Site icon ETHIO12.COM

“የከሀዲዎችና የሰርጎ ገቦችን ጉዳይ ህጋዊ እልባት መስጠት ይጠበቅብናል” አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም

“ዛሬ በድጋሜ ደስ ብሎኛል!” ሲሉ ባሰራጩት ጽሁፍ የአብን ብክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም በደሴና ኮምቦልቻ እንዲሁም በሁሉም አቅጣጫ “የከሀዲዎችና የሰርጎ ገቦችን ጉዳይ ህጋዊ እልባት መስጠት ይጠበቅብናል” ሲሉ አምረው አስታወቁ። “እኛ እያንዳንዷን የወንጀል ፍሬ ነገር እንመዘግባለን፣ ሰንደን እናቀርባለን፣ ፍትህም እንጠይቃለን” ብለዋል።

ሁሉም የስራውን ውጤት ያገኛል። በመካከል የሽብርተኛ አማላጅ ለመሆን መሞከር አያዋጣም፣ ግብዝነት ነው፣ ከወዲሁ እጃቸውን መሰብሰብ አለባቸው። ጣራ እና ግርግዳቸውን በእሳት እየለኮሱ ባቃጠሏቸው ቤተ-እምነቶች ውስጥ ዳግም ሊደበቁና ከለላ ሊያገኙ አይችሉም!

አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም

“ወራሪው ሃይል የሽብር እርሾ እንዳይተርፈው በማድረግ በቋሚነት ልናሸንፈው ይገባል” ያሉት አቶ ኢብራሂም፣ የ1983 ቱን ጨምሮ በሳቸው እድሜ መሰለ ዘረፋ ሲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ይህ በአይነቱ ለየት ያለና ቂምና ጥ፤አቻን እንሣትን ሳይቀር በመግደል የተከናወነ እንደሆነ በአባታቸው መኖሪያ ቤት የሆነውን ጠቅሰው አመልክተዋል። አባትና እናታቸውንም ከግድያ ሙከራ በሁዋላ ማግኘታቸውን አመልክተዋል።

“ወራሪዎቹ ተሸንፈው ሲሸሹ ቀደም ሲል ያሰባሰቧቸውንና ራሳቸው ‘ሁለተኛ ደረጃ ተጋሩዎች’ ሲሉ የሰየሙትንና ትህነግ ‘የሸኔ ምልምሎችና ጀሌዎች’ የሚሏቸውን ሁሉ ‘እንዳትከተሉን’ የሚል ትዕዛዝ በመስጠት በየጫካው በትነዋቸውቸው ሄደዋል” ሲሉ የጥምረቱን መጨረሻ ያሳዩት አቶ ኢብራሂም፣ “ትህነግና ጀሌው አሁን ተዳክመው፣ ተስፋ ቆርጠውና በየስርቻው ወድቀው በሰልፍ እየመጡ ለወገን ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

“ለማንኛውም ሁሉም የስራውን ውጤት ያገኛል” ካሉ በሁዋላ “… በመካከል የሽብርተኛ አማላጅ ለመሆን መሞከር አያዋጣም፣ ግብዝነት ነው፣ ከወዲሁ እጃቸሁን መሰብሰብ አለባቸው። ጣራና ግርግዳቸውን በእሳት እየለኮሱ ባቃጠሏቸው ቤተዕምነቶች ውስጥ ዳግም ሊደበቁና ከለላ ሊያገኙ አይችሉም” አይችሉም ሲሉ ለማስታረቅ በሚል እዛና እዚህ የሚረግጡትን አስጠንቀቀዋል።

“ዛሬ ደስ ብሎኛል” ሲል ያጋሩት ጽሁፍ ሙሉ ቃል ከስር ቀርቧል።

የወያኔ ሰርጎ ገቦች እኔንና ጓዶኞቸን ለመያዝ ወይም ለመግደል በሚሯሯጡበት ወቅት እኔ አባታችንን ከአካባቢው ለማስወጣት ጥረት አድርጌ ነበር። ነገር ግን ሁኔታዎች በፍጥነት ስለተቀያየሩና አስቻይ ስላልነበሩ በኪሴ ውስጥ የነበረውን የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቸው እና አጭር መልዕክት ተለዋውጠን ተለያየን ነበር።

በተለይ የእግር ህመም እንዳለበት ስለማውቅ ራቅ ወዳለ አካባቢ ለመጓዝ ችግር እንደሚገጥመው ሳስብ ረፍት ነስቶኝ ከረምኩ። እንቅልፍ ያጣሁባቸው በርካታ ሌሊቶች ነበሩ!

ሆኖም አባታችን ወዲያው አካባቢውን ለቅቆ በመውጣት የተወረረበትን ጊዜ እንደዋዛ አሳልፎ በሰላም ተመልሷል። አሁን ዓመለ-ሸጋውንና ዘወትር ተናፋቂውን አባት ኢብራሂምን አግኝተነዋል፣ አልሀምዱሊላህ!

