Site icon ETHIO12.COM

“ኦነግ ሸኔ ምክንያት አልባ፣ በየጫካው እየተሹለከለከ ንጹሃንን የሚገድል በአንቂዎች ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ የመንደር ሽፍታ ነው”

“ከ400 በላይ ተገድለዋል፤ 165 እጅ ሰጥተዋል፣ ይህ ነው የሚባል አመራር የለውም፤ ያሉትም እየተመቱ ነውና ቡድኑ እየከሰመ ነው ” የጦር መኮንኖች ከስር ባለው ፊልም ከገለጹት የተወሰደ

ኦነግ ሸኔን በማስተዋወቅ ደረጃ የአማርኛው ቪኦኤ ሬዲዮ ቅድሚያ እንዳለው ብዙዎች ይተቻሉ። ማንነቱና አድራሻው የማይታወቅ ሰው በተደጋጋሚ እያቀረቡ ማስታወቂያ የሰሩለት ኩማ ድሪባ ወይም ጃል መሮ የሚመራው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ “… ምክንያት አልባ፣ በየጫካው እየተሹለከለከ ንጹሃንን የሚገድል በአንቂዎች ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ የመንደር ሽፍታ ነው” ሲል መንግስት ይገልጸዋል።

“የወታደራዊ ክንፉ መሪ ነኝ” ብሎ ጃልመሮ በተደጋጋሚ ለቃለ ምልልስ ቪኦኤ ላይ ሲቀርብ፣ አንድም ቀን እንደ ፖለቲካ ድርጅት መሪው ማን እንደሆነ እንዲያብራራ፣ በምንና እንዴት አዲስ አበባ ካለው ኦነግ ጋር እንደሚለይና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች፣ ” ለመሆኑ አንተ ማን ነህ? እንዴትስ እንመንህ?” በሚል ጠልቆም በመጠየቅ በወጉ እንዳላስተዋወቀው እነዚሁ ወገኖች ቪኦኤን አጠንክረው ይቃወሙታል።

“የአምቦው ልብ” የሚባለው ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደሉን ተከትሎ አስቀድሞ እንደሚገሉት ከኦነግ ሸኔ አባላት የድምጽ የስክል ማስፈራሪያ ተልኮለት እንደነበር ከነ ደዋዩ ምስል ይፋ እንደሆነ ቪኦኤ ጃልመሮን ጋብዞ ነበር። በፕሮግራሙ ጃልመሮ ” ከፖለቲካዊ ሞት ዳነ” እስኪባል ድረስ ቪኦኤ የሰራው ማስተባበያ በረካቶችን አነጋግሮ ነበር።

እንደ ቪኦኤ ሁሉ ቢቢሲ አማርኛውን አዘውትሮ በመጠቀም በወለጋ አካባቢዎች በንጹሃን ላይ ከሚፈጸመው ጥቃትና ማፈናቀል ” የለንበትም” የሚለውን መረጃ የሚያሰራጨው ” ሲያሻውም ” ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዘልቀው አምራውን የሚገሉት የአማራ ክልል ወታደሮች ናቸው” በሚል የሚናገርባቸው ሚዲያዎች ተግባር በድብቅ ተይዞ የነበረው ትህነግና ኦነግ ሸኔ ቀድሞውንም አንድ ዓይነት ድርጅት መሆናቸው ይፋ እንደሆነ የተቹ “ለካ ቅስቀሳው ለዚህ ነው” በማለት ” ተልዕኮው ” በሚዲያዎቹ ቀጣሪዎች የተሰጠ መሆኑንን “ልብ ያለው ልብ ይበል” ሲሉ አምልክተዋል።

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ” ዛሬ ኦሮሞ ነፍጥ ይዞ ጫካ የሚገባበት ምድራዊ ምክንያት የለውም” ሲሉ እንዳስታወቁት፣ የኦነግ አመራር ከነበሩት መካከል ” ሁለት መንገድ አጣቅሰን አንጓዝም” በሚል የተለዩ ዘርዝረው እንዳስረዱት፣ በርካታ የኦሮሞ ምሁራን እንዳብራሩት ኦነግ ሸኔ ምድር የጨበጠ የትግል ዓላማና ግብ የለውም።

ጃል መሮ በቪኦኤና በቢቢሲ “ኦሮሞን ከብልጽግና ነጻ እናወጣለን” የሚለውና የኦሮሞ ሕዝብ ከቀድሞው በበለጠ መጨቆኑንን የሚገልጸው ጃል መሮ ይህንኑ ዓልማ ለማሳካት ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ጋር መስማማታቸውን ማስታወቁ ይታወሳል። በዚህም ሕብረት አሁን ክልሉን የሚመሩትን የኦሮሞ ልጆች ለፍርድ ያቀርቧቸው ዘንድ ከትህነግ ጋር ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ እንደሆነ፣ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ጥቂት ኪሎሜትሮች እንደቀሩት በታዋቂ ሚዲያዎች፣ አገራት፣ ሰዎችና የትህነግ ሚዲያዎች የተነገረለትን ድርጅት ዛሬ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ” የመንደር ሽፍታ” ብለውታል።

“ሸኔ በባህሪዉ የተደራጀ የፖለቲካ ዓላማና ለትጥቅ ትግል የሚያበቃዉ ይህ ነዉ የሚባል መሠረታዊ ምክንያት የለዉም” ያሉት ዶክተር ለገሰ፣ ኦነግ ሸኔ በግለሰቦችና በማኅበራዊ አንቂዎች ያልተገባ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ህዝባዊና የጋራ ዓላማ የሌለው እንደሆነ ተናግረዋል። “በትጥቅ ዐቅሙም ይሁን በተዋጊ ኃይል ቁመናዉ እዚህ ግባ የማይባል ነው” ሲሉ የገለጹት ሸኔ “በየጫካዉ እየተሸሎከለከ ሰዎችን በማንነታቸው እየገደለ፣ ሀብት ንብረታቸዉን የሚዘርፍና የሚያወድም የመንደር ሽፍታ ነዉ” ሲሉ እንደ ድርጅት እንደማይቆጠር አብራርተዋል።

“ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ሀገርን ለማፈራረስ ከትህነግ የጁንታ ቡድን ጋር በጥምረት እየሠራ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ቡድን በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ ቢገኝም በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ሕልሙ እየመከነ ይገኛል” ሲሉ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። አያይዘውም ” ሸኔ በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ታዋቂ ሰዎችን፣ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎችን በመግደል የፖለቲካ ትርፍ ለመግኘት የሚሞክር የሽፍታ ቡድን ነው” ብለዋል። “ቀን ቀን ሰላማዊ ነዋሪ እየመሰሉ፣ የጸጥታ ኃይሎች በሌሉበት ደግሞ እንደ ሽፍታ በየመንደሩ እየዞሩ ንጹሐንን የሚገድሉ የሽፍታና የሽብር ፈጻሚዎች ስብስብ ነው” ሲሉ የገለጹት ኦነግ ሸኔ እየተደመሰሰ መሆኑንን ተናግረዋል።

ኦነግ ሸኔ ላይ የፌደራል ፖሊስና ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከፍተኛ ርምጃ መውሰዳቸውን፣ ርምጃዉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ ኅብረተሰቡም ተደራጅቶ ከአካባቢዉ የሚሊሺያ ኃይል ጋር በመሆን አካባቢዉን እነዚህ የሽብር ቡድኖች ማጽዳት እንዳለበት፣ ለዚህም በስፋት ሕዝብ ያሳተፈ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ከሚኒስትሩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል። የትግል አጋሩ በጦር ሜዳ የደረሰበትን ሽንፈትና ኪሳራ ላለመቀበል የትግል ስልቱን ቀይሮ ወደ መቀለ መግባቱን ይፋ ሲያደርግ ኦነግ ሸኔ እስካሁን “ከአዲስ አበባ 40 ኪሎሜትና 30 ኪሎ ሜትር አድፍጫለሁ” እንዳለው እዛው ይሁን ወደ ወለጋ ይመልስ በግልጽ ያስታወቀው ነገር የለም። ኦነግ ሸኔ ይህን ቢልም አዲስ አበባ ዙሪያም ሆነ በቅርብ ርቀት ይህ እስከታተመ ድረስ ስጋት እንዳልተፈጠረ ነዋሪዎች ” ማንን እንመን?” ሲሉ የሰላማቸውን ብዛት እየገለጹ ነው።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ዛሬ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱዋና ዋና ሐሳቦች ከተቋማቸው ማህበራዊ ገጽ ላይ ተወስዶ እንዳለ እንደሚከተለው ከታች ቀርቧል።

• የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የተጀመረዉ ከፍተኛ የማጥቃት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አሸናፊነታቸዉን በማረጋገጥ ወደፊት የሚያደርጉትን ግሥገሤ ቀጥለዋል፡፡

• ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም የመጀመሪያ ምእራፍ የግንባር ቆይታቸውን አጠናቅቀዉ ለቀጣይ ሥራቸዉ ዝግጅት ለተወሰነ ጊዜ ወደ ቢሯቸዉ ተመልሰዋል።

• ይህ ዘመቻ የኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ጎልቶ የታየበት፣ ሉዓላዊነታቸዉን ለማስከበር ከውስጥ የተነሡ ባንዳዎችንና የዉጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን ለመመከት ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር ያለ ልዩነት አንድ ሆነዉ የቆሙበት ዘመቻ ነው

• በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተመራዉ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በጠላት ምሽጎችና ወረዳዎች በጥልቀት ዘልቆ በመግባት የአሸባሪውን ጀሌዎች እየለቀመ፣ እየማረከና እምቢ ያሉትን እየደመሰሰ ይገኛል።

• የሽብር ቡድኑን በማስወገድ ረገድ ስኬታማ በነበረው ዘመቻ ነጻ በወጡ አካባቢዎችም የመንግሥት አስተዳዳር ወደ ቦታዉ እንዲመለስ ተደርጓል። የወደሙ መሠረተ ልማቶችን የመጠገንና እነዚህን አካባቢዎች ወደ ተሟላ ሥራ ለማስገባት የሁሉንም አካላት ርብርብ ስለሚጠይቅ ኅብረተሰቡም ሆነ የኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግሥት ጥሪ ያቀርባል፡፡

• ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ያወጣውን መመሪያ በተመለከተ ከዳያስፖራው የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉ። ብዥታው የተፈጠረው መመሪያው የወጣበት ጊዜና ለዳያስፖራው የቀረበው ጥሪ በመገጣጠሙ ነው።

• መመሪያው ለዳያስፖራው ከቀረበው ጥሪ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም። መመሪያው የሚመለከተው ተመላላሽ ነጋዴዎችን ብቻ መሆኑን ሁሉም የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ ይገባል።

• በቀረበው ጥሪ መሠረት ለሀገሩ አጋርነቱን ለመግለጽ ዳያስፖራው ሲመጣ አሠራሩን ቀላል አድርጎ ለመጠበቅ ከተዘጋጁት ተቋማት አንዱ የጉምሩክ መሥሪያ ቤት ነው።

• የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክም በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጥበታል።

Exit mobile version