፈ ታሪክ መስራታቸውን ገልጸው ጄነራሉ እንደተናገሩት ብቻ ሳይሆን በግንባር የተገኙ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮሽ ሳይቀሩ የሪፕብሊካን ጋርድና አየር ወለዶች በጦርነቱ ወቅት የፈጸሙትን ግድልና ፕሮፌሽናል ወታደራዊ ብቃት ታሪክ ወደፊት እንደሚገልጸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

“ጀግኖቹ ከሰሞኑ በጣርማበርና ዙሪያገባዎቹ የፈፀሙት አንፀባራቂ ድል የጠላትን ቅስም የሰበረ” ሲሉ የጠቀሱት ሌተናል ጄኔራል ባጫ አሁንም የደም የመስዋዕትነትና የድል አድራጊነት ምልክት የሆነውን ቀይ መለዮዋቸውን አጥልቀው ለዳግም ድል መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋቸዋል።

የልዩ ዘመቻዎች፣ የሪፐብሊኩ ኃይል፣ አየር ወለዶችና በዘመቻው የተሳተፉ ሁሉም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በህብረት የምድር ላይ ድሮን መሆናቸውን አስመስክረዋል ብለዋል። አክለውም ” የኅልውናችን ጠንቅ ሆኖ በአንዳንድ ፅንፈኛ ምዕራባዊያን የሚጋለበውን የሕወሓት ሽብር ቡድን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን” ብለዋል።

የትግራይ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ህዳር 30/2014 ዓ.ም ” የጠላት ዕድሜ በአጭር ጊዜ ለመቋጨት… የሰራዊት አመራሮች ፋሽስቱ አብይ ቡድን እንደ ሰማይ የራቀውን ድል አሰፍስፎ ለማዲያ ፍጀታ ለማዋል ሲፍጨረጨር ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ደግሞ የጠላትን ሃይል የተለያየ ወታደራዊ ስልት ተጠቅሞ በማዳከም ከዚህም ከዚያም የተሸመቱ የጦር መሳሪያዎች እየተረከበው መሆኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች ገለፁ ሲል ትግራይ ቴለቪዥ ዘግቧል። አመራሮቹ ሰራዊቱ እንደጀመረው በአጭር ጊዜ የጠላት ዕድሜን ያሳጥራልም ብለዋል። ትግራይ ታሸንፋለች!!” ሲል በፌስ ቡክ ገጹ ጽፏል።

ድርጅቱ ይህን ቢልም ተከቦ መውጫ ያጣው ሰራዊት እጁን መስጠት መቀጠሉን፣ በርካታ ሺህ ምርኮኞች መንግስት በቅርቡ ይፋ እንደሚያድረግ ተሰምቷል። ግንባር ላይ ያሉም መስክረዋል። የመንግስ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በደርጅቱ ውስጥ መካሰስ መጀመሩንና ቤተሰብ “ወደ ትግራይ ካፈገፈጋችሁ ልጆች የት አሉ” ሲል እየጠየቀ መሆኑንን መረጃ እንደደረሰው አስታውቋል።

በሌላ በኩል የድርጅቱ የውጭ ክንፎች ጋር ቅርበት ያላቸውን ጠቅሶ የአሜሪካ ተባባሪያችን እንዳለው ትህነግ በውጭ ሊፈነዳ የተቃረበ ጉምጉምታ፣ በውስጥ ከፍተኛ አመራሮቹ እርስ በርስ መካሰስ መጀመራቸው ተሰምቷል። ከክልላቸው በመውጣት ተበትነው ለደረሰባቸው ከፍተኛ የሰው ሃይል ኪሳራ አንዱ ሌላው ላይ “ታክቲካል ስህተት ሰርተሃል” በሚል መወነጃጀል መጀመራቸው ተሰምቷል።

Exit mobile version