ጥርጣሬ እና ስጋቴ ልክ ነበር። እነ ጌታቸው ረዳ ያሰማሩት ወራሪ ሀይል እሰፈራችን እንደ ደረሰ ወዲያውኑ ተንደርድሮ የገባው ወደ አባታችን መኖሪያ ቤት ነበር። ግን አባታችንን ቤት ውስጥ አላገኙትም። (እናታችን ከአካባቢው የለቀቀችው ቀድማ ነበር)

ሆኖም ቤቱን ሰብረው የቤት እቃቸውን ሁሉ ዘርፈው ከወሰዱ በኋላ እንደገና በድጋሜ ተመልሰው የቤት እንስሳቱን (የእርሻ በሬ ጭምር) በጥይት ገድለዋል። በወቅቱ ጥጋብ ላይ ስለነበሩ እንስሳቱን ከገደሉ በኋላ ጥለው ሄደዋል፣ አርደው አልበሉም! (የጥላቻ ስሜታቸውን እንስሳቱን በመግደል ገልፀዋል)።

ወራሪው ሀይል በተመሳሳይ 1983 ዓ.ም ከሰፈራችን ህዝብ በርካታ የወተት ላሞችን ዘርፎ እንደነበር አስታውሳለሁ። የአሁኑ ወረራ በእኛ እድሜ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈፀመ መሆኑ ነው! ግን የዘንድሮው የከፋ ነው፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች የወረራው አይነተኛ መገለጫዎች ናቸው!

ከአንድ አካባቢ የሚነሱ ወራሪዎች የወሎን ህዝብ ለተደጋጋሚ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ውድመቶች ዳርገውታል። የወራሪዎቹ አላማ የህዝባችንን ሰብዓዊ፣ መንፈሳዊ፣ ቁሳዊ፣ ባህላዊ፣ ኪነጥበባዊና ታሪካዊ ስልጣኔዎች ለማጥፋት፣ ህዝባችንን እሴት አልባና ቋሚ ተሸናፊ ለማድረግ የታሰበ ነው። ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት የምናደርገው የህልውና ዘመቻ ወራሪውን ሀይል ሰተት ብሎ እንዲወጣ ለማድረግ አይደለም፣ ወራሪውን ሀይል ለማሸነፍ ብቻም አይደለም። የሽብር እርሾ እንዳይተርፈው በማድረግ በቋሚነት ልናሸንፈው ይገባል!

ከገዳዩና ዘራፉው ስብስብ በተጨማሪ የከሀዲዎችና የሰርጎ ገቦችን ጉዳይ ህጋዊ እልባት መስጠት ይጠበቅብናል። በተለያዩ አግባቦች በር እየከፈቱ ተጋላጭ የሚያደርጉንን ስርዓት ማስያዝ ያስፈልጋል። ቸልተኛ እና ዝንጉ ማህበረሰብ ዘወትር ተጋላጭ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። የህዝባችንን ፅኑ ጉዳይ የፉክክር ቤት ማድረግ የለብንም። አሁን ባለፈው ስህተት ልንቆጭ ይገባል፣ ያለፈው ይበቃናል ማለት አለብን! ማህበረሰባዊ ማንነታችን፣ ክብራችን እና ታሪካችን ከጎደፈ በግለሰብ ደረጃ ማንም ሰው የተሟላ ግርማ ሞገስ እንደማይኖረው ይታወቃል!

በነገራችን ላይ ወራሪዎቹ ተሸንፈው ሲሸሹ ቀደም ሲል ያሰባሰቧቸውንና ራሳቸው “ሁለተኛ ደረጃ ተጋሩዎች”፣ “የሸኔ ምልምሎችና ጀሌዎች” የሚሏቸውን ሁሉ እንዳትከተሉን የሚል ትዕዛዝ በመስጠት በየጫካው በትነዋቸውቸው ሄደዋል። አሁን ተዳክመው፣ ተስፋ ቆርጠው እና በየስርቻው ወድቀው በሰልፍ እየመጡ ለወገን ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

ለማንኛውም ሁሉም የስራውን ውጤት ያገኛል። በመካከል የሽብርተኛ አማላጅ ለመሆን መሞከር አያዋጣም፣ ግብዝነት ነው፣ ከወዲሁ እጃቸውን መሰብሰብ አለባቸው። ጣራ እና ግርግዳቸውን በእሳት እየለኮሱ ባቃጠሏቸው ቤተ-እምነቶች ውስጥ ዳግም ሊደበቁና ከለላ ሊያገኙ አይችሉም!

“የደሴ እና የኮምቦልቻ ህዝብ አልተዘረፉም ያለው ማን ነበር?” ባካችሁ “የሌባ አይነ ደረቅ መሆን ይደብራል በሏቸው” ጉና ተራራ እንደ ነበረው ምርኮኛ በባዶ ሜዳ መዋጀጅ ጥሩ አይደለም! እኛ እያንዳንዷን የወንጀል ፍሬ ነገር እንመዘግባለን፣ ሰንደን እናቀርባለን፣ ፍትህም እንጠይቃለን!

አቶ ጌታቸው ረዳ አቶ የሱፍና ባልደረቦቻቸው፣ የአብን አመራሮችና አባላት የትህነግን ወረራ ለመመከት ሲንቀሳቀሱ ” ውርጋጦች እናገናችኋለን” በሚል በትግራይ ሚዲያ ሃውስ ዝተዋባቸው ነበር። በማህበራዊ ገጻቸውም ይህንን ጠቅሰው ጽፈው እንደነበር ይታወሳል።

Exit mobile